1በዚያም፡ዓመት፡በይሁዳ፡ንጉሥ፡በሴዴቅያስ፡መንግሥት፡መዠመሪያ፡በአራተኛው፡ዓመት፡በዐምስተኛው፡ ወር፡ነቢዩ፡የገባዖን፡ሰው፡የዓዙር፡ልጅ፡ሐናንያ፡በእግዚአብሔር፡ቤት፡በካህናትና፡በሕዝብ፡ዅሉ፡ፊት፡ እንዲህ፡ብሎ፡ተናገረኝ።
2የእስራኤል፡አምላክ፡የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ብሎ፡ይናገራል።የባቢሎንን፡ንጉሥ፡ቀንበር፡ ሰብሬያለኹ።
3የባቢሎን፡ንጉሥ፡ናቡከደነጾር፡ከዚች፡ስፍራ፡ወደ፡ባቢሎን፡የወሰዳትን፡የእግዚአብሔርን፡ቤት፡ዕቃ፡ዅሉ፡ በኹለት፡ዓመት፡ውስጥ፡ወደዚች፡ስፍራ፡እመልሳታለኹ፤
4ወደ፡ባቢሎንም፡የኼዱትን፡የይሁዳን፡ንጉሥ፡የኢዮአቄምን፡ልጅ፡ኢኮንያንንና፡የይሁዳን፡ምርኮ፡ዅሉ፡ ወደዚች፡ስፍራ፡እመልሳቸዋለኹ፤የባቢሎንን፡ንጉሥ፡ቀንበር፡እሰብራለኹና።
5ነቢዩ፡ኤርምያስም፡በካህናቱና፡በእግዚአብሔር፡ቤት፡በቆሙት፡ሕዝብ፡ዅሉ፡ፊት፡ለነቢዩ፡ለሐናንያ፡ ተናገረ።
6ነቢዩም፡ኤርምያስ፡እንዲህ፡አለ፦አሜን፥እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ያድርግ፤የእግዚአብሔርን፡ቤት፡ዕቃ፡ ምርኮውንም፡ዅሉ፡ከባቢሎን፡ወደዚህ፡ስፍራ፡በመመለስ፡እግዚአብሔር፡የተናገርኸውን፡ትንቢት፡ይፈጽም።
7ነገር፡ግን፥በዦሮኽና፡በሕዝብ፡ዅሉ፡ዦሮ፡የምናገረውን፡ይህን፡ቃል፡ስማ፤
8ከጥንት፡ከእኔና፡ከአንተ፡በፊት፡የነበሩ፡ነቢያት፡በብዙ፡አገርና፡በታላላቅ፡መንግሥታት፡ላይ፡ስለ፡ሰልፍና፡ ስለ፡ክፉ፡ነገር፡ስለ፡ቸነፈርም፡ትንቢት፡ተናገሩ።
9ስለ፡ሰላም፡የተናገረ፡ነቢይ፥የነቢዩ፡ቃል፡በኾነ፡ጊዜ፥እግዚአብሔር፡በእውነት፡የሰደደው፡ነቢይ፡እንደ፡ ኾነ፡ይታወቃል።
10ነቢዩም፡ሐናንያ፡ቀንበሩን፡ከነቢዩ፡ከኤርምያስ፡ዐንገት፡ወስዶ፡ሰበረው።
11ሐናንያም፡በሕዝብ፡ዅሉ፡ፊት፦እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦እንዲሁ፡በኹለት፡ዓመት፡ውስጥ፡ የባቢሎንን፡ንጉሥ፡የናቡከደነጾርን፡ቀንበር፡ከአሕዛብ፡ዅሉ፡ዐንገት፡እሰብራለኹ፡አለ።ነቢዩም፡ኤርምያስ፡ መንገዱን፡ኼደ።
12ነቢዩም፡ሐናንያ፡ቀንበሩን፡ከነቢዩ፡ከኤርምያስ፡ዐንገት፡ከሰበረ፡በዃላ፥የእግዚአብሔር፡ቃል፡ወደ፡ ኤርምያስ፡እንዲህ፡ሲል፡መጣ፦
13ኺድ፥ለሐናንያ፡እንዲህ፡ብለኽ፡ንገረው፦እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦አንተ፡የዕንጨትን፡ቀንበር፡ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org ሰብረኻል፥እኔ፡ግን፡በርሱ፡ፋንታ፡የብረትን፡ቀንበር፡እሠራለኹ።
14የእስራኤልም፡አምላክ፡የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላልና፦ለባቢሎን፡ንጉሥ፡ለናቡከደነጾር፡ ይገዙለት፡ዘንድ፡የብረትን፡ቀንበር፡በእነዚህ፡አሕዛብ፡ዅሉ፡ዐንገት፡ላይ፡አድርጌያለኹ፤እነርሱም፡ ይገዙለታል፥የምድረ፡በዳ፡አራዊት፡ደግሞ፡ሰጥቼዋለኹ።
15ነቢዩም፡ኤርምያስ፡ነቢዩን፡ሐናንያን፦ሐናንያ፡ሆይ፥ስማ፤ይህ፡ሕዝብ፡በሐሰት፡እንዲታመን፡ አድርገኻል፡እንጂ፡እግዚአብሔር፡አላ፟ከኽም።
16ስለዚህ፥እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦እንሆ፥ከምድር፡ላይ፡እሰድ፟ኻለኹ፤በእግዚአብሔር፡ላይ፡ ዐመፅን፡ተናግረኻልና፥በዚህ፡ዓመት፡ትሞታለኽ፡አለው።
17ነቢዩም፡ሐናንያ፡በዚያው፡ዓመት፡በሰባተኛው፡ወር፡ሞተ።