1የማሰማሪያዬን፡በጎች፡ለሚያጠፉና፡ለሚበትኑ፡እረኛዎች፡ወዮላቸው! ይላል፡እግዚአብሔር።
2ስለዚህ፥የእስራኤል፡አምላክ፡እግዚአብሔር፥ሕዝቤን፡ስለሚጠብቁ፡እረኛዎች፡እንዲህ፡ይላል፦በጎቼን፡ በትናችዃል፥አባራ፟ችዃቸውማል፥አልጐበኛችዃቸውምም፤እንሆ፥የሥራችኹን፡ክፋት፡ እጐበኝባችዃለኹ፥ይላል፡እግዚአብሔር።
3የመንጋዬም፡ቅሬታ፡ካባረርዃቸው፡ምድር፡ዅሉ፡ወደ፡በረታቸው፡ሰብስቤ፡እመልሳቸዋለኹ፤እነርሱም፡ ያፈራሉ፥ይበዙማል።
4የሚጠብቋቸውን፡እረኛዎች፡አስነሣላቸዋለኹ፥ዳግመኛም፡አይፈሩምና፡አይደነግጡም፥ከነሱም፡አንድ፡ አይጐድልም፥ይላል፡እግዚአብሔር።
5እንሆ፥ለዳዊት፡ጻድቅ፡ቍጥቋጥ፡የማስነሣበት፡ዘመን፡ይመጣል፥ይላል፡እግዚአብሔር፥ርሱም፡እንደ፡ ንጉሥ፡ይነግሣል፥ይከናወንለታልም፥በምድርም፡ፍርድንና፡ጽድቅን፡ያደርጋል።
6በዘመኑም፡ይሁዳ፡ይድናል፡እስራኤልም፡ተዘልሎ፡ይቀመጣል፥የሚጠራበትም፡ስም፦እግዚአብሔር፡ ጽድቃችን፡ተብሎ፡ነው።
7ስለዚህ፥እንሆ፦የእስራኤልን፡ልጆች፡ከግብጽ፡ምድር፡ያወጣ፡ሕያው፡እግዚአብሔርን! ዳግመኛ፡ የማይባልበት፡ዘመን፡ይመጣል፥ይላል፡እግዚአብሔር፤
8ነገር፡ግን፦የእስራኤልን፡ቤት፡ዘር፡ከሰሜን፡አገርና፡ካሰደድዃቸውም፡አገር፡ዅሉ፡ያወጣና፡የመራ፡ ሕያው፡እግዚአብሔርን! ይባላል፤በምድራቸውም፡ይቀመጣሉ።
9ስለ፡ነቢያት፤ልቤ፡በውስጤ፡ተሰብሯል፡ዐጥንቶቼም፡ዅሉ፡ታውከዋል፤ከእግዚአብሔር፡የተነሣ፡ከቅዱስ፡ ቃሉም፡የተነሣ፡የወይን፡ጠጅ፡እንዳሸነፈው፡እንደ፡ሰካራም፡ሰው፡ኾኛለኹ።
10ምድር፡ከአመንዝራዎች፡ተሞልታለችና፥ከመርገምም፡የተነሣ፡ምድር፡አልቅሳለች፤የምድረ፡በዳ፡ ማሰማሪያ፡ደርቋል፤አካኼዳቸው፡ክፉ፡ነው፥ብርታታቸውም፡ቅን፡አይደለም።
11ነቢዩና፡ካህኑም፡ረክሰዋልና፥በቤቴም፡ውስጥ፡ክፋታቸውን፡አግኝቻለኹ፥ይላል፡እግዚአብሔር።
12ስለዚህ፥መንገዳቸው፡በጨለማ፡እንዳለች፡እንደ፡ድጥ፡ስፍራ፡ትኾንባቸዋለች፥እነርሱም፡ፍግምግም፡ ብለው፡ይወድቁባታል፤እኔም፡በምጐበኛቸው፡ዓመት፡ክፉ፡ነገርን፡አመጣባቸዋለኹና፥ይላል፡እግዚአብሔር።
13በሰማርያ፡ነቢያት፡ላይ፡ስንፍናን፡አይቻለኹ፤በበዓል፡ትንቢት፡ይናገሩ፡ነበር፥ሕዝቤንም፡እስራኤል፡ያስቱ፡ ነበር።
14በኢየሩሳሌምም፡ነቢያት፡ላይ፡የሚያስደነግጥን፡ነገር፡አይቻለኹ፤ያመነዝራሉ፡በሐሰትም፡ይኼዳሉ፤ማንም፡ ከክፋቱ፡እንዳይመለስ፡የክፉ፡አድራጊዎችን፡እጅ፡ያበረታሉ፤ዅሉም፡እንደ፡ሰዶም፡የሚኖሩባትም፡እንደ፡ ገሞራ፡ኾኑብኝ።
15ስለዚህ፥እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦እንሆ፥ከኢየሩሳሌም፡ነቢያት፡ዘንድ፡ርኵሰት፡በምድር፡ዅሉ፡ ላይ፡ወጥቷልና፥ሬትን፡አበላቸዋለኹ፥የሐሞትንም፡ውሃ፡አጠጣቸዋለኹ።
16የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ትንቢት፡የሚናገሩላችኹን፡የነቢያትን፡ቃል፡ አትሰሙ፤ከንቱነትን፡ያስተምሯችዃል፤ከእግዚአብሔር፡አፍ፡ሳይኾን፡ከገዛ፡ልባቸው፡የወጣውን፡ራእይ፡ ይናገራሉ።
17ለሚንቁኝ፡ዅልጊዜ፦እግዚአብሔር፦ሰላም፡ይኾንላችዃል፡ብሏል፡ይላሉ፤በልቡም፡እልከኝነት፡ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org ለሚኼድ፡ዅሉ፦ክፉ፡ነገር፡አያገኛችኹም፡ይላሉ።
18ቃሉን፡ያይና፡ይሰማ፡ዘንድ፡በእግዚአብሔር፡ምክር፡የቆመ፡ማን፡ነውና፧ቃሉንስ፡ያደመጠ፡የሰማስ፡ ማን፡ነው፧
19እንሆ፥የእግዚአብሔር፡ዐውሎ፡ነፋስ፥ርሱም፡ቍጣው፥የሚያገለባብጥ፡ዐውሎ፡ነፍስ፡ ወጥቷል፤የዐመፀኛዎችን፡ራስ፡ይገለባብጣል።
20የእግዚአብሔር፡ቍጣ፡የልቡን፡ዐሳብ፡ሠርቶ፡እስኪፈጽም፡ድረስ፡አይመለስም፤በዃለኛው፡ዘመን፡ ፈጽማችኹ፡ታስተውሉታላችኹ።
21እኔ፡ሳል፟ካቸው፡እነዚህ፡ነቢያት፡ሮጡ፤እኔም፡ሳልነግራቸው፡ትንቢትን፡ተናገሩ።
22በምክሬ፡ግን፡ቢቆሙ፡ኖሮ፥ለሕዝቤ፡ቃሌን፡ባሰሙ፡ነበር፥ከክፉም፡መንገዳቸው፡ከሥራቸውም፡ክፋት፡ በመለሷቸው፡ነበር።
23እኔ፡የቅርብ፡አምላክ፡ነኝ፡እንጂ፡የሩቅ፡አምላክ፡አይደለኹም።
24ሰው፡በስውር፡ቢሸሸግ፥እኔ፡አላየውምን፧ሰማይንና፡ምድርንስ፡የሞላኹ፡እኔ፡አይደለኹምን፧ይላል፡ እግዚአብሔር።
25ዐለምኹ፥ዐለምኹ፡እያሉ፡በስሜ፡ሐሰትን፡የሚናገሩትን፡የነቢያትን፡ነገር፡ሰምቻለኹ።
26ትንቢትን፡በሐሰት፡በሚናገሩ፥የልባቸውንም፡ሽንገላ፡በሚናገሩ፡በነቢያት፡ልብ፡ይህ፡የሚኾነው፡እስከ፡ መቼ፡ነው፧
27አባቶቻቸው፡ስለ፡በዓል፡ስሜን፡እንደ፡ረሱ፥እያንዳንዱ፡ለባልንጀራው፡በሚናገራት፡ሕልማቸው፡ሕዝቤ፡ ስሜን፡ለማስረሳት፡ያስባሉ።
28የሚያልም፡ነቢይ፡ሕልምን፡ይናገር፤ቃሌም፡ያለበት፡ቃሌን፡በእውነት፡ይናገር።ገለባ፡ከስንዴ፡ጋራ፡ ምን፡አለው፧
29በእውኑ፡ቃሌ፡እንደ፡እሳት፥ድንጋዩንም፡እንደሚያደቅ፟፡መዶሻ፡አይደለችምን፧ይላል፡እግዚአብሔር።
30ስለዚህ፥እንሆ፥እያንዳንዱ፡ከባልንጀራው፡ዘንድ፡ቃሌን፡በሚሰርቁ፡ነቢያት፡ላይ፡ነኝ፥ይላል፡ እግዚአብሔር።
31እንሆ፥ከምላሳቸው፡ትንቢትን፡አውጥተው።ርሱ፡ይላል፡በሚሉ፡ነቢያት፡ላይ፡ነኝ፥ይላል፡እግዚአብሔር።
32እንሆ፥ሐሰትን፡በሚያልሙ፡በሚናገሩም፡በሐሰታቸውና፡በድፍረታቸውም፡ሕዝቤን፡በሚያስቱ፡በነቢያት፡ ላይ፡ነኝ፥ይላል፡እግዚአብሔር፤እኔም፡አልላክዃቸውም፡አላዘዝዃቸውምም፡ለእነዚህም፡ሕዝብ፡በማናቸውም፡ አይረቧቸውም፥ይላል፡እግዚአብሔር።
33ይህ፡ሕዝብ፡ወይም፡ነቢይ፡ወይም፡ካህን፦የእግዚአብሔር፡ሸክም፡ምንድር፡ነው፧ብሎ፡ ቢጠይቅኽ፥አንተ፦ሸክሙ፡እናንተ፡ናችኹ፥እጥላችኹማለኹ፥ይላል፡እግዚአብሔር፡ትላቸዋለኽ።
34የእግዚአብሔር፡ሸክም፡የሚለውን፡ነቢይንና፡ካህንን፡ሕዝቡንም፡ያን፡ሰውና፡ቤቱን፡እቀጣለኹ።
35አንዱም፡አንዱ፡ለባልንጀራው፥አንዱም፡አንዱ፡ለወንድሙ፡እንዲህ፡ይበል፦እግዚአብሔር፡የመለሰው፡ ምንድር፡ነው፧እግዚአብሔርስ፡ምን፡ነገር፡ተናገረ፧
36ለሰው፡ዅሉ፡ቃል፡ሸክም፡ይኾንበታልና፥የእግዚአብሔር፡ሸክም፡ይኾንበታልና፥የእግዚአብሔር፡ሸክም፡ ብላችኹ፡ከእንግዲህ፡ወዲህ፡አትጥሩ፤የሰራዊትን፡ጌታ፡የአምላካችንን፡የእግዚአብሔርን፡የሕያውን፡አምላክ፡ ቃል፡ለውጣችዃልና።
37ለነቢዩ፦እግዚአብሔር፡ምን፡መለሰልኽ፧እግዚአብሔርስ፡የተናገረው፡ምንድር፡ነው፧ትላለኽ።
38ነገር፡ግን፦የእግዚአብሔር፡ሸክም፡ብትሉ፥እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦እኔ፦የእግዚአብሔር፡ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org ሸክም፡አትበሉ፡ብዬ፡ልኬባችዃለኹና፥እናንተም፡ይህን፡ቃል፦
39የእግዚአብሔር፡ሸክም፡ብላችዃልና፥ስለዚህ፥እንሆ፥ፈጽሜ፡እረሳችዃለኹ፥እናንተንም፡ለእናንተና፡ ለአባቶቻችኹም፡የሰጠዃትን፡ከተማ፡ከፊቴ፡እጥላለኹ።
40የዘለዓለምንም፡ስድብ፡ከቶም፡ተረስቶ፡የማይጠፋውን፡የዘለዓለምን፡ዕፍረት፡አመጣባችዃለኹ።