1በይሁዳ፡ንጉሥ፡በሴዴቅያስ፡በዐሥረኛው፡ዓመት፥በናቡከደነጾር፡በዐሥራ፡ስምንተኛው፡ ዓመት፥ከእግዚአብሔር፡ዘንድ፡ወደ፡ኤርምያስ፡የመጣው፡ቃል፡ይህ፡ነው።
2በዚያን፡ጊዜም፡የባቢሎን፡ንጉሥ፡ሰራዊት፡ኢየሩሳሌምን፡ከቦ፟፡ነበር፤ነቢዩም፡ኤርምያስ፡በይሁዳ፡ንጉሥ፡ ቤት፡በነበረው፡በግዞት፡ቤት፡አደባባይ፡ታስሮ፡ነበር።
3የይሁዳ፡ንጉሥ፡ሴዴቅያስ፡እንዲህ፡ብሎ፡አስጠብቆት፡ነበርና፦ስለ፡ምን፡እንዲህ፡ብለኽ፡ትንቢት፡ ትናገራለኽ፦እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦እንሆ፥ይህችን፡ከተማ፡ለባቢሎን፡ንጉሥ፡እጅ፡አሳልፌ፡ እሰጣለኹ፡ርሱም፡ይይዛታል፤
4የይሁዳም፡ንጉሥ፡ሴዴቅያስ፡በእውነት፡በባቢሎን፡ንጉሥ፡እጅ፡ዐልፎ፡ይሰጣል፥አፍ፡ለአፍም፡ ይናገረዋል፥ዐይኑም፡ዐይኑን፡ያያል፡እንጂ፡ከከለዳውያን፡እጅ፡አያመልጥም፤
5ርሱም፡ሴዴቅያስን፡ወደ፡ባቢሎን፡ያፈልሰዋል፥እኔም፡እስክጐበኘው፡ድረስ፡በዚያ፡ይኖራል፥ይላል፡ እግዚአብሔር፤ከከለዳውያን፡ጋራ፡ብትዋጉ፡ምንም፡አትረቡም።
6ኤርምያስም፡እንዲህ፡አለ፦የእግዚአብሔር፡ቃል፡ወደ፡እኔ፡እንዲህ፡ሲል፡መጣ፦
7እንሆ፥የአጎትኽ፡የሰሎም፡ልጅ፡ዐናምኤል፡ወዳንተ፡መጥቶ፦ትገዛው፡ዘንድ፡መቤዠቱ፡የአንተ፡ ነውና፥በዐናቶት፡ያለውን፡ዕርሻዬን፡ግዛ፡ይልኻል።
8እንደእግዚአብሔርም፡ቃል፡የአጎቴ፡ልጅ፡ዐናምኤል፡እኔ፡ወዳለኹበት፡ወደግዞቱ፡ቤት፡አደባባይ፡ መጥቶ፦በብንያም፡አገር፡በዐናቶት፡ያለውን፡ዕርሻዬን፥እባክኽ፥ግዛ፤ርስቱ፡የአንተ፡ነውና፥መቤዠቱም፡ የአንተ፡ነውና፤ለአንተ፡ግዛው፡አለኝ።ይህም፡የእግዚአብሔር፡ቃል፡እንደ፡ኾነ፡ዐወቅኹ።
9በዐናቶትም፡ያለውን፡ዕርሻ፡ከአጎቴ፡ልጅ፡ከዐናምኤል፡ገዛኹ፥ዐሥራ፡ሰባት፡ሰቅል፡ብርም፡መዘንኹለት።
10በውሉም፡ወረቀት፡ላይ፡ፈረምኹ፡ዐተምኹትም፥ምስክሮችንም፡ጠርቼ፡ብሩን፡በሚዛን፡መዘንኹለት።
11የታተመውንና፡የተከፈተውን፡የውል፡ወረቀት፡ወሰድኹ፤
12የአጎቴም፡ልጅ፡ዐናምኤል፥የውሉንም፡ወረቀት፡የፈረሙ፡ምስክሮች፥በግዞትም፡ቤት፡አደባባይ፡ የተቀመጡ፡አይሁድ፡ዅሉ፡እያዩ፡የውሉን፡ወረቀት፡ለመሕሤያ፡ልጅ፡ለኔርያ፡ልጅ፡ለባሮክ፡ሰጠኹት።
13በፊታቸውም፡እንዲህ፡ብዬ፡ባሮክን፡አዘዝኹት፦
14የእስራኤል፡አምላክ፡የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ብዙ፡ቀን፡ይጠበቁ፡ዘንድ፡ የታተመውንና፡የተከፈተውን፡ይህን፡የውል፡ወረቀት፡ወስደኽ፡በሸክላ፡ዕቃ፡ውስጥ፡አኑራቸው። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org
15የእስራኤል፡አምላክ፡የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላልና፦ሰዎች፡በዚች፡ምድር፡ቤትንና፡ ዕርሻን፡የወይን፡ቦታንም፡እንደ፡ገና፡ይገዛሉ።
16ለኔርያ፡ልጅ፡ለባሮክም፡የውሉን፡ወረቀት፡ከሰጠኹት፡በዃላ፥እንዲህ፡ብዬ፡ወደ፡እግዚአብሔር፡ ጸለይኹ።
17አቤቱ፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡ሆይ፥እንሆ፥አንተ፡ሰማይንና፡ምድርን፡በታላቅ፡ኀይልኽና፡በተዘረጋች፡ ክንድኽ፡ፈጥረኻል፥ከአንተም፡የሚያቅት፡ነገር፡የለም።
18ለብዙ፡ሺሕ፡ምሕረት፡ታደርጋለኽ፥የአባቶችንም፡በደል፡ከነርሱ፡በዃላ፡በልጆቻቸው፡ብብት፡ ትመልሳለኽ፤ስምኽ፡ታላቅና፡ኀያል፡አምላክ፡የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡ነው።
19በምክር፡ታላቅ፡በሥራም፡ብርቱ፡ነኽ፤ለዅሉም፡እንደ፡መንገዱና፡እንደ፡ሥራው፡ፍሬ፡ትሰጥ፡ዘንድ፡ ዐይኖችኽ፡በአዳም፡ልጆች፡መንገድ፡ዅሉ፡ተገልጠዋል።
20እስከ፡ዛሬም፡ድረስ፡ምልክትንና፡ድንቅን፡ነገር፡በግብጽ፡ምድር፡ደግሞም፡በእስራኤልና፡በሌላዎች፡ ሰዎች፡መካከል፡አድርገኻል፥እንደ፡ዛሬም፡ለአንተ፡ስም፡አድርገኻል።
21በምልክትና፡በድንቅ፡ነገር፥በብርቱ፡እጅና፡በተዘረጋች፡ክንድ፡በታላቅም፡ግርማ፡ሕዝብኽን፡እስራኤልን፡ ከግብጽ፡ምድር፡አወጣኽ።
22ትሰጣቸውም፡ዘንድ፡ለአባቶቻቸው፡የማልኽላቸውን፡ምድር፥ወተትና፡ማርንም፡የምታፈሰ፟ውን፡ ምድር፥ሰጠኻቸው፤
23እነርሱም፡ገብተው፡ወረሷት፤ነገር፡ግን፥ቃልኽን፡አልሰሙም፥በሕግኽም፡አልኼዱም፤ያደርጉም፡ዘንድ፡ ካዘዝኻቸው፡ዅሉ፡ምንም፡አላደረጉም፤ስለዚህ፥ይህን፡ክፉ፡ነገር፡ዅሉ፡አመጣኽባቸው።
24እንሆ፥የዐፈር፡ድልድል፥ሊይዟትም፡እስከ፡ከተማዪቱ፡ድረስ፡ቀርበዋል፤ከሰይፍና፡ከራብ፡ከቸነፈርም፡ የተነሣ፡ከተማዪቱ፡ለሚዋጓት፡ለከለዳውያን፡እጅ፡ተሰጥታለች፥የተናገርኸውም፡ኾኗል፤እንሆም፥አንተ፡ ታየዋለኽ።
25አንተም፥ጌታ፡እግዚአብሔር፡ሆይ፦ዕርሻውን፡በብር፡ግዛ፡ምስክሮችንም፡ጥራ፡አልኸኝ፤ከተማዪቱ፡ ግን፡ለከለዳውያን፡እጅ፡ተሰጥታለች።
26የእግዚአብሔርም፡ቃል፡ወደ፡ኤርምያስ፡እንዲህ፡ሲል፡መጣ፦
27እንሆ፥እኔ፡የሥጋ፡ለባሽ፡ዅሉ፡አምላክ፡እግዚአብሔር፡ነኝ፤
28በእውኑ፡እኔን፡የሚያቅተኝ፡ነገር፡አለን፧ስለዚህ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦እንሆ፥ይህችን፡ ከተማ፡ለከለዳውያን፡እጅና፡ለባቢሎን፡ንጉሥ፡ለናቡከደነጾር፡እጅ፡አሳልፌ፡እሰጣለኹ፥ርሱም፡ይይዛታል።
29ይህችን፡ከተማ፡የሚወጉ፡ከለዳውያን፡መጥተው፡በእሳት፡ያነዷ፟ታል፥ያስቈጡኝም፡ዘንድ፡በሰገነታቸው፡ ላይ፡ለበዓል፡ካጠኑባቸው፥ለሌላዎችም፡አማልክት፡የመጠጥን፡ቍርባን፡ካፈሰሱባቸው፡ቤቶች፡ጋራ፡ ያቃጥሏታል።
30የእስራኤል፡ልጆችና፡የይሁዳ፡ልጆች፡ከታናሽነታቸው፡ዠምሮ፡በፊቴ፡ክፉ፡ነገርን፡ብቻ፡ አድርገዋልና፤የእስራኤልም፡ልጆች፡እኔን፡በእጃቸው፡ሥራ፡ከማስቈጣት፡በቀር፡ሌላ፡ሥራ፡አላደረጉምና።
31ከፊቴ፡አስወግዳት፡ዘንድ፡ይህች፡ከተማ፡ከሠሯት፡ቀን፡ዠምሮ፡እስከ፡ዛሬ፡ድረስ፡ቍጣዬንና፡መዓቴን፡ ለማነሣሣት፡ኾናለችና፤
32ይህም፡እኔን፡ያስቈጡኝ፡ዘንድ፥እነርሱና፡ነገሥታታቸው፡አለቃዎቻቸውም፡ካህናታቸውም፡ነቢያታቸውም፡ የይሁዳም፡ሰዎች፡በኢየሩሳሌምም፡የሚንኖሩ፥ስላደረጉት፡ስለእስራኤል፡ልጆችና፡ስለይሁዳ፡ልጆች፡ክፋት፡ዅሉ፡ ነው።
33ፊታቸውንም፡ሳይኾን፡ዠርባቸውን፡ወደ፡እኔ፡መለሱ፤እኔም፡በማለዳ፡ተነሥቼ፡ሳሰተምራቸው፡ተግሣጽን፡ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org ይቀበሉ፡ዘንድ፡አልሰሙም።
34ያረክሱትም፡ዘንድ፡ስሜ፡በተጠራበት፡ቤት፡ውስጥ፡ርኵሰታቸውን፡አኖሩ።
35ይሁዳን፡ወደ፡ኀጢአት፡እንዲያገቡት፥ይህንን፡ርኵሰት፡ያደርጉ፡ዘንድ፥እኔ፡ያላዘዝኹትንና፡በልቤ፡ ያላሰብኹትን፡ነገር፥ወንዶችና፡ሴቶች፡ልጆቻቸውን፡ለሞሎክ፡በእሳት፡ያሳልፉ፡ዘንድ፡በሄኖም፡ልጅ፡ሸለቆ፡ ውስጥ፡ያሉትን፡የበዓልን፡የኰረብታውን፡መስገጃዎች፡ሠሩ።
36አኹን፡እንግዲህ፡የእስራኤል፡አምላክ፡እግዚአብሔር፡አንተ፡ስለ፡ርሷ፦በሰይፍና፡በራብ፡በቸነፈርም፡ ለባቢሎን፡ንጉሥ፡እጅ፡ተሰጥታለች፡ስለምትላት፡ከተማ፡እንዲህ፡ይላል፦
37እንሆ፥በቍጣዬና፡በመዓቴ፡በታላቅም፡መቅሠፍቴ፡እነርሱን፡ካሳደድኹባት፡አገር፡ዅሉ፡ እሰበስባቸዋለኹ፥ወደዚህም፡ስፍራ፡እመልሳቸዋለኹ፥ተዘልለውም፡እንዲኖሩ፡አደርጋለኹ፤
38እነርሱም፡ሕዝብ፡ይኾኑኛል፡እኔም፡አምላክ፡እኾናቸዋለኹ።
39ለእነርሱም፡ከነርሱም፡በዃላ፡ለልጆቻቸው፡መልካም፡ይኾንላቸው፡ዘንድ፡ለዘለዓለም፡እንዲፈሩኝ፡አንድ፡ ልብና፡አንድ፡መንገድ፡እሰጣቸዋለኹ።
40ለእነርሱም፡ከማደርገው፡በጎነት፡አልመለስም፡ስል፥ከነርሱ፡ጋራ፡የዘለዓለምን፡ቃል፡ኪዳን፡ እገባለኹ፤ከእኔም፡ዘንድ፡ፈቀቅ፡እንዳይሉ፡መፈራቴን፡በልባቸው፡ውስጥ፡አኖራለኹ።
41ለእነርሱም፡መልካምን፡በማድረግ፡ደስ፡ይለኛል፡በእውነትም፡በፍጹም፡ልቤና፡በፍጹም፡ነፍሴ፡በዚች፡ ምድር፡እተክላቸዋለኹ።
42እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላልና፦ይህን፡እጅግ፡ክፉ፡ነገር፡ዅሉ፡በዚህ፡ሕዝብ፡ላይ፡ እንዳመጣኹ፥እንዲሁ፡የተናገርኹላቸውን፡በጎነት፡ዅሉ፡አመጣላቸዋለኹ።
43እናንተም፦ያለሰውና፡ያለእንስሳ፡ያለች፡ባድማ፡ናት፥ለከለዳውያንም፡እጅ፡ተሰጥታለች፡በምትሏት፡ ምድር፡ዕርሻን፡ይገዛሉ።
44ምርኮኛዎቻቸውንም፡እመልሳለኹና፡በብንያም፡አገር፡በኢየሩሳሌምም፡ዙሪያ፡ባሉ፡ስፍራዎች፥በይሁዳም፡ ከተማዎች፡በደጋውም፡ባሉ፡ከተማዎች፡በቈላውም፡ባሉ፡ከተማዎች፡በደቡብም፡ባሉ፡ከተማዎች፥ሰዎች፡ ዕርሻውን፡በብር፡ይገዛሉ፡በውሉም፡ወረቀት፡ፈርመው፡ያትማሉ፡ምስክሮችንም፡ይጠራሉ።