1ከእግዚአብሔር፡ዘንድ፡ወደ፡ኤርምያስ፡የመጣው፡ቃል፡ይህ፡ነው፦ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org
2የእስራኤል፡አምላክ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦የነገርኹኽን፡ቃል፡ዅሉ፡በመጽሐፍ፡ጻፍ።
3እንሆ፥የሕዝቤን፡የእስራኤልንና፡የይሁዳን፡ምርኮ፡የምመልስባት፡ዘመን፡ይመጣልና፥ይላል፡ እግዚአብሔር፤ለአባቶቻቸውም፡ወደሰጠዃት፡ምድር፡እመልሳቸዋለኹ፥እነርሱም፡ይገዟታል።
4እግዚአብሔር፡ስለ፡እስራኤልና፡ስለ፡ይሁዳ፡የተናገረው፡ቃል፡ይህ፡ነው፦
5እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላልና፦የሚያስፈራ፡ድምፅ፡ሰምተናል፤የፍርሀት፡ነው፡እንጂ፡የሰላም፡አይደለም።
6ጠይቁ፥ወንድ፡ይወልድ፡እንደ፡ኾነ፡ተመልከቱ፤ስለ፡ምን፡ሰው፡ዅሉ፡እንደ፡ወላድ፡እጁን፡በወገቡ፡ ላይ፡አድርጎ፡ፊቱም፡ዅሉ፡ወደ፡ጥቍረት፡ተለውጦ፡አየኹ፧
7ወዮ! ያ፡ቀን፡ታላቅ፡ነውና፥ርሱንም፡የሚመስል፡የለምና፤ያ፡የያዕቆብ፡መከራ፡ዘመን፡ነው፥ነገር፡ ግን፥ከርሱ፡ይድናል።
8በዚያ፡ቀን፡እንዲህ፡ይኾናል፥ይላል፡የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፤ቀንበርን፡ከዐንገትኽ፡ እሰብራለኹ፥እስራትኽንም፡እበጥሳለኹ፥ከእንግዲህ፡ወዲህም፡ለሌላ፡አትገዛም፤
9ለአምላካቸው፡ለእግዚአብሔርም፡ለማስነሣላቸው፡ለንጉሣቸው፡ለዳዊትም፡ይገዛሉ፡እንጂ፡ሌላዎች፡አሕዛብ፡ እንደ፡ገና፡አይገዟቸውም።
10እንሆ፥አንተን፡ከሩቅ፡ዘርኽንም፡ከምርኮ፡አገር፡አድናለኹና፡ባሪያዬ፡ያዕቆብ፡ሆይ፥አትፍራ፥ይላል፡ እግዚአብሔር፥አንተም፡እስራኤል፡ሆይ፥አትደንግጥ፤ያዕቆብም፡ይመለሳል፡ያርፍማል፡ተዘልሎም፡ ይቀመጣል፤ማንም፡አያስፈራውም።
11አድንኽ፡ዘንድ፡ከአንተ፡ጋራ፡ነኝና፥ይላል፡እግዚአብሔር፤አንተንም፡የበተንኹባቸውን፡አሕዛብን፡ዅሉ፡ ፈጽሜ፡አጠፋለኹ፥አንተን፡ግን፡ፈጽሜ፡አላጠፋኽም፤በመጠን፡እቀጣኻለኹ፥ያለቅጣትም፡ከቶ፡ አልተውኽም።
12እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ስብራትኽ፡የማይፈወስ፡ቍስልኽም፡ክፉ፡ነው።
13ትጠገን፡ዘንድ፡ክርክርኽን፡የሚፈርድልኽ፡የለም፥ቍስልኽንም፡የሚፈውስ፡መድኀኒት፡የለኽም።
14ውሽማዎችኽ፡ዅሉ፡ረስተውኻል፡አይፈልጉኽምም፤በደልኽ፡ታላቅ፡ስለ፡ኾነ፥ኀጢአትኽም፡ስለ፡ በዛ፥በጠላት፡ማቍሰልና፡በጨካኝ፡ቅጣት፡አቍስዬኻለኹና።
15ሕመምኽ፡የማይፈወስ፡ኾኗልና፥ስለ፡ስብራትኽ፡ለምን፡ትጮኻለኽ፧በደልኽ፡ታላቅ፡ስለ፡ኾነ፡ ኀጢአትኽም፡ስለ፡በዛ፥ይህን፡አድርጌብኻለኹ።
16ስለዚህ፥የሚውጡኽ፡ዅሉ፡ይዋጣሉ፥ጠላቶችኽም፡ዅላቸው፡ይማረካሉ፤የዘረፉኽም፡ ይዘረፋሉ፥የበዘበዙኽንም፡ዅሉ፡ለመበዝበዝ፡አሳልፌ፡እሰጣለኹ።
17እኔ፡ጤናኽን፡እመልስልኻለኹ፡ቍስልኽንም፡እፈውሳለኹ፥ይላል፡እግዚአብሔር፤ማንም፡ የማይሻት፥የተጣለች፡ጽዮን፡ብለው፡ጠርተውሻልና።
18እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦እንሆ፥የያዕቆብን፡ድንኳን፡ምርኮ፡እመልሳለኹ፥ለማደሪያውም፡ እራራለኹ፤ከተማዪቱም፡በጕብታዋ፡ላይ፡ትሠራለች፥አዳራሹም፡እንደ፡ዱሮው፡የሰው፡መኖሪያ፡ይኾናል።
19ከርሱም፡ዘንድ፡የምስጋናና፡የዘፋኞች፡ድምፅ፡ይወጣል፤እኔም፡አበዛቸዋለኹ፡አያንሱምም፥እኔም፡ አከብራቸዋለኹ፡ታናሽም፡አይኾኑም።
20ልጆቻቸውም፡እንደ፡ቀድሞ፡ይኾናሉ፥ማኅበራቸውም፡በፊቴ፡ጸንቶ፡ይኖራል፤የሚያስጨንቋቸውንም፡ ዅሉ፡እቀጣለኹ።
21አለቃቸው፡ከነርሱ፡ውስጥ፡ይኾናል፥ገዣቸውም፡ከመካከላቸው፡ይወጣል፤እኔ፡አቀርበዋለኹ፡ርሱም፡ ይቀርባል፤ይህስ፡ባይኾን፡ወደ፡እኔ፡ለመቅረብ፡የሚደፍር፡ማን፡ነው፧ይላል፡እግዚአብሔር።
22እናንተም፡ሕዝብ፡ትኾኑኛላችኹ፡እኔም፡አምላክ፡እኾናችዃለኹ። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org
23እንሆ፥የእግዚአብሔር፡ዐውሎ፡ነፋስ፥ርሱም፡ቍጣው፥የሚያገለባብጥ፡ዐውሎ፡ነፋስ፡ ወጥቷል፤የዐመፀኛዎችንም፡ራስ፡ይገለባብጣል።
24የእግዚአብሔር፡ጽኑ፡ቍጣ፡የልቡን፡ዐሳብ፡ሠርቶ፡እስኪፈጽም፡ድረስ፡አይመለስም፡በዃለኛው፡ዘመን፡ ታስተውሉታላችኹ።