1በይሁዳ፡ንጉሥ፡በኢዮስያስ፡ልጅ፡በኢዮአቄም፡መንግሥት፡መዠመሪያ፡ይህ፡ቃል፡ከእግዚአብሔር፡ዘንድ፡ ወደ፡ኤርምያስ፡መጣ።
2እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይለኛል፦እስራትና፡ቀንበር፡ሥራ፡በዐንገትኽም፡ላይ፡አድርግ፤
3ወደይሁዳ፡ንጉሥም፡ወደ፡ሴዴቅያስ፡ወደ፡ኢየሩሳሌም፡በመጡት፡መልእክተኛዎች፡እጅ፡ወደኤዶምያስ፡ ንጉሥ፡ወደሞዐብም፡ንጉሥ፡ወደዐሞንም፡ልጆች፡ንጉሥ፡ወደጢሮስም፡ንጉሥ፡ወደሲዶናም፡ንጉሥ፡ላካቸው።
4ለጌታዎቻቸውም፡እንዲነግሩ፡እንዲህ፡ብለኽ፡እዘዛቸው፦የእስራኤል፡አምላክ፡የሰራዊት፡ጌታ፡ እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ለጌታዎቻችኹ፡እንዲህ፡በሉ።
5ምድሪቱን፡በምድርም፡ፊት፡ላይ፡ያሉትን፡ሰዎችንና፡እንስሳዎችን፡በታላቅ፡ኀይሌና፡በተዘረጋችው፡ክንዴ፡ ፈጥሬያለኹ፤ለዐይኔም፡መልካም፡ለኾነው፡እሰጣታለኹ።
6አኹንም፡እነዚህን፡ምድሮች፡ዅሉ፡ለባሪያዬ፡ለባቢሎን፡ንጉሥ፡ለናቡከደነጾር፡እጅ፡አሳልፌ፡ ሰጥቻለኹ፤ይገዙለትም፡ዘንድ፡የምድረ፡በዳ፡አራዊትን፡ደግሞ፡ሰጥቼዋለኹ።
7የገዛ፡ራሱም፡ምድር፡ጊዜ፡እስኪመጣ፡ድረስ፡አሕዛብ፡ዅሉ፡ለርሱና፡ለልጅ፡ለልጅ፡ልጁም፡ ይገዛሉ፤በዚያን፡ጊዜም፡ብዙ፡አሕዛብና፡ታላላቆች፡ነገሥታት፡ርሱን፡ያስገዙታል።
8ለባቢሎን፡ንጉሥም፡ለናቡከደነጾር፡የማይገዛውን፥ከባቢሎንም፡ንጉሥ፡ቀንበር፡በታች፡ዐንገቱን፡ዝቅ፡ የማያደርገውን፡ሕዝብና፡መንግሥት፥ያን፡ሕዝብ፡በእጁ፡እስካጠፋው፡ድረስ፥በሰይፍና፡በራብ፡በቸነፈርም፡ እቀጣለኹ፥ይላል፡እግዚአብሔር።
9እናንተ፡ግን፦ለባቢሎን፡ንጉሥ፡አትገዙም፡የሚሏችኹን፡ነቢያታችኹንና፡ሟርተኛዎቻችኹን፥ሕልም፡ ዐላሚዎቻችኹንና፡ቃላ፟ተኛዎቻችኹን፡መተተኛዎቻችኹንም፡አትስሙ፤
10ከምድራችኹ፡እንዲያርቋችኹ፥እኔም፡እንዳሳድዳችኹ፡እናንተም፡እንድትጠፉ፡ሐሰተኛ፡ትንቢትን፡ ይናገሩላችዃልና።
11ነገር፡ግን፥ከባቢሎን፡ንጉሥ፡ቀንበር፡በታች፡ዐንገቱን፡ዝቅ፡የሚያደርገውንና፡የሚገዛለትን፡ሕዝብ፡ በአገሩ፡ላይ፡እተወዋለኹ፤እነርሱም፡ያርሷታል፡ይቀመጡባትማል።
12ለይሁዳ፡ንጉሥ፡ለሴዴቅያስም፡በዚህ፡ቃል፡ተናገርኹ፦ከባቢሎን፡ንጉሥ፡ቀንበር፡በታች፡ዐንገታችኹን፡ ዝቅ፡አድርጉ፥ለርሱና፡ለሕዝቡም፡ተገዙላቸው፥በሕይወትም፡ኑሩ።
13ለባቢሎን፡ንጉሥ፡ይገዛ፡ዘንድ፡እንቢ፡ስለ፡አለ፡ሕዝብ፡እግዚአብሔር፡እንደ፡ተናገረ፥አንተና፡ ሕዝብኽ፡በሰይፍና፡በራብ፡በቸነፈርም፡ለምን፡ትሞታላችኹ፧
14ሐሰተኛን፡ትንቢት፡ይናገሩላችዃልና።ለባቢሎን፡ንጉሥ፡አትገዙም፡የሚሏችኹን፡የነቢያትን፡ቃል፡ አትስሙ።
15እኔ፡አልላክዃቸውምና፤ነገር፡ግን፥እኔ፡እንዳሳድዳችኹ፥እናንተና፡ትንቢት፡የሚናገሩላችኹ፡ነቢያትም፡ እንድትጠፉ፡በስሜ፡ሐሰተኛ፡ትንቢትን፡ይናገራሉ፥ይላል፡እግዚአብሔር።
16ለካህናትም፡ለዚህም፡ሕዝብ፡እንዲህ፡ብዬ፡ተናገርኹ፦እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ሐሰተኛውን፡ ትንቢት፡ይናገሩላችዃልና፦የእግዚአብሔር፡ቤት፡ዕቃ፡በቅርብ፡ጊዜ፡ከባቢሎን፡ይመለሳል፡የሚሏችኹን፡ የነቢያታችኹን፡ቃል፡አትስሙ።
17እነርሱም፡አትስሙ፤ለባቢሎን፡ንጉሥ፡ተገዙ፡በሕይወትም፡ኑሩ።ይህችስ፡ከተማ፡ስለ፡ምን፡ባድማ፡ ትኾናለች፧ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org
18እነርሱ፡ግን፡ነቢያት፡ቢኾኑ፥የእግዚአብሔርም፡ቃል፡በእነርሱ፡ዘንድ፡ቢገኝ፥በእግዚአብሔር፡ቤትና፡ በይሁዳ፡ንጉሥ፡ቤት፡በኢየሩሳሌምም፡የቀረችው፡ዕቃ፡ወደ፡ባቢሎን፡እንዳትኼድ፡ወደሰራዊት፡ጌታ፡ወደ፡ እግዚአብሔር፡ይማለሉ። 19-
20የባቢሎን፡ንጉሥ፡ናቡከደነጾር፡የይሁዳን፡ንጉሥ፡የኢዮአቄምን፡ልጅ፡ኢኮንያንንና፡የይሁዳንና፡ የኢየሩሳሌምን፡ከበርቴዎች፡ዅሉ፡ማርኮ፡ከኢየሩሳሌም፡ወደ፡ባቢሎን፡ባፈለሳቸው፡ጊዜ፡ስላልወሰዳቸው፡ ዐምዶች፡ስለ፡ኵሬውም፡ስለ፡መቀመጫዎቹም፡በዚችም፡ከተማ፡ስለቀረች፡ዕቃ፡ዅሉ፡የሰራዊት፡ጌታ፡ እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላልና፤
21በእግዚአብሔር፡ቤትና፡በይሁዳ፡ንጉሥ፡ቤት፡በኢየሩሳሌምም፡ስለቀረችው፡ዕቃ፡የእስራኤል፡አምላክ፡ የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦
22ወደ፡ባቢሎን፡ትወሰዳለች፡እስከምጐበኛትም፡ቀን፡ድረስ፡በዚያ፡ትኖራለች፥ይላል፡ እግዚአብሔር፤በዚያን፡ጊዜም፡አወጣታለኹ፡ወደዚህም፡ስፍራ፡እመልሳታለኹ።