Skip to content
← Jeremiah

Chapter 20 · Amharic

Jeremiah

1በእግዚአብሔርም፡ቤት፡የተሾመው፡አለቃ፡የካህኑ፡የኢሜር፡ልጅ፡ጳስኮር፡ኤርምያስ፡በዚህ፡ነገር፡ ትንቢት፡ሲናገር፡ሰማ።

2ጳስኮርም፡ነቢዩን፡ኤርምያስን፡መታው፥በእግዚአብሔርም፡ቤት፡በነበረው፡በላይኛው፡በብንያም፡በር፡ ባለው፡በእግር፡ግንድ፡ውስጥ፡አኖረው።

3በነጋውም፡ጳስኮር፡ኤርምያስን፡ከግንድ፡ውስጥ፡አወጣው።ኤርምያስም፡እንዲህ፡አለው፦እግዚአብሔር፡ ስምኽን፦ማጎርሚሳቢብ፡እንጂ፡ጳስኮር፡ብሎ፡አይጠራኽም።

4እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላልና፦እንሆ፥ለራስኽና፡ለወዳጆችኽ፡ዅሉ፡ፍርሀት፡አደርግኻለኹ፤እነርሱም፡ በጠላቶቻቸው፡ሰይፍ፡ይወድቃሉ፡ዐይኖችኽም፡ያያሉ፤ይሁዳንም፡ዅሉ፡በባቢሎን፡ንጉሥ፡እጅ፡አሳልፌ፡ እሰጣለኹ፥ርሱም፡ወደ፡ባቢሎን፡ያፈልሳቸዋል፡በሰይፍም፡ይገድላቸዋል።

5የዚችንም፡ከተማ፡ባለጠግነት፡ዅሉ፡ጥሪቷንም፡ዅሉ፡ክብሯንም፡ዅሉ፡የይሁዳንም፡ነገሥታት፡መዝገብ፡ ዅሉ፡በጠላቶቻቸው፡እጅ፡አሳልፌ፡እሰጣለኹ፥እነርሱም፡ይበዘብዟቸዋል፡ይዘውም፡ወደ፡ባቢሎን፡ ያፈልሷቸዋል። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org

6አንተም፥ጳስኮር፡ሆይ፥በቤትኽም፡የሚኖሩት፡ዅሉ፡ተማርካችኹ፡ትኼዳላችኹ፤አንተም፡በሐሰትም፡ ትንቢት፡የተናገርኽላቸው፡ወዳጆችኽ፡ዅሉ፡ወደ፡ባቢሎን፡ትገባላችኹ፥በዚያም፡ትሞታላችኹ፥በዚያም፡ ትቀበራላችኹ።

7አቤቱ፥አታለልኸኝ፡እኔም፡ተታለልኹ፥ከእኔም፡በረታኽ፡አሸነፍኽም፤ቀኑን፡ዅሉ፡መሳቂያ፡ ኾኛለኹ፥ዅሉም፡ያላግጡብኛል።

8በተናገርኹ፡ቍጥር፡እጮኻለኹ፤ግፍና፡ጥፋት፡ብዬ፡እጮኻለኹ፤የእግዚአብሔር፡ቃል፡ቀኑን፡ዅሉ፡ ስድብና፡ዋዛ፡ኾኖብኛልና።

9እኔም፦የእግዚአብሔርን፡ስም፡አላነሣም፥ከእንግዲህ፡ወዲህም፡በስሙ፡አልናገርም፡ብል፥በዐጥንቶቼ፡ ውስጥ፡እንደ፡ገባ፡እንደሚነድ፟፡እሳት፡ያለ፡በልቤ፡ኾነብኝ፤ደከምኹ፥መሸከምም፡አልቻልኹም።

10የብዙ፡ሰዎችን፡ስድብ፡ሰምቻለኹ፥ማስፈራራትም፡ከቦ፟ኛል።መውደቄን፡የሚጠብቁ፡የሰላሜ፡ሰዎች፡ ዅሉ፦ምናልባት፡ይታለል፡እንደ፡ኾነ፥እናሸንፈውም፡እንደ፡ኾነ፥ርሱንም፡እንበቀል፡እንደ፡ኾነ፥ክሰሱት፡ እኛም፡እንከሰ፟ዋለን፡ይላሉ።

11እግዚአብሔር፡ግን፡እንደ፡ኀያልና፡እንደ፡ጨካኝ፡ከእኔ፡ጋራ፡ነው፤ስለዚህ፥አሳዳጆቼ፡ ይሰናከላሉ፥አያሸንፉም፤አይከናወንላቸውምና፥በጽኑ፡ዕፍረት፡ያፍራሉ፤ለዘለዓለምም፡በማይረሳ፡ጕስቍልና፡ ይጐሰቍላሉ።

12አቤቱ፥ጻድቅን፡የምትመረምር፡ኵላሊትንና፡ልብን፡የምትመለከት፡የሰራዊት፡ጌታ፡ሆይ፥ክርክሬን፡ ገልጬልኻለኹና፡በቀልኽን፡በላያቸው፡ለይ።

13ለእግዚአብሔር፡ዘምሩ፡እግዚአብሔርንም፡አመስግኑ፤የችግረኛውን፡ነፍስ፡ከክፉ፡አድራጊዎች፡እጅ፡ አድኗልና።

14የተወለድኹባት፡ቀን፡የተረገመች፡ትኹን፤እናቴ፡እኔን፡የወለደችባት፡ቀን፡የተባረከች፡አትኹን።

15ወንድ፡ልጅ፡ተወልዶልኻል፡ብሎ፡ለአባቴ፡የምሥራች፡ነግሮ፡ደስ፡ያሠኘው፡ሰው፡የተረገመ፡ይኹን።

16ያም፡ሰው፡እግዚአብሔር፡ሳይጸጸት፡እንደ፡ገለበጣቸው፡ከተማዎች፡ይኹን፥በማለዳም፡ልቅሶን፡በቀትርም፡ ጩኸትን፡ይስማ፤

17እናቴ፡መቃብር፡ትኾነኝ፡ዘንድ፡ማሕፀኗም፡ዘወትር፡ይዞኝ፡ያቈይ፡ዘንድ፡በማሕፀን፡ውስጥ፡ አልገደለኝምና።

18ድካምንና፡ጣርን፡አይ፡ዘንድ፡ዘመኔም፡በዕፍረት፡ታልቅ፡ዘንድ፡ስለ፡ምን፡ከማሕፀን፡ወጣኹ፧

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source