1ከእግዚአብሔር፡ዘንድ፡ወደ፡ኤርምያስ፡የመጣ፡ቃል፡ይህ፡ነው።
2ይህም፡የኾነው፡ንጉሡ፡ሴዴቅያስ፦የባቢሎን፡ንጉሥ፡ናቡከደነጾር፡ይወጋናልና፥ስለ፡ እኛ፥እባክኽ፥እግዚአብሔርን፡ጠይቅ፤ከእኛም፡ይመለስ፡ዘንድ፡ምናልባት፡እግዚአብሔር፡ከእኛ፡ጋራ፡እንደ፡ ተኣምራቱ፡ዅሉ፡ያደርግ፡ይኾናል፡ብሎ፡የመልክያን፡ልጅ፡ጳስኮርንና፡ካህኑን፡የመዕሴያን፡ልጅ፡ሶፎንያስ፡ ወደ፡ኤርምያስ፡በላከ፡ጊዜ፡ነው።
3ኤርምያስም፡እንዲህ፡አላቸው፦ሴዴቅያስን፡እንዲህ፡በሉት፦
4የእስራኤል፡አምላክ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦እንሆ፥የባቢሎንን፡ንጉሥ፡በቅጥርም፡ውጭ፡ የከበቧችኹን፡ከለዳውያንን፡የምትወጉበትን፡በእጃችኹ፡ያለውን፡ዕቃ፡ጦራችኹን፡እመልሰዋለኹ፥እነዚያንም፡ ወደዚች፡ከተማ፡ውስጥ፡እሰበስባቸዋለኹ።
5እኔም፡በተዘረጋች፡እጅና፡በብርቱ፡ክንድ፥በቍጣና፡በመዓት፡በታላቅም፡መቅሠፍት፡እወጋችዃለኹ። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org
6በዚችም፡ከተማ፡የሚኖሩትን፡ዅሉ፡ሰዎችንና፡እንስሳዎችን፡እመታለኹ፥በጽኑም፡ቸነፈር፡ይሞታሉ።
7ከዚህ፡በዃላ፥ይላል፡እግዚአብሔር፥የይሁዳን፡ንጉሥ፡ሴዴቅያስን፡ከቸነፈርና፡ከሰይፍ፡ከራብም፡በዚች፡ ከተማ፡የቀሩትንም፡ባሪያዎቹንና፡ሕዝቡን፡በባቢሎን፡ንጉሥ፡በናቡከደነጾር፡እጅ፡በጠላቶቻቸውና፡ነፍሳቸውንም፡ በሚሹት፡እጅ፡አሳልፌ፡እሰጣቸዋለኹ፤ርሱም፡በሰይፍ፡ስለት፡ ይመታቸዋል፤አያዝንላቸውም፥አይራራላቸውም፥አይምራቸውም።
8ለዚህም፡ሕዝብ፡እንዲህ፡በል፦እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦እንሆ፥በፊታችኹ፡የሕይወትን፡ መንገድና፡የሞትን፡መንገድ፡አድርጌያለኹ።
9በዚች፡ከተማ፡ውስጥ፡የሚዘገይ፥በሰይፍና፡በራብ፡በቸነፈርም፡ይሞታል፤ወጥቶ፡ወደከበቧችኹ፡ወደ፡ ከለዳውያን፡የሚገባ፡ግን፡በሕይወት፡ይኖራል፥ነፍሱም፡ምርኮ፡ትኾንለታለች።
10ለመልካም፡ሳይኾን፡ለክፉ፡ፊቴን፡በዚች፡ከተማ፡ላይ፡አድርጌያለኹና፤ለባቢሎን፡ንጉሥ፡እጅ፡ ትሰጣለች፥ርሱም፡በእሳት፡ያቃጥላታል።
11የይሁዳ፡ንጉሥ፡ቤት፡ሆይ፥የእግዚአብሔርን፡ቃል፡ስሙ።
12የዳዊት፡ቤት፡ሆይ፥እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ስለሥራችኹ፡ክፋት፡ቍጣዬ፡እንደ፡እሳት፡ እንዳይወጣና፡ማንም፡ሳያጠፋው፡እንዳይነድ፟፥በማለዳ፡ፍርድን፡አድርጉ፡የተበዘበዘውንም፡ካስጨናቂው፡እጅ፡ አድኑ።
13እንሆ፥በሸለቆው፡ውስጥ፡በሜዳ፡ላይም፡ባለው፡ዐምባ፡የምትቀመጪ፡ሆይ፥እኔ፡ባንቺ፡ላይ፡ ነኝ፤እናንተም፦በእኛ፡ላይ፡የሚወርድ፡ወይም፡ወደ፡መኖሪያችን፡የሚገባ፡ማን፡ነው፧የምትሉ፡ሆይ፥እኔ፡ በእናንተ፡ላይ፡ነኝ፤
14እንደ፡ሥራችኹም፡ፍሬ፡እቀጣችዃለኹ፤በዱሯም፡ውስጥ፡እሳትን፡አነዳ፟ለኹ፥በዙሪያዋም፡ያለውን፡ዅሉ፡ ይበላል።