Skip to content
← Jeremiah

Chapter 26 · Amharic

Jeremiah

1በይሁዳ፡ንጉሥ፡በኢዮስያስ፡ልጅ፡በኢዮአቄም፡መንግሥት፡መዠመሪያ፡ይህ፡ቃል፡ከእግዚአብሔር፡ዘንድ፡ መጣ።

2እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦በእግዚአብሔር፡ቤት፡አደባባይ፡ቁም፥በእግዚአብሔርም፡ቤት፡ውስጥ፡ ይሰግዱ፡ዘንድ፡ለሚመጡት፡ለይሁዳ፡ከተማዎች፡ዅሉ፡ትነግራቸው፡ዘንድ፡ያዘዝኹኽን፡ቃል፡ዅሉ፡ ተናገራቸው፤አንዲትም፡ቃል፡አታጕድል።

3ምናልባት፡ይሰሙ፥ከክፉ፡መንገዳቸውም፡ይመለሱ፡ይኾናል፤እኔም፡ስለሥራቸው፡ክፋት፡ያሰብኹባቸውን፡ ክፉ፡ነገር፡እተዋለኹ።

4እንዲህም፡በላቸው፦እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦በፊታችኹ፡በሰጠዃት፡ሕጌ፡ትኼዱ፡ዘንድ፡ ባትሰሙኝ፥

5ያልሰማችኹትን፡በማለዳ፡ተነሥቼ፡ወደ፡እናንተ፡የላክዃቸውን፡የባሪያዎቼን፡የነቢያትን፡ቃል፡ባትሰሙ፥

6ይህን፡ቤት፡እንደ፡ሴሎ፡አደርገዋለኹ፥ይህችንም፡ከተማ፡ለምድር፡አሕዛብ፡ዅሉ፡ርግማን፡ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org አደርጋታለኹ።

7ካህናቱም፡ነቢያቱም፡ሕዝቡም፡ዅሉ፡ኤርምያስ፡በእግዚአብሔር፡ቤት፡ይህን፡ቃል፡ሲናገር፡ሰሙ።

8ኤርምያስም፡ለሕዝቡ፡ዅሉ፡ይናገር፡ዘንድ፡እግዚአብሔር፡ያዘዘውን፡ነገር፡ዅሉ፡በፈጸመ፡ጊዜ፡ካህናትና፡ ነቢያት፡ሕዝቡም፡ዅሉ፦ሞትን፡ትሞታለኽ።

9በእግዚአብሔር፡ስም፦ይህ፡ቤት፡እንደ፡ሴሎ፡ይኾናል፥ይህችም፡ከተማ፡ባድማና፡ወና፡ትኾናለች፡ ብለኽ፡ስለ፡ምን፡ትንቢት፡ተናገርኽ፧ብለው፡ያዙት።ሕዝቡም፡ዅሉ፡በእግዚአብሔር፡ቤት፡ውስጥ፡ በኤርምያስ፡ላይ፡ተሰብስበው፡ነበር።

10የይሁዳም፡አለቃዎች፡ይህን፡በሰሙ፡ጊዜ፡ከንጉሥ፡ቤት፡ወደእግዚአብሔር፡ቤት፡ወጡ፥በዐዲሱም፡ በእግዚአብሔር፡ቤት፡ደጅ፡መግቢያ፡ተቀመጡ።

11ካህናቱና፡ነቢያቱም፡ለአለቃዎቹና፡ለሕዝቡ፡ዅሉ፦በዦሯችኹ፡እንደ፡ሰማችኹ፡በዚች፡ከተማ፡ላይ፡ ትንቢት፡ተናግሯልና፥ይህ፡ሰው፡ሞት፡የሚገ፟ባ፟ው፡ነው፡ብለው፡ተናገሩ።

12ኤርምያስም፡ለአለቃዎችና፡ለሕዝቡ፡ዅሉ፡እንዲህ፡ብሎ፡ተናገረ፦በሰማችኹት፡ቃል፡ዅሉ፡በዚች፡ ቤትና፡በዚች፡ከተማ፡ላይ፡ትንቢት፡እናገር፡ዘንድ፡እግዚአብሔር፡ልኮኛል።

13አኹንም፡መንገዳችኹንና፡ሥራችኹን፡አሳምሩ፥የአምላካችኹንም፡የእግዚአብሔርን፡ቃል፡ ስሙ፤እግዚአብሔርም፡የተናገረባችኹን፡ክፉ፡ነገር፡ይተዋል።

14እኔ፡ግን፥እንሆ፥በእጃችኹ፡ነኝ፤በዐይናችኹ፡መልካምና፡ቅን፡የመሰለውን፡አድርጉብኝ።

15ነገር፡ግን፥ይህን፡ቃል፡ዅሉ፡በዦሯችኹ፡እናገር፡ዘንድ፡በእውነት፡እግዚአብሔር፡ወደ፡እናንተ፡ ልኮኛልና፥ብትገድሉኝ፡ንጹሕ፡ደምን፡በራሳችኹና፡በዚች፡ከተማ፡በሚኖሩባትም፡ላይ፡እንድታመጡ፡በርግጥ፡ ዕወቁ።

16አለቃዎቹና፡ሕዝቡም፡ዅሉ፡ለካህናትና፡ለነቢያት፦ይህ፡ሰው፡በአምላካችን፡በእግዚአብሔር፡ስም፡ ተናግሮናልና፥ሞት፡አይገ፟ባ፟ውም፡አሉ።

17ከአገሩ፡ሽማግሌዎችም፡ሰዎች፡ተነሥተው፡ለሕዝቡ፡ጉባኤ፡ዅሉ፡እንዲህ፡ብለው፡ተናገሩ።

18ሞሬታዊው፡ሚክያስ፡በይሁዳ፡ንጉሥ፡በሕዝቅያስ፡ዘመን፡ነቢይ፡ነበረ፤ለይሁዳም፡ሕዝብ፡ ዅሉ፦የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ጽዮን፡እንደ፡ዕርሻ፡ትታረሳለች፥ኢየሩሳሌም፡ የፍርስራሽ፡ክምር፡ትኾናለች፥የቤቱም፡ተራራ፡እንደ፡ዱር፡ከፍታ፡ይኾናል፡ብሎ፡ተናገረ።

19በእውኑ፡የይሁዳ፡ንጉሥ፡ሕዝቅያስና፡ሕዝቡ፡ዅሉ፡ገደሉትን፧በእውኑ፡እግዚአብሔርን፡ አልፈሩምን፧ወደ፡እግዚአብሔርስ፡አልተማለሉምን፧እግዚአብሔርስ፡የተናገረባቸውን፡ክፉ፡ነገር፡ አይተውምን፧እኛም፡በነፍሳችን፡ላይ፡ታላቅ፡ክፋት፡እናደርጋለን።

20ደግሞም፡በእግዚአብሔር፡ስም፡ትንቢት፡የተናገረ፡አንድ፡ሰው፡ነበረ፤ርሱም፡የቂርያትይዓሪም፡ ሰው፥የሸማያ፡ልጅ፥ኦርዮ፡ይባል፡ነበር፤በዚችም፡ከተማ፡በዚችም፡ምድር፡ላይ፡እንደ፡ኤርምያስ፡ቃል፡ ዅሉ፡ትንቢት፡ተናገረ።

21ንጉሡም፡ኢዮአቄም፡ኀያላኑም፡ዅሉ፡አለቃዎቹም፡ዅሉ፡ቃሉን፡በሰሙ፡ጊዜ፡ንጉሡ፡ሊገድለው፡ ፈለገ፤ኦርዮም፡ይህን፡በሰማ፡ጊዜ፡ፈርቶ፡ሸሸ፡ወደ፡ግብጽም፡ገባ።

22ንጉሡም፡ኢዮአቄም፡የዓክቦርን፡ልጅ፡ኤልናታንን፡ከርሱም፡ጋራ፡ሌላዎችን፡ሰዎች፡ወደ፡ግብጽ፡ ላካቸው፤

23ከግብጽም፡ኦርዮን፡አውጥተው፡ወደ፡ንጉሡ፡ወደ፡ኢዮአቄም፡ይዘውት፡መጡ፤ርሱም፡በሰይፍ፡ ገደለው፡ሬሳውንም፡ክቡራን፡ባልኾኑ፡ሰዎች፡መቃብር፡ጣለው።

24ነገር፡ግን፥በሕዝቡ፡እጅ፡እንዳይሰጥና፡እንዳይገድሉት፡የሳፋን፡ልጅ፡የአኪቃም፡እጅ፡ከኤርምያስ፡ጋራ፡ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org ነበረች።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source