1ነቢዩ፡ኤርምያስ፡ወደተረፉት፡የምርኮ፡ሽማግሌዎች፥ወደ፡ካህናቱም፥ወደ፡ነቢያቱም፥ናቡከደነጾር፡ ከኢየሩሳሌም፡ወደ፡ባቢሎን፡ማርኮ፡ወዳፈለሰውም፡ሕዝብ፡ዅሉ፡ከኢየሩሳሌም፡የላከው፡የደብዳቤው፡ቃል፡ ይህ፡ነው።
2ይህም፡የኾነው፡ንጉሡ፡ኢኮንያን፣እናቱም፡እቴጌዪቱ፣ጃን፡ደረባዎቹም፣የይሁዳና፡የኢየሩሳሌምም፡ አለቃዎች፣ጠራቢዎችና፡ብረት፡ሠራተኛዎችም፡ከኢየሩሳሌም፡ከወጡ፡በዃላ፡ነው።
3ኤርምያስ፡የይሁዳ፡ንጉሥ፡ሴዴቅያስ፡ወደ፡ባቢሎን፡ንጉሥ፡ወደ፡ናቡከደነጾር፡ወደ፡ባቢሎን፡በላካቸው፡ በሳፋን፡ልጅ፡በኤልዓሣና፡በኬልቅያስ፡ልጅ፡በገማርያ፡እጅ፡ደብዳቤውን፡እንዲህ፡ሲል፡ላከው።
4የእስራኤል፡አምላክ፡የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡ከኢየሩሳሌም፡ወደ፡ባቢሎን፡ላስማረክዃቸው፡ ምርኮኛዎች፡ዅሉ፡እንዲህ፡ይላል፦
5ቤት፡ሠርታችኹ፡ተቀመጡ፥አታክልትም፡ተክላችኹ፡ፍሬዋን፡ብሉ፤
6ተጋቡ፡ወንዶችና፡ሴቶች፡ልጆችንም፡ውለዱ፤ወንዶችና፡ሴቶች፡ልጆቻችኹንም፡አጋቡ፥እነርሱም፡ ወንዶችንና፡ሴቶችን፡ልጆች፡ይውለዱ፤ከዚያም፡ተባዙ፡ጥቂቶችም፡አትኹኑ።
7በርሷ፡ሰላም፡ሰላም፡ይኾንላችዃልና፥ወደ፡ርሷ፡ላስማርክዃችኹ፡ከተማ፡ሰላምን፡ፈልጉ፥ስለ፡ርሷም፡ ወደ፡እግዚአብሔር፡ጸልዩ።
8የእስራኤልም፡አምላክ፡የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላልና፦በመካከላችኹ፡ያሉት፡ ነቢያታችኹና፡ሟርተኛዎቻችኹ፡አያታሏ፟ችኹ፥እናንተም፡የምታልሙትን፡ሕልም፡አትስሙ።
9በስሜ፡ሐሰተኛ፡ትንቢትን፡ይናገሩላችዃልና፤እኔም፡አላ፟ክዃቸውም።
10እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላልና፦ሰባው፡ዓመት፡በባቢሎን፡በተፈጸመ፡ጊዜ፡እጐበኛችዃለኹ፥ወደዚህም፡ ስፍራ፡እመልሳችኹ፡ዘንድ፡መልካሚቱን፡ቃሌን፡እፈጽምላችዃለኹ።
11ለእናንተ፡የማስባትን፡ዐሳብ፡እኔ፡ዐውቃለኹ፤ፍጻሜና፡ተስፋ፡እሰጣችኹ፡ዘንድ፡የሰላም፡ዐሳብ፡ነው፡ እንጂ፡የክፉ፡ነገር፡አይደለም።
12እናንተም፡ትጠሩኛላችኹ፥ኼዳችኹም፡ወደ፡እኔ፡ትጸልያላችኹ፥እኔም፡እሰማችዃለኹ።
13እናንተ፡ትሹኛላችኹ፥በፍጹም፡ልባችኹም፡ከሻችኹኝ፡ታገኙኛላችኹ።
14ከእናንተም፡ዘንድ፡እገኛለኹ፥ይላል፡እግዚአብሔር፥ምርኳችኹንም፡እመልሳለኹ፥ከአሕዛብም፡ዅሉ፡ ዘንድ፡እናንተንም፡ካሳደድኹበት፡ስፍራ፡ዅሉ፡እሰበስባችዃለኹ፥ይላል፡እግዚአብሔር፤እናንተንም፡ለምርኮ፡ ወዳፈለስኹበት፡ስፍራ፡እመልሳችዃለኹ። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org
15እናንተም፦እግዚአብሔር፡በባቢሎን፡ነቢያትን፡አስነሥቶልናል፡ብላችዃልና፤
16እግዚአብሔር፡በዳዊት፡ዙፋን፡ስለተቀመጠ፡ንጉሥ፡ከእናንተም፡ጋራ፡ስላልተማረኩት፡ ወንድሞቻችኹ፥በዚች፡ከተማ፡ስለሚኖሩ፡ሕዝብ፡ዅሉ፥እንዲህ፡ይላልና፦
17የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦እንሆ፥ሰይፍንና፡ራብን፡ቸነፈርንም፡ እሰድ፟ባቸዋለኹ፥ከክፋቱም፡የተነሣ፡ይበላ፡ዘንድ፡እንደማይቻል፡እንደ፡ክፉ፡በለስ፡አደርጋቸዋለኹ።
18በሰይፍም፡በራብም፡በቸነፈርም፡አሳዳድዳቸዋለኹ፥ባሳደድኹባቸውም፡አሕዛብ፡ዅሉ፡ዘንድ፡ለጥላቻና፡ ለመደነቂያ፡ለማፏጫም፡ለመሰደቢያም፡እንዲኾኑ፡በምድር፡መንግሥታት፡ዅሉ፡ዘንድ፡ለመበተን፡አሳልፌ፡ እሰጣቸዋለኹ።
19ይህም፡የኾነው፡ቃሌን፡ስላልሰሙ፡ነው፥ይላል፡እግዚአብሔር፤በማለዳ፡ተነሥቼ፡ባሪያዎቼን፡ነቢያትን፡ ወደ፡እነርሱ፡ሰድጃለኹና፤እናንተ፡ግን፡አልሰማችኹም፥ይላል፡እግዚአብሔር።
20ስለዚህ፥ከኢየሩሳሌም፡ወደ፡ባቢሎን፡የሰደድዃችኹ፡ምርኮኛዎች፡ዅሉ፡ሆይ፥የእግዚአብሔርን፡ቃል፡ ስሙ።
21የእስራኤል፡አምላክ፡የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡በስሜ፡ሐሰተኛ፡ትንቢትን፡ስለሚናገሩላችኹ፡ስለቆላያ፡ ልጅ፡ስለ፡አክአብና፡ስለመዕሴያ፡ልጅ፡ስለ፡ሴዴቅያስ፡እንዲህ፡ይላል፦እንሆ፥በባቢሎን፡ንጉሥ፡ በናቡከደነጾር፡እጅ፡አሳልፌ፡እሰጣቸዋለኹ፥በዐይኖቻችኹም፡ፊት፡ይገድላቸዋል።
22ከነርሱም፡የተነሣ፡በባቢሎን፡ያሉ፡የይሁዳ፡ምርኮኛዎች፡ዅሉ፦የባቢሎን፡ንጉሥ፡በእሳት፡እንደ፡ ጠበሳቸው፡እንደ፡ሴዴቅያስና፡እንደ፡አክአብ፡እግዚአብሔር፡ያድርግኽ፡የምትባል፡ርግማንን፡ያነሣሉ፤እኔም፡ ዐውቃለኹ፡ምስክርም፡ነኝ፥ይላል፡እግዚአብሔር።
23በእስራኤል፡ዘንድ፡ስንፍና፡አድርገዋልና፥ከባልንጀራዎቻቸውም፡ሚስቶች፡ጋራ፡ አመንዝረዋልና፥ያላዘዝዃቸውንም፡ቃል፡በስሜ፡በሐሰት፡ተናግረዋልና።
24ለኔሔላማዊው፡ለሸማያ፡እንዲህ፡በል፦
25የእስራኤል፡አምላክ፡የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦በኢየሩሳሌም፡ወዳለው፡ሕዝብ፡ ዅሉ፥ወደ፡ካህኑም፡ወደመዕሴያ፡ልጅ፡ወደ፡ሶፎንያስ፥ወደ፡ካህናቱም፡ዅሉ፡ደብዳቤዎችን፡በስምኽ፡ እንዲህ፡ስትል፡ልከኻል።
26እያበደ፡ትንቢት፡የሚናገርን፡ሰው፡ዅሉ፡በእግር፡ግንድና፡በዛንጅር፡ታኖረው፡ዘንድ፡በእግዚአብሔር፡ ቤት፡አለቃ፡እንድትኾን፡እግዚአብሔር፡በካህኑ፡በዮዳዔ፡ፋንታ፡ካህን፡አድርጎኻል።
27አኹንስ፡ትንቢት፡ተናጋሪውን፡የዓናቶቱን፡ሰው፡ኤርምያስን፡ስለ፡ምን፡አትዘልፈውም፧
28ርሱ፦ምርኮው፡የረዘመው፡ነውና፥ቤት፡ሠርታችኹ፡ተቀመጡ፥አታክልትንም፡ተክላችኹ፡ፍሬዋን፡ ብሉ፡ብሎ፡ወደ፡እኛ፡ወደ፡ባቢሎን፡ልኳልና።
29ካህኑም፡ሶፎንያስ፡ይህን፡ደብዳቤ፡በነቢዩ፡በኤርምያስ፡ዦሮ፡አነበበው።
30የእግዚአብሔርም፡ቃል፡ወደ፡ኤርምያስ፡እንዲህ፡ሲል፡መጣ፦
31እግዚአብሔር፡ስለ፡ኔሔላማዊው፡ስለ፡ሸማያ፡እንዲህ፡ይላል፡ብለኽ፡ወደ፡ምርኮኛዎች፡ዅሉ፡ላክ።እኔ፡ ሳል፟ከው፡ሸማያ፡ትንቢት፡ተናግሮላችዃልና፥በሐሰትም፡እንድትታመኑ፡አድርጓችዃልና፤
32ስለዚህ፥እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦እንሆ፥ኔሔላማዊውን፡ሸማያንና፡ዘሩን፡እቀጣለኹ፤እኔም፡ የማደርግላችኹን፡መልካሙን፡ነገር፡የሚያይ፡ሰው፡በመካከላችኹ፡አይኖርላችኹም፡