Skip to content
← Jeremiah

Chapter 16 · Amharic

Jeremiah

1የእግዚአብሔር፡ቃል፡ወደ፡እኔ፡እንዲህ፡ሲል፡መጣ፦

2በዚህ፡ስፍራ፡ሚስት፡አታግባ፥ወንዶችና፡ሴቶች፡ልጆችም፡አይኹኑልኽ።

3እግዚአብሔር፡በዚህ፡ስፍራ፡ስለተወለዱ፡ወንዶችና፡ሴቶች፡ልጆች፥ስለወለዷቸውም፡ስለ፡ እናቶቻቸው፥በዚችም፡ምድር፡ስለወለዷቸው፡ስለ፡አባቶቻቸው፡እንዲህ፡ይላልና፦

4በክፉ፡ሞት፡ይሞታሉ፤አይለቀስላቸውም፡አይቀበሩምም፥በመሬትም፡ላይ፡እንደ፡ጕድፍ፡ ይኾናሉ፤በሰይፍና፡በራብ፡ይጠፋሉ፥ሬሳቸውም፡ለሰማይ፡ወፎችና፡ለምድር፡አራዊት፡መብል፡ይኾናሉ።

5እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ሰላሜን፥ቸርነትና፡ምሕረትን፥ከዚህ፡ሕዝብ፡አስወግጃለኹና፡ልቅሶ፡ ወዳለበት፡ቤት፡አትግባ፥ታለቅስም፥ታዝንም፡ዘንድ፡አትኺድ።

6ታላላቆችና፡ታናናሾች፡በዚች፡ምድር፡ይሞታሉ፤አይቀበሩም፥ሰዎችም፡አያለቅሱላቸውም፥ስለ፡እነርሱም፡ ገላን፡አይነጩላቸውም፥ራስንም፡አይላጩላቸውም፤

7ሰዎችም፡ስለሞቱት፡ለማጽናናት፡የዕዝን፡እንጀራ፡አይቈርሱላቸውም፥ስለ፡አባታቸውና፡ስለ፡እናታቸውም፡ የመጽናናት፡ጽዋ፡አያጠጧቸውም።

8ትበላና፡ትጠጣ፡ዘንድ፡ከነርሱ፡ጋራ፡ለመቀመጥ፡ወደግብዣ፡ቤት፡አትግባ።

9የእስራኤል፡አምላክ፡የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላልና፦እንሆ፥በዐይናችኹ፡ፊት፡ በዘመናችኹም፡የእልልታን፡ድምፅና፡የደስታን፡ድምፅ፡የወንድ፡ሙሽራን፡ድምፅና፡የሴት፡ሙሽራን፡ድምፅ፡ ከዚህ፡ስፍራ፡አስቀራለኹ።

10ለዚህም፡ሕዝብ፡ይህን፡ቃል፡ዅሉ፡በተናገርኽ፡ጊዜ፦ይህን፡ዅሉ፡ታላቅ፡የኾነ፡ክፉ፡ነገርን፡ስለ፡ምን፡ እግዚአብሔር፡ተናገረብን፧በደላችንስ፡ምንድር፡ነው፧በአምላካችንስ፡በእግዚአብሔር፡ላይ፡የሠራነው፡ ኀጢአታችን፡ምንድር፡ነው፧ቢሉኽ፥

11አንተ፡እንዲህ፡ትላቸዋለኽ፦አባቶቻችኹ፡እኔን፡ስለ፡ተዉ፡ነው፥ይላል፡እግዚአብሔር፥ሌላዎችንም፡ አማልክት፡ተከተሉ፡አመለኳቸውም፡ሰገዱላቸውም፥እነርሱም፡ትተውኛል፥ሕጌንም፡አልጠበቁም፤እናንተም፡ ከአባቶቻችኹ፡ይልቅ፡ክፉ፡አድርጋችዃል፤እንሆም፥ዅላችኹ፡እንደ፡ክፉ፡ልባችኹ፡እልከኝነት፡ኼዳችዃል፡ እኔንም፡አልሰማችኹም።

13ስለዚህ፥ከዚች፡ምድር፡እናንተና፡አባቶቻችኹ፡ወዳላወቃችዃት፡ምድር፡እጥላችዃለኹ፤ምሕረትንም፡ አላደርግላችኹምና፥በዚያ፡ሌላዎችን፡አማልክት፡ቀንና፡ሌሊት፡ታመልካላችኹ።

14ስለዚህ፥እንሆ፦የእስራኤልን፡ልጆች፡ከግብጽ፡ምድር፡ያወጣ፡ሕያው፡እግዚአብሔርን! ዳግመኛ፡ የማይባልበት፡ዘመን፡ይመጣል፥ይላል፡እግዚአብሔር፤

15ነገር፡ግን፦የእስራኤልን፡ልጆች፡ከሰሜን፡ምድር፡ካሳደዳቸውም፡ምድር፡ዅሉ፡ያወጣ፡ሕያው፡ እግዚአብሔርን! ይባላል፤እኔም፡ለአባቶቻቸው፡ወደሰጠዃት፡ወደ፡ምድራቸው፡እመልሳቸዋለኹ።

16እንሆ፥ብዙ፡ዓሣ፡አጥማጆችን፡እሰዳ፟ለኹ፥ይላል፡እግዚአብሔር፥እነርሱም፡ያጠምዷቸዋል፤ከዚያም፡ በዃላ፡ብዙ፡አዳኞችን፡እሰዳ፟ለኹ፥እነርሱም፡ከየተራራውና፡ከየኰረብታው፡ዅሉ፡ከየድንጋዩም፡ስንጣቂ፡ውስጥ፡ ያድኗቸዋል።

17ዐይኔ፡በመንገዳቸው፡ዅሉ፡ላይ፡ነው፤ከፊቴም፡አልተሰወሩም፥ኀጢአታቸውም፡ከዐይኔ፡አልተሸሸገም።

18ምድሬንም፡በተጠሉ፡በጣዖቶቻቸው፡ሬሳዎች፡አርክሰዋልና፥ርስቴንም፡አስጸያፊ፡በኾኑ፡ነገሮች፡ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org ሞልተዋልና፥አስቀድሜ፡የበደላቸውንና፡የኀጢአታቸውን፡ዕዳ፡ኹለት፡ዕጥፍ፡እከፍላቸዋለኹ።

19አቤቱ፥ኀይሌ፥ዐምባዬ፥በመከራም፡ቀን፡መጠጊያዬ፡ሆይ፥ከምድር፡ዳርቻ፡አሕዛብ፡ወዳንተ፡ መጥተው፦በእውነት፡አባቶቻችን፡ውሸትንና፡ከንቱን፡ነገር፡የማይረባቸውንም፡ወርሰዋል፡ይላሉ።

20በእውኑ፡ሰው፡አማልክት፡ያልኾኑትን፡ለራሱ፡አማልክትን፡አድርጎ፡ይሠራልን፧

21ስለዚህ፥እንሆ፥አስታውቃቸዋለኹ፥በዚች፡ጊዜ፡እጄንና፡ኀይሌን፡አስታውቃቸዋለኹ፤እነርሱም፡ስሜ፡ እግዚአብሔር፡እንደ፡ኾነ፡ያውቃሉ።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source