Skip to content
← Jeremiah

Chapter 17 · Amharic

Jeremiah

1የይሁዳ፡ኀጢአት፡በብረት፡ብርዕና፡በተሾለ፡እብነ፡አልማዝ፡ተጽፏል፤በልባቸው፡ጽላትና፡በመሠዊያቸው፡ ቀንዶች፡ተቀርጿል።

2ልጆቻቸውም፡ከለመለሙ፡ዛፎች፡በታችና፡በረዘሙት፡ኰረብታዎች፡ላይ፡ያሉትን፡መሠዊያቸውንና፡ የማምለኪያ፡ዐጸዳቸውን፡ያስባሉ።

3በሜዳ፡ያለው፡ተራራዬ፡ሆይ፥ባለጠግነትኽንና፡መዝገብኽን፡ዅሉ፡የኰረብታውን፡መስገጃዎችኽም፡ስለ፡ ኀጢአት፡በድንበሮችኽ፡ዅሉ፡ለመበዝበዝ፡እሰጣለኹ።

4አንተም፡የሰጠኹኽን፡ርስት፡ትለቃ፟ለኽ፡ለዘለዓለምም፡በማታውቃትም፡ምድር፡ለጠላቶቻችኹ፡ባሪያ፡ አደርግኻለኹ፤ለዘለዓለም፡የሚነደ፟ውን፡እሳት፡በቍጣዬ፡አንድዳችዃልና።

5እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦በሰው፡የሚታመን፡ሥጋ፡ለባሹንም፡ክንዱ፡የሚያደርግ፡ልቡም፡ ከእግዚአብሔር፡የሚመለስ፡ሰው፡ርጉም፡ነው።

6በምድረ፡በዳ፡እንዳለ፡ቍጥቋጦ፡ይኾናል፥መልካምም፡በመጣ፡ጊዜ፡አያይም፤ሰውም፡በሌለበት፥ጨው፡ ባለበት፡ምድር፡በምድረ፡በዳ፡በደረቅ፡ስፍራ፡ይቀመጣል።

7በእግዚአብሔር፡የታመነ፡እምነቱም፡እግዚአብሔር፡የኾነ፡ሰው፡ቡሩክ፡ነው።

8በውሃ፡አጠገብ፡እንደ፡ተተከለ፥በወንዝም፡ዳር፡ሥሩን፡እንደሚዘረጋ፡ሙቀትም፡ሲመጣ፡እንደማይፈራ፡ ቅጠሉም፡እንደሚለመልም፥በድርቅ፡ዓመትም፡እንደማይሠጋ፡ፍሬውንም፡እንደማያቋርጥ፡ዛፍ፡ይኾናል።

9የሰው፡ልብ፡ከዅሉ፡ይልቅ፡ተንኰለኛ፡እጅግም፡ክፉ፡ነው፤ማንስ፡ያውቀዋል፧

10እኔ፡እግዚአብሔር፡ለሰው፡ዅሉ፡እንደ፡መንገዱ፥እንደ፡ሥራው፡ፍሬ፡እሰጥ፡ዘንድ፡ልብን፡ እመረምራለኹ፡ኵላሊትንም፡እፈትናለኹ።

11ያልወለደችውን፡እንደምታቅፍ፡ቆቅ፥እንዲሁ፡በቅን፡ሳይኾን፡ባለጠግነትን፡የሚሰበስብ፡ሰው፡ ነው፤በእኩሌታ፡ዘመኑ፡ይተወዋል፥በፍጻሜውም፡ሰነፍ፡ይኾናል።

12የመቅደሳችን፡ስፍራ፡ከጥንት፡ዠምሮ፡ከፍ፡ያለ፡የክብር፡ዙፋን፡ነው።

13አቤቱ፥የእስራኤል፡ተስፋ፡ሆይ፥የሚተዉኽ፡ዅሉ፡ያፍራሉ፤ከአንተም፡የሚለዩ፡የሕይወትን፡ውሃ፡ ምንጭ፡እግዚአብሔርን፡ትተዋልና፥በምድር፡ላይ፡ይጻፋሉ።

14አቤቱ፥ፈውሰኝ፡እኔም፡እፈወሳለኹ፤አድነኝ፡እኔም፡እድናለኹ፤አንተ፡ምስጋናዬ፡ነኽና።

15እንሆ፦የእግዚአብሔር፡ቃል፡ወዴት፡አለች፧አኹን፡ትምጣ፡ይሉኛል።

16እኔም፡አንተን፡ተከትዬ፡እረኛ፡ከመኾን፡አልቸኰልኹም፥የመከራንም፡ቀን፡አልወደድኹም፤አንተ፡ ታውቃለኽ፤ከከንፈሬ፡የወጣው፡በፊትኽ፡ነበረ።

17ለማስፈራራት፡አትኹንብኝ፤በመከራ፡ቀን፡አንተ፡መጠጊያዬ፡ነኽ።

18አሳዳጆቼ፡ይፈሩ፥እኔ፡ግን፡አልፈር፤እነርሱ፡ይደንግጡ፥እኔ፡ግን፡አልደንግጥ፤ክፉንም፡ቀን፡ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org አምጣባቸው፥በኹለት፡ዕጥፍ፡ጥፋት፡አጥፋቸው።

19እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይለኛል፦ኺድ፥የይሁዳም፡ነገሥታት፡በሚገቡበትና፡በሚወጡበት፡በሕዝቡ፡ ልጆች፡በር፡በኢየሩሳሌምም፡በሮች፡ዅሉ፡ቁም፤

20እንዲህም፡በላቸው፦በእነዚህ፡በሮች፡የምትገቡ፥እናንተ፡የይሁዳ፡ነገሥታት፥ይሁዳም፡ ዅሉ፥በኢየሩሳሌምም፡የምትኖሩ፡ዅሉ፥የእግዚአብሔርን፡ቃል፡ስሙ።

21እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ለራሳችኹ፡ተጠንቀቁ፥በሰንበትም፡ቀን፡ሸክም፡ አትሸከሙ፥በኢየሩሳሌምም፡በሮች፡አታግቡ፥

22ከቤቶቻችኹም፡በሰንበት፡ቀን፡ሸክምን፡አታውጡ፥ሥራንም፡ዅሉ፡አትሥሩበት፤አባቶቻችኹንም፡ እንዳዘዝኹ፡የሰንበትን፡ቀን፡ቀድሱ።

23እነርሱ፡ግን፡አልሰሙም፡ዦሯቸውን፡አላዘነበሉም፥እንዳይሰሙና፡እንዳይገሠጹም፡ዐንገታቸውን፡አደነደኑ።

24እኔን፡ፈጽሞ፡ብትሰሙ፤ይላል፡እግዚአብሔር፥በሰንበትም፡ቀን፡በዚች፡ከተማ፡በሮች፡ሸክም፡ ባታገቡ፥የሰንበትንም፡ቀን፡ብትቀድሱ፡ሥራንም፡ዅሉ፡ባትሠሩበት፥

25በዳዊት፡ዙፋን፡ላይ፡የሚቀመጡ፡ነገሥታትና፡መሳፍንት፡በሠረገላዎችና፡በፈረሶች፡ላይ፡እየተቀመጡ፡ በዚች፡ከተማ፡በሮች፡ይገባሉ፤እነርሱና፡መሳፍንቶቻቸው፡የይሁዳም፡ሰዎች፡በኢየሩሳሌምም፡የሚቀመጡ፡ ይገባሉ፥ይህችም፡ከተማ፡ለዘለዓለም፡የሰው፡መኖሪያ፡ትኾናለች።

26የሚቃጠለው፡መሥዋዕትና፡ሌላ፡መሥዋዕትን፡የእኽሉንም፡ቍርባን፡ዕጣኑንም፡የምስጋናውንም፡ መሥዋዕት፡ይዘው፡ከይሁዳ፡ከተማዎች፡ከኢየሩሳሌምም፡ዙሪያ፡ከብንያምም፡አገር፡ከቈላውም፡ከደጋውም፡ ከደቡብም፡ወደእግዚአብሔር፡ቤት፡ይመጣሉ።

27ነገር፡ግን፥የሰንበትን፡ቀን፡እንድትቀድሱ፥በሰንበትም፡ቀን፡ሸክምን፡ተሸክማችኹ፡በኢየሩሳሌም፡በሮች፡ እንዳትገቡ፡የነገርዃችኹን፡ባትሰሙኝ፥በበሮቿ፡ላይ፡እሳትን፡አነዳ፟ለኹ፥የኢየሩሳሌምንም፡አዳራሾች፡ ትበላለች፥አትጠፋም።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source