Skip to content
← Jeremiah

Chapter 25 · Amharic

Jeremiah

1በይሁዳ፡ንጉሥ፡በኢዮስያስ፡ልጅ፡በኢዮአቄም፡በአራተኛው፡ዓመት፥በባቢሎን፡ንጉሥ፡በናቡከደነጾር፡ በመዠመሪያው፡ዓመት፥ስለይሁዳ፡ሕዝብ፡ዅሉ፡ወደ፡ኤርምያስ፡የመጣው፡ቃል፡ይህ፡ነው።

2ይህንም፡ቃል፡ነቢዩ፡ኤርምያስ፡ለይሁዳ፡ሕዝብ፡ዅሉና፡በኢየሩሳሌም፡ለተቀመጡ፡ዅሉ፡እንዲህ፡ሲል፡ ተናገረው፦

3ከይሁዳ፡ንጉሥ፡ከዓሞጽ፡ልጅ፡ከኢዮስያስ፡ከዐሥራ፡ሦስተኛው፡ዓመት፡ዠምሮ፡እስከ፡ዛሬ፡ድረስ፡ ባሉት፡በእነዚህ፡በኻያ፡ሦስቱ፡ዓመታት፥የእግዚአብሔር፡ቃል፡ወደ፡እኔ፡መጣ፥እኔም፡ማልጄ፡ተነሥቼ፡ ተናገርዃችኹ፤ነገር፡ግን፥አልሰማችኹም።

4እግዚአብሔርም፡ማልዶ፡ተነሥቶ፡ባሪያዎቹን፡ነቢያትን፡ወደ፡እናንተ፡ላከ፤እናንተም፡አላደመጣችኹም፡ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org ዦሯችኹንም፡አላዘነበላችኹም።

5ርሱም፦ዅላችኹ፡እናንተ፡ከክፉ፡መንገዳችኹና፡ከሥራችኹ፡ክፋት፡ተመለሱ፤እግዚአብሔርም፡ ከዘለዓለም፡ወደ፡ዘለዓለም፡ለእናንተና፡ለአባቶቻችኹ፡በሰጣችኹ፡ምድር፡ተቀመጡ።

6ታመልኳቸውም፡ትሰግዱላቸውም፡ዘንድ፡ሌላዎችን፡አማልክት፡አትከተሉ፥ክፉም፡እንዳላደርግባችኹ፡ በእጃችኹ፡ሥራ፡አታስቈጡኝ፡አለ።

7ለእናንተ፡ጕዳት፡እንዲኾን፡በእጃችኹ፡ሥራ፡ታስቈጡኝ፡ዘንድ፡አልሰማችኹኝም፥ይላል፡እግዚአብሔር።

8ስለዚህ፥የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ቃሌን፡አልሰማችኹምና፥እንሆ፥

9ልኬ፡የሰሜንን፡ወገኖች፡ዅሉ፡ባሪያዬንም፡የባቢሎንን፡ንጉሥ፡ናቡከደነጾርን፡እወስዳለኹ፥በዚችም፡ ምድር፡በሚቀመጡባትም፡ሰዎች፡በዙሪያዋም፡ባሉ፡በእነዚህ፡አሕዛብ፡ዅሉ፡ላይ፡አመጣቸዋለኹ፤ፈጽሜም፡ አጠፋቸዋለኹ፥ለመደነቂያና፡ለማፏጫም፡ለዘለዓለምም፡ባድማ፡አደርጋቸዋለኹ።

10ከነርሱም፡የእልልታን፡ድምፅና፡የደስታን፡ድምፅ፥የወንድ፡ሙሽራን፡ድምፅና፡የሴት፡ሙሽራን፡ ድምፅ፥የወፍጮንም፡ድምፅ፡የመብራትንም፡ብርሃን፡አስቀራለኹ።

11ይህችም፡ምድር፡ዅሉ፡ባድማና፡መደነቂያ፡ትኾናለች፤እነዚህም፡አሕዛብ፡ለባቢሎን፡ንጉሥ፡ሰባ፡ዓመት፡ ይገዛሉ።

12ሰባው፡ዓመትም፡በተፈጸመ፡ጊዜ፥የባቢሎንን፡ንጉሥና፡ያንን፡ሕዝብ፡ስለ፡ኀጢአታቸው፡ እቀጣለኹ፥ይላል፡እግዚአብሔር፥የከለዳውያንንም፡ምድር፡ለዘለዓለም፡ባድማ፡አደርጋታለኹ።

13በርሷም፡ላይ፡የተናገርኹትን፡ቃሌን፡ዅሉ፥ማለት፡ኤርምያስ፡በአሕዛብ፡ዅሉ፡ላይ፡ትንቢት፡ የተናገረውን፡በዚች፡መጽሐፍ፡የተጻፈውን፡ዅሉ፥በዚያች፡ምድር፡አመጣለኹ።

14ብዙ፡አሕዛብና፡ታላላቆች፡ነገሥታት፡እነርሱን፡ያስገዟቸዋል፤እኔም፡እንደ፡አደራረጋቸውና፡እንደ፡ እጃቸው፡ሥራ፡እከፍላቸዋለኹ።

15የእስራኤል፡አምላክ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይለኛል፦የዚህን፡ቍጣ፡የወይን፡ጠጅ፡ጽዋ፡ከእጄ፡ውሰድ፡ አንተንም፡የምሰድ፟ባቸውን፡አሕዛብን፡ዅሉ፡አጠጣቸው።

16ከምሰድ፟ባቸውም፡ሰይፍ፡የተነሣ፡ይጠጣሉ፡ይወላገዱማል፡ያብዳሉም።

17ከእግዚአብሔርም፡እጅ፡ጽዋውን፡ወሰድኹ፥እግዚአብሔርም፡እኔን፡የሰደደባቸውን፡አሕዛብ፡ዅሉ፡ አጠጣዃቸው።

18ዛሬ፡እንደኾነው፡ዅሉ፡ባድማና፡መደነቂያ፡ማፏጫም፡ርግማንም፡ኣደርጋቸው፡ዘንድ፡ኢየሩሳሌምንና፡ የይሁዳን፡ከተማዎች፡ነገሥታቷንም፡አለቃዎቿንም፡አጠጣዃቸው።

19የግብጽንም፡ንጉሥ፡ፈርዖንን፡ባሪያዎቹንም፡አለቃዎቹንም፡ሕዝቡንም፡ዅሉ፥

20የተደባለቀውንም፡ሕዝብ፡ዅሉ፥የዖፅ፡ምድር፡ነገሥታትንም፡ዅሉ፥የፍልስጥኤም፡ምድር፡ነገሥታትንም፡ ዅሉ፡አስቀሎናንም፡ጋዛንም፡ዐቃሮንንም፡የአዞጦንንም፡ቅሬታ፥

21ኤዶምያስንም፥ሞዐብንም፥የዐሞንም፡ልጆች፥

22የጤሮስን፡ነገሥታትም፡ዅሉ፥የሲዶናን፡ነገሥታት፡ዅሉ፥በባሕር፡ማዶ፡ያለች፡የደሴት፡ነገሥታትንም፥

23ድዳንንም፥ቴማንንም፥ቡዝንም፥ጠጕራቸውንም፡የሚቈርጡትን፡ዅሉ፥

24የዐረብ፡ነገሥታትንም፡ዅሉ፥በምድረ፡በዳ፡የሚቀመጡ፡የድብልቅ፡ሕዝብ፡ነገሥታትንም፡ዅሉ፥

25የዘምሪ፡ነገሥታትንም፡ዅሉ፥የዔላም፡ነገሥታትንም፡ዅሉ፥

26የሜዶን፡ነገሥታትንም፡ዅሉ፥የቀረቡና፡የራቁ፥አንዱ፡ከሌላው፡ጋራ፡ያሉ፡የሰሜን፡ነገሥታትንም፡ ዅሉ፥በምድር፡ፊት፡ላይ፡ያሉ፡የዓለም፡መንግሥታትንም፡ዅሉ፡አጠጣዃቸው፤የሼሻክም፡ንጉሥ፡ከነርሱ፡ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org በዃላ፡ይጠጣል።

27አንተም፦የእስራኤል፡አምላክ፡የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦በመካከላችኹ፡ከምሰደ፟ው፡ ሰይፍ፡የተነሣ፡ጠጡ፥ስከሩም፥አስታውኩም፡ውደቁም፥ከእንግዲህም፡ወዲህ፡አትነሡም፡በላቸው።

28ይጠጡም፡ዘንድ፡ጽዋውን፡ከእጅኽ፡ለመቀበል፡እንቢ፡ቢሉ፦የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ ይላል፦ፈጽማችኹ፡ትጠጣላችኹ፡በላቸው።

29እንሆ፥ስሜ፡የተጠራባትን፡ከተማ፡አስጨንቃት፡ዘንድ፡እዠምራለኹ፤በእውኑ፡እናንተ፡ያልተቀጣችኹ፡ ትኾናላችኹን፧በምድር፡በሚኖሩ፡ዅሉ፡ላይ፡ሰይፍን፡እጠራለኹና፡ያለቅጣት፡አትቀሩም፥ይላል፡የሰራዊት፡ ጌታ፡እግዚአብሔር።

30ስለዚህ፥ይህን፡ቃል፡ዅሉ፡ትንቢት፡ትናገርባቸዋለኽ፥እንዲህም፡ትላቸዋለኽ፦እግዚአብሔር፡በላይ፡ ኾኖ፡ይጮኻል፥በቅዱስ፡ማደሪያውም፡ኾኖ፡ድምፁን፡ያሰማል፤በበረቱ፡ላይ፡እጅግ፡ይጮኻል፥ወይንም፡ እንደሚጠምቁ፡በምድር፡በሚኖሩ፡ዅሉ፡ላይ፡ይጮኻል።

31እግዚአብሔር፡ከአሕዛብ፡ጋራ፡ክርክር፡አለውና፡ድምፅ፡እስከምድር፡ዳርቻ፡ድረስ፡ይደርሳል፤ከሥጋ፡ ለባሽ፡ዅሉ፡ጋራ፡ይፋረዳል፥ኀጢአተኛዎችንም፡ለሰይፍ፡አሳልፎ፡ይሰጣል፥ይላል፡እግዚአብሔር።

32የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦እንሆ፥ክፉ፡ነገር፡ከሕዝብ፡ወደ፡ሕዝብ፡ ይወጣል፥ጽኑም፡ዐውሎ፡ነፍስ፡ከምድር፡ዳርቻ፡ይነሣል።

33በዚያም፡ቀን፡የእግዚአብሔር፡ግዳዩች፡ከምድር፡ዳር፡ዠምሮ፡እስከምድር፡ዳር፡ድረስ፡ ይኾናሉ፤አይለቀስላቸውም፤በምድር፡ላይ፡እንደ፡ጕድፍ፡ይኾናሉ፡እንጂ፡አይከማቹም፡አይቀበሩምም።

34ትታረዱና፡ትበተኑ፡ዘንድ፡ቀናችኹ፡ደርሷልና፥እንደ፡ተወደደም፡የሸክላ፡ዕቃ፡ትወድቃላችኹና፡እናንተ፡ እረኛዎች፥አልቅሱ፡ጩኹም፤እናንተ፡የመንጋ፡አውራዎች፥በዐመድ፡ውስጥ፡ተንከባለሉ።

35ሽሽትም፡ከእረኛዎች፡ማምለጥም፡ከመንጋ፡አውራዎች፡ይጠፋል።

36እግዚአብሔር፡ማሰማሪያቸውን፡አጥፍቷልና፥የእረኛዎች፡ጩኸት፡ድምፅ፡የመንጋ፡አውራዎችም፡ልቅሶ፡ ኾኗል።

37ከእግዚአብሔር፡ጽኑ፡ቍጣ፡የተነሣ፡የሰላም፡በረት፡ፈርሷል።

38እንደ፡አንበሳ፡መደቡን፡ለቋ፟ል፤ካስጨናቂውም፡ሰይፍና፡ከጽኑ፡ቍጣው፡የተነሣ፡ምድራቸው፡ባድማ፡ ኾናለችና።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source