Skip to content
← Jeremiah

Chapter 15 · Amharic

Jeremiah

1እግዚአብሔርም፡እንደዚህ፡አለኝ፦ሙሴና፡ሳሙኤል፡በፊቴ፡ቢቆሙም፥ልቤ፡ወደዚህ፡ሕዝብ፡ አይዘነብልም፤ከፊቴ፡ጣላቸው፤ይውጡ።

2እነርሱም፦ወዴት፡እንውጣ፡ቢሉኽ፥አንተ፦እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ለሞት፡የኾነ፡ወደ፡ ሞት፥ለሰይፍም፡የኾነ፡ወደ፡ሰይፍ፥ለራብም፡የኾነ፡ወደ፡ራብ፥ለምርኮም፡የኾነ፡ወደ፡ምርኮ፡ትላቸዋለኽ።

3ሰይፍን፡ለመግደል፡ውሻዎችንም፡ለመጐተት፡የሰማያትንም፡ወፎች፡የምድርንም፡አራዊት፡ለመብላትና፡ ለማጥፋት፥አራቱን፡ዐይነት፡ጥፋት፡አዝ፟ባቸዋለኹ፥ይላል፡እግዚአብሔር።

4የይሁዳም፡ንጉሥ፡የሕዝቅያስ፡ልጅ፡ምናሴ፡በኢየሩሳሌም፡ስላደረገው፡ዅሉ፡በምድር፡መንግሥታት፡ዅሉ፡ መካከል፡ለመከራ፡አሳልፌ፡እሰጣቸዋለኹ።

5ኢየሩሳሌም፡ሆይ፥የሚራራልሽ፡ማን፡ነው፧የሚያዝንልሽስ፡ማን፡ነው፧ወይስ፡ስለ፡ደኅንነትሽ፡ይጠይቅ፡ ዘንድ፡ፈቀቅ፡የሚል፡ማን፡ነው፧

6አንቺ፡እኔን፡ጥለሻል፥ይላል፡እግዚአብሔር፥ወደ፡ዃላሽም፡ተመልሰሻል፤ስለዚህ፥እጄን፡ባንቺ፡ላይ፡ ዘርግቼ፡አጥፍቼሻለኹ፤ከይቅርታ፡ደክሜያለኹ።

7በአገርም፡ደጆች፡ውስጥ፡በመንሽ፡አበጥሬያቸዋለኹ፤የወላድ፡መካን፡አድርጌያቸዋለኹ፥ሕዝቤንም፡ አጥፍቻለኹ፤ከመንገዳቸውም፡አልተመለሱም።

8መበለቶቻቸውም፡ከባሕር፡አሸዋ፡ይልቅ፡በዝተውብኛል፤በብላቴናዎች፡እናት፡ላይ፡በቀትር፡ጊዜ፡ አጥፊውን፡አምጥቻለኹ፤ጣርንና፡ድንጋጤን፡በድንገት፡አምጥቼባታለኹ።

9ሰባት፡የወለደች፡ደክማለች፥ነፍሷንም፡አውጥታለች፤ቀን፡ገና፡ሳለ፡ፀሓይዋ፡ገብታባታለች፤ዐፍራለች፡ ተዋርዳማለች፤የተረፉትንም፡በጠላቶቻቸው፡ፊት፡ለሰይፍ፡አሳልፌ፡እሰጣለኹ።

10እናቴ፡ሆይ፥ወዮልኝ! ለምድር፡ዅሉ፡የክርክርና፡የጥል፡ሰው፡የኾንኹትን፡ወለድሽኝ፡ለማንም፡ አላበደርኹም፥ማንም፡ለእኔ፡አላበደረም፥ነገር፡ግን፥ዅሉ፡ይረግመኛል።

11እግዚአብሔር፡እንዲህ፡አለ፦በእውነት፡ለደኅንነትኽ፡አጸናኻለኹ፤በእውነት፡በመከራና፡በጭንቅ፡ጊዜ፡ ጠላትኽ፡እንዲለምንኽ፡አደርገዋለኹ።

12በእውኑ፡ብረትን፥የሰሜንን፡ብረት፥ናስንም፡የሚሰብር፡አለን፧

13በዳርቻኽ፡ዅሉ፡ስለ፡አለ፡ኀጢአትኽ፡ዅሉ፡ባለጠግነትኽንና፡መዝገብኽን፡ለመበዝበዝ፡በከንቱ፡ እሰጣለኹ።

14የምታቃጥላችኹ፡እሳት፡ከቍጣዬ፡ትነዳ፟ለችና፡ከጠላቶችኽ፡ጋራ፡ወደማታውቀው፡ምድር፡አሳልፍኻለኹ።

15አቤቱ፥አንተ፡ታውቃለኽ፤ዐስበኝ፡ጐብኘኝም፡የሚያሳድዱኝንም፡ተበቀላቸው፡እንጂ፡አትታገሣቸው፤ስለ፡ አንተ፡ስድብን፡እንደ፡ታገሥኹ፡ዕወቅ።

16ቃልኽ፡ተገኝቷል፡እኔም፡በልቼዋለኹ፤አቤቱ፥የሰራዊት፡አምላክ፡ሆይ፥በስምኽ፡ተጠርቻለኹና፡ቃልኽ፡ ሐሤትና፡የልብ፡ደስታ፡ኾነኝ።

17በዋዘኛዎችና፡በደስተኛዎች፡ጉባኤ፡አልተቀመጥኹም፤ቍጣን፡ሞልተኽብኛልና፥በእጅኽ፡ፊት፡ለብቻዬ፡ ተቀመጥኹ።

18ስለ፡ምን፡ሕመሜ፡አዘወተረኝ፧ቍስሌስ፡ስለ፡ምን፡የማይፈወስ፡ኾነ፧ስለ፡ምንስ፦አልሽርም፡ አለ፧በእውኑ፡እንደ፡ሐሰተኛ፡ምንጭ፥እንዳልታመነች፡ውሃ፡ትኾነኛለኽን፧

19ስለዚህ፥እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ብትመለስ፡እመልስኻለኹ፡በፊቴም፡ትቆማለኽ፤የከበረውንም፡ ከተዋረደው፡ብትለይ፡እንደ፡አፌ፡ትኾናለኽ፤እነርሱ፡ወዳንተ፡ይመለሳሉ፥አንተ፡ግን፡ወደ፡እነርሱ፡ አትመለስም።

20ለዚህም፡ሕዝብ፡የተመሸገ፡የናስ፡ቅጥር፡አደርግኻለኹ፤ይዋጉኻል፡እኔ፡ግን፡ለማዳን፡ከአንተ፡ጋራ፡ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org ነኝና፡አያሸንፉኽም።

21ከክፉ፡ሰዎችም፡እጅ፡እታደግኻለኹ፥ከጨካኞችም፡ጡጫ፡እቤዥኻለኹ።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source