Skip to content
← Jeremiah

Chapter 22 · Amharic

Jeremiah

1እግዚአብሔር፡እንዲህ፡አለ፦ወደይሁዳ፡ንጉሥ፡ቤት፡ውረድ፡በዚያም፡ይህን፡ቃል፡ተናገር፥

2እንዲህም፡በል፦በዳዊት፡ዙፋን፡የምትቀመጥ፡የይሁዳ፡ንጉሥ፡ሆይ፥አንተና፡ባሪያዎችኽ፡በእነዚህም፡ በሮች፡የሚገባ፡ሕዝብኽ፥የእግዚአብሔርን፡ቃል፡ስሙ።

3እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ፍርድንና፡ጽድቅን፡አድርጉ፡የተበዘበዘውንም፡ካስጨናቂው፡እጅ፡ አድኑ፤መጻተኛውንና፡ድኻ፡አደጉን፡መበለቲቱንም፡አትበድሉ፥አታምፁባቸውም፥በዚህም፡ስፍራ፡ንጹሕ፡ ደምን፡አታፍስሱ።

4ይህንንም፡ነገር፡ብታደርጉ፥በዳዊት፡ዙፋን፡የሚቀመጡ፡ነገሥታት፥በሠረገላዎችና፡በፈረሶች፡ላይ፡ ተቀምጠው፥በዚህ፡ቤት፡በሮች፡ይገባሉ፤ርሱም፡ባሪያዎቹም፡ሕዝቡም፡እንዲሁ፡ይገባሉ።

5ነገር፡ግን፥ይህን፡ቃል፡ባትሰሙ፥ይህ፡ቤት፡ወና፡እንዲኾን፡በራሴ፡ምያለኹ፥ይላል፡እግዚአብሔር።

6እግዚአብሔር፡ስለይሁዳ፡ንጉሥ፡ቤት፡እንዲህ፡ይላልና፦አንተ፡በእኔ፡ዘንድ፡እንደ፡ገለዓድና፡እንደ፡ ሊባኖስ፡ራስ፡ነኽ፥ነገር፡ግን፥በርግጥ፡ምድረ፡በዳ፡ማንም፡የማይቀመጥባቸውም፡ከተማዎች፡አደርግኻለኹ።

7መሣሪያም፡የሚይዙትን፡አጥፊዎች፡ባንተ፡ላይ፡አዘጋጃለኹ፥የተመረጡትንም፡የዝግባ፡ዛፎችኽን፡ ይቈርጣሉ፥በእሳትም፡ውስጥ፡ይጥሏቸዋል።

8ብዙ፡አሕዛብም፡በዚች፡ከተማ፡አጠገብ፡ያልፋሉ፥ዅሉም፡ባልንጀራዎቻቸውን፦እግዚአብሔር፡በዚች፡ ታላቅ፡ከተማ፡ለምን፡እንዲህ፡አደርገ፧ይላሉ።

9እነርሱም፦የአምላካቸውን፡የእግዚአብሔርን፡ቃል፡ኪዳን፡ትተው፡ለሌላዎች፡አማልክት፡ስለ፡ሰገዱ፡ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org ስላመለኳቸውም፡ነዋ፡ብለው፡ይመልሳሉ።

10ከእንግዲህ፡ወዲህ፡አይመለስምና፥የተወለደባትንም፡አገር፡አያይምና፡ለሚወጣ፡እጅግ፡አልቅሱ፡እንጂ፡ ለሞተ፡አታልቅሱ፡አትዘኑለትም።

11በአባቱ፡በኢዮስያስ፡ፋንታ፡ስለነገሠው፡ከዚህም፡ስፍራ፡ስለወጣው፡ስለይሁዳ፡ንጉሥ፡ስለኢዮስያስ፡ልጅ፡ ስለ፡ሰሎም፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላልና፦

12እንግዲህም፡ወደዚህ፡አይመለስም፥በተማረከባት፡አገር፡ይሞታል፡እንጂ፤ይህችንም፡አገር፡ከእንግዲህ፡ ወዲህ፡አያይም።

13ቤቱን፡በግፍ፡ሰገነቱንም፡በዐመፅ፡ለሚሠራ፥ባልንጀራውንም፡እንዲያው፡በከንቱ፡ለሚያሠራ፥ዋጋውንም፡ ለማይሰጠው፤

14ለራሴ፡ሰፊ፡ቤት፡ትልቅም፡ሰገነት፡እሠራለኹ፡ለሚል፥መስኮትንም፡ለሚያወጣ፥በዝግባም፡ሥራ፡ ለሚያሳጌጥ፥በቀይ፡ቀለምም፡ለሚቀባው፡ወዮለት!

15በዝግባ፡ዕንጨት፡ስለምትወዳደር፡በእውኑ፡ትነግሣለኽን፧በእውኑ፡አባትኽ፡አይበላምና፡አይጠጣም፡ ነበርን፧ፍርድንና፡ጽድቅንስ፡አያደርግም፡ነበርን፧በዚያም፡ጊዜ፡መልካም፡ኾኖለት፡ነበር።

16የድኻውንና፡የችግረኛውን፡ፍርድ፡ይፈርድ፡ነበር፥በዚያም፡ጊዜ፡መልካም፡ኾኖ፡ነበር።ይህ፡እኔን፡ ማወቅ፡አይደለምን፧ይላል፡እግዚአብሔር።

17ዐይንኽና፡ልብኽ፡ግን፡ለሥሥት፡ንጹሕ፡ደምንም፡ለማፍሰስ፡ዐመፅንና፡ግፍንም፡ለመሥራት፡ብቻ፡ነው።

18ስለዚህ፥እግዚአብሔር፡ስለይሁዳ፡ንጉሥ፡ስለኢዮስያስ፡ልጅ፡ስለ፡ኢዮአቄም፡እንዲህ፡ይላል፦ወንድሜ፡ ሆይ፥ወዮ! እያሉ፡አያለቅሱለትም፥ወይም፦ጌታ፡ሆይ፥ወዮ! እያሉ፡አያለቅሱለትም።

19አህያም፡እንደሚቀበር፡ይቀበራል፥ከኢየሩሳሌምም፡በር፡ወደ፡ውጭ፡ተጐትቶ፡ይጣላል።

20ውሽማዎችሽ፡ዅሉ፡ጠፍተዋልና፥ወደ፡ሊባኖስ፡ወጥተሽ፡ጩኺ፤በባሳን፡ላይ፡ድምፅሽን፡ አንሺ፤በዓባሪምም፡ውስጥ፡ኾነሽ፡ጩኺ።

21በደኅንነትሽ፡ጊዜ፡ተናገርኹሽ፤አንቺም፦አልሰማም፡አልሽ።ከሕፃንነትሽ፡ዠምሮ፡ቃሌን፡አለመስማትሽ፡ መንገድሽ፡ነው።

22በግ፡ጠባቂዎችሽን፡ዅሉ፡ነፋስ፡ይጠብቃቸዋል፥ውሽማዎችሽም፡ተማርከው፡ይኼዳሉ፤በዚያን፡ጊዜም፡ ስለ፡ክፋትሽ፡ዅሉ፡ታፍሪያለሽ፡ትጐሳቈይማለሽ።

23አንቺ፡በሊባኖስ፡የምትቀመጪ፥በዝግባ፡ዛፍም፡ውስጥ፡ጐዦሽን፡የምትሠሪ፡ሆይ፥ምጥ፡እንደ፡ያዛት፡ ሴት፡ሕማም፡በያዘሽ፡ጊዜ፡እንዴት፡ታጓሪያለሽ!

24እኔ፡ሕያው፡ነኝና፡የይሁዳ፡ንጉሥ፡የኢዮአቄም፡ልጅ፡ኢኮንያን፡የቀኝ፡እጄ፡ማኅተም፡ቢኾን፡ኖሮ፡ እንኳ፥ከዚያ፡እነቅልኽ፡ነበር፥ይላል፡እግዚአብሔር፤

25ነፍስኽንም፡ለሚሹት፡ለምትፈራቸውም፡እጅ፥ለባቢሎን፡ንጉሥ፡ለናቡከደነጾር፡ለከለዳውያንም፡እጅ፡ እሰጥኻለኹ።

26አንተንም፡የወለደችኽንም፡እናትኽን፡ወዳልተወለዳችኹባት፡ወደ፡ሌላ፡አገር፡እጥላችዃለኹ፥በዚያም፡ ትሞታላችኹ።

27ይመለሱባትም፡ዘንድ፡ነፍሳቸው፡ወደምትመኛት፡ወደዚያች፡ምድር፡አይመለሱም።

28በእውኑ፡ይህ፡ሰው፡ኢኮንያን፡የተናቀና፡የተሰበረ፡የሸክላ፡ዕቃ፡ነውን፧ወይስ፡ርሱ፡ለአንዳች፡የማይረባ፡ የሸክላ፡ዕቃ፡ነውን፧ርሱና፡ዘሩስ፡በማያውቋት፡ምድር፡ስለ፡ምን፡ተጥለው፡ወደቁ፧

29ምድር፡ሆይ፥ምድር፡ሆይ፥ምድር፡ሆይ፥የእግዚአብሔርን፡ቃል፡ስሚ። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org

30እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ከዚህ፡ሰው፡ዘር፡የሚከናወን፡በዳዊትም፡ዙፋን፡ላይ፡የሚቀመጥ፡ በይሁዳም፡የሚነግሥ፡እንግዲህ፡አይገኝምና።መካን፡በዘመኑም፡የማይከናወንለት፡ሰው፡ብላችኹ፡ጻፉ።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source