Skip to content
← Jeremiah

Chapter 31 · Amharic

Jeremiah

1በዚያን፡ዘመን፥ይላል፡እግዚአብሔር፥ለእስራኤል፡ወገኖች፡ዅሉ፡አምላክ፡እኾናቸዋለኹ፡እነርሱም፡ ሕዝብ፡ይኾኑኛል።

2እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦እስራኤል፡ማረፊያ፡ሊሻ፡በኼደ፡ጊዜ፡ከሰይፍ፡የተረፈው፡ሕዝብ፡ በምድረ፡በዳ፡ሞገስ፡አገኘ።

3እግዚአብሔርም፡ከሩቅ፡ተገለጠልኝ፡እንዲህም፡አለኝ፦በዘለዓለም፡ፍቅር፡ ወድጄሻለኹ፤ስለዚህ፥በቸርነት፡ሳብኹሽ።

4የእስራኤል፡ድንግል፡ሆይ፥እንደ፡ገና፡እሠራሻለኹ፡አንቺም፡ትሠሪያለሽ፤እንደ፡ገናም፡ከበሮሽን፡ አንሥተሽ፡ከዘፋኞች፡ጋራ፡ወደ፡ዘፈን፡ትወጫለሽ።

5እንደ፡ገናም፡በሰማርያ፡ተራራዎች፡ላይ፡የወይን፡ቦታዎችን፡ትተክሊያለሽ፤አትክልተኛዎች፡ይተክላሉ፡ በፍሬውም፡ደስ፡ይላቸዋል።

6በኤፍሬምም፡ተራራዎች፡ላይ፡ያሉ፡ጠባቂዎች፦ተነሡ፥ወደ፡ጽዮን፡ወደ፡አምላካችን፡ወደ፡ እግዚአብሔር፡እንውጣ፡ብለው፡የሚጮኹበት፡ቀን፡ይመጣልና።

7እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላልና፦ስለ፡ያዕቆብ፡ደስ፡ይበላችኹ፡ስለ፡አሕዛብም፡አለቃዎች፡እልል፡ በሉ፤አውሩ፥አመስግኑ።እግዚአብሔር፡ሕዝቡን፡የእስራኤልን፡ቅሬታ፡አድኗል፡በሉ።

8እንሆ፥ከሰሜን፡አገር፡አመጣቸዋለኹ፥ከምድርም፡ዳርቻ፡እሰበስባቸዋለኹ፥በመካከላቸውም፡ዕውሩና፡ ዐንካሳው፡ያረገዘችና፡የወለደችም፡በአንድነት፤ታላቅ፡ጉባኤ፡ኾነው፡ወደዚህ፡ይመለሳሉ።

9በልቅሶ፡ወጡ፡እኔም፡በማጽናናት፡አመጣቸዋለኹ፤በወንዝ፡ዳር፡በቅን፡መንገድ፡ አስኬዳቸዋለኹ፥በርሱም፡አይሰናከሉም፤እኔ፡ለእስራኤል፡አባት፡ነኝና፥ኤፍሬምም፡በኵሬ፡ነውና።

10አሕዛብ፡ሆይ፥የእግዚአብሔርን፡ቃል፡ስሙ፥በሩቅም፡ላሉ፡ደሴቶች፡አውሩና፦እስራኤልን፡የበተነ፡ርሱ፡ ይሰበስበዋል፥እረኛም፡መንጋውን፡እንደሚጠብቅ፡ይጠብቀዋል፡በሉ።

11እግዚአብሔር፡ያዕቆብን፡ተቤዥቶታል፥ከበረቱበትም፡እጅ፡አድኖታል።

12ይመጣሉ፡በጽዮንም፡ተራራ፡እልል፡ይላሉ፤ወደእግዚአብሔርም፡በጎነት፥ወደ፡እኽልና፡ወደ፡ወይን፡ ጠጅ፡ወደ፡ዘይትም፥ወደ፡በጎችና፡ወደ፡ላሞች፡ይሰበሰባሉ፤ነፍሳቸውም፡እንደ፡ረካች፡ገነት፡ ትኾናለች፥ከእንግዲህም፡ወዲህ፡አያዝኑም።

13በዚያን፡ጊዜም፡ድንግሊቱ፡በዘፈን፡ደስ፡ይላታል፥ጐበዛዝቱና፡ሽማግሌዎቹም፡ባንድ፡ላይ፡ደስ፡ ይላቸዋል፤ልቅሷቸውንም፡ወደ፡ደስታ፡እመልሳለኹ፥አጽናናቸውማለኹ፥ከሐዘናቸውም፡ደስ፡አሠኛቸዋለኹ።

14የካህናቱንም፡ነፍስ፡በብዛት፡አረካታለኹ፡ሕዝቤም፡በጎነቴን፡ይጠግባል።

15እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦የዋይታና፡የመራራ፡ልቅሶ፡ድምፅ፡በራማ፡ተሰማ፤ራሔል፡ስለ፡ልጆቿ፡ አለቀሰች፤የሉምና፡ስለ፡ልጆቿ፡መጽናናትን፡እንቢ፡አለች።

16እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ድምፅሽን፡ከልቅሶ፡ዐይንሽንም፡ከእንባ፡ከልክዪ፤ለሥራሽ፡ዋጋ፡ ይኾናልና፥ከጠላትም፡ምድር፡ይመለሳሉ።

17ለፍጻሜሽም፡ተስፋ፡አለ፥ይላል፡እግዚአብሔር፥ልጆችሽም፡ወደ፡ዳርቻቸው፡ይመለሳሉ። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org

18ኤፍሬም፦ቀጣኸኝ፡እኔም፡እንዳልተገራ፡ወይፈን፡ተቀጣኹ፤አንተ፡እግዚአብሔር፡አምላኬ፡ ነኽና፥መልሰኝ፡እኔም፡እመለሳለኹ።

19ከተመለስኹ፡በዃላ፡ተጸጸትኹ፥ከተገሠጽኹም፡በዃላ፡ጭኔን፡ጸፋኹ፤የብላቴንነቴንም፡ስድብ፡ ተሸክሜያለኹና፡ዐፈርኹ፥ተዋረድኹም፡ብሎ፡ሲያለቅስ፡ሰማኹ።

20በእውነት፡ኤፍሬም፡ለእኔ፡የከበረ፡ልጅ፡ነውን፧ወይስ፡የተወደደ፡ሕፃን፡ነውን፧በርሱ፡ላይ፡በተናገርኹ፡ ቍጥር፡ዐስበዋለኹ፤ስለዚህ፥አንዠቴ፡ታወከችለት፥ርኅራኄም፡እራራለታለኹ፥ይላል፡እግዚአብሔር።

21ለራስሽ፡የመንገድ፡ምልክት፡አድርጊ፥መንገድንም፡የሚመሩ፡ዐምዶችን፡ትከዪ፥ልብሽንም፡ ወደኼድሽበት፡መንገድ፡ወደ፡ጥርጊያው፡አቅኚ፤አንቺ፡የእስራኤል፡ድንግል፡ሆይ፥ተመለሺ፥ወደ፡እነዚህም፡ ወደ፡ከተማዎችሽ፡ተመለሺ።

22አንቺ፡ከዳ፟ተኛ፡ልጅ፡ሆይ፥እስከ፡መቼ፡ትቅበዘበዣለሽ፧እግዚአብሔር፡በምድር፡ላይ፡ዐዲስ፡ነገርን፡ ፈጥሯልና፥ሴት፡ወንድን፡ትከባ፟ለች።

23የእስራኤል፡አምላክ፣የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ምርኳቸውን፡በመለስኹ፡ጊዜ፡ በይሁዳ፡አገር፡በከተማዎቿ።የጽድቅ፡ማደሪያ፡ሆይ፥የቅድስና፡ተራራ፡ሆይ፥እግዚአብሔር፡ይባርክኽ፡የሚልን፡ ነገር፡እንደ፡ገና፡ይናገራሉ።

24በይሁዳ፡ከተማዎችና፡በአገሩ፡ዅሉ፡ከገበሬዎችና፡መንጋን፡ይዘው፡ከሚዞሩ፡ጋራ፡የሚኖሩ፡ሰዎች፡ ይገኛሉ።

25የደከመችውን፡ነፍስ፡አርክቻለኹና፥ያዘነችውንም፡ነፍስ፡ዅሉ፡አጥግቤያለኹና።

26ከዚህም፡በዃላ፡ነቃኹ፡ተመለከትኹም፥እንቅልፌም፡ጣፋጭ፡ኾነልኝ።

27የእስራኤልን፡ቤትና፡የይሁዳን፡ቤት፡በሰው፡ዘርና፡በእንስሳ፡ዘር፡የምዘራበት፡ ዘመን፥እንሆ፥ይመጣል፥ይላል፡እግዚአብሔር።

28እንዲህም፡ይኾናል፤አፈርሳቸውና፡ክፉ፡አድርግባቸው፡ዘንድ፡እንደ፡ተጋኹባቸው፥እንዲሁ፡እሠራቸውና፡ እተክላቸው፡ዘንድ፡እተጋለኹ፥ይላል፡እግዚአብሔር።

29በዚያ፡ዘመን፡ሰው፡ዳግመኛ፡እንዲህ፡አይልም፦አባቶች፡ጨርቋ፡የወይን፡ፍሬ፡በሉ፥የልጆችም፡ ጥርሶች፡ጠረሱ፤

30ነገር፡ግን፥ሰው፡ዅሉ፡በገዛ፡በደሉ፡ይሞታል፤መራራውን፡የወይን፡ፍሬ፡የሚበላ፡ዅሉ፡ጥርሶቹ፡ ይጠርሳሉ።

31እንሆ፥ከእስራኤል፡ቤትና፡ከይሁዳ፡ቤት፡ጋራ፡ዐዲስ፡ቃል፡ኪዳን፡የምገባበት፡ወራት፡ይመጣል፥ይላል፡ እግዚአብሔር፤

32ከግብጽ፡አገር፡አወጣቸው፡ዘንድ፡እጃቸውን፡በያዝኹበት፡ቀን፡ከአባቶቻቸው፡ጋራ፡እንደ፡ገባኹት፡ ያለ፡ቃል፡ኪዳን፡አይደለም፤እነርሱ፡በኪዳኔ፡አልጸኑምና፥እኔም፡ቸል፡አልዃቸው፥ይላል፡እግዚአብሔር።

33ከነዚያ፡ወራት፡በዃላ፡ከእስራኤል፡ቤት፡ጋራ፡የምገባው፡ቃል፡ኪዳን፡ይህ፡ነውና፥ይላል፡ እግዚአብሔር፤ሕጌን፡በልቡናቸው፡አኖራለኹ፥በልባቸውም፡እጽፈዋለኹ፤እኔም፡አምላክ፡እኾናቸዋለኹ፡ እነርሱም፡ሕዝብ፡ይኾኑኛል።

34እያንዳንዱ፡ሰው፡ባልንጀራውን፥እያንዳንዱም፡ወንድሙን፦እግዚአብሔርን፡ዕወቅ፡ብሎ፡ አያስተምርም፤ከታናሹ፡ዠምሮ፡እስከ፡ታላቁ፡ድረስ፡ዅሉ፡ያውቁኛልና፥ይላል፡እግዚአብሔር።በደላቸውን፡ እምራቸዋለኹና፥ኀጢአታቸውንም፡ከእንግዲህ፡ወዲህ፡አላስብምና።

35ስሙ፡የሰራዊት፡ጌታ፡የሚባል፥ፀሓይን፡በቀን፡የጨረቃንና፡የከዋክብትን፡ሥርዐት፡በሌሊት፡ብርሃን፡ አድርጎ፡የሚሰጥ፥እንዲተሙ፟ም፡የባሕርን፡ሞገዶች፡የሚያናውጥ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org

36ይህ፡ሕግ፡ከፊቴ፡ቢወገድ፥ይላል፡እግዚአብሔር፥በዚያን፡ጊዜ፡ደግሞ፡የእስራኤል፡ዘር፡በፊቴ፡ሕዝብ፡ እንዳይኾን፡ለዘለዓለም፡ይቀራል።

37እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ሰማይ፡በላይ፡ቢከነዳ፥የምድርም፡መሠረት፡በታች፡ቢመረመር፥በዚያን፡ ጊዜ፡ስላደረጉት፡ነገር፡ዅሉ፡የእስራኤልን፡ዘር፡ዅሉ፡እጥላለኹ፥ይላል፡እግዚአብሔር።

38ከሐናንኤል፡ግንብ፡ዠምሮ፡እስከማእዘኑ፡በር፡ድረስ፡ከተማ፡ለእግዚአብሔር፡የሚሠራበት፡ ዘመን፥እንሆ፥ይመጣል፥ይላል፡እግዚአብሔር።

39የተለካበትም፡ገመድ፡ወደጋሬብ፡ኰረብታ፡በቀጥታ፡ወደ፡ፊት፡ይኼዳል፥ወደ፡ጎዓም፡ይዞራል።

40የሬሳም፡ሸለቆ፡ዅሉ፡የዐመድም፡ዕርሻ፡ዅሉ፡እስከቄድሮን፡ወንዝ፡ድረስ፡በምሥራቅ፡በኩል፡እስካለው፡ እስከፈረስ፡በር፡ማእዘን፡ድረስ፡ለእግዚአብሔር፡የተቀደሰ፡ይኾናል፤ከእንግዲህም፡ወዲህ፡ለዘለዓለም፡ አይነቀልም፡አይፈርስምም።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source