1የባቢሎን፡ንጉሥ፡ናቡከደነጾርና፡ሰራዊቱ፡ዅሉ፡ከእጁም፡ግዛት፡በታች፡ያሉ፡የምድር፡መንግሥታት፡ዅሉ፡ አሕዛብም፡ዅሉ፡ኢየሩሳሌምንና፡ከተማዎቿን፡ዅሉ፡ይወጉ፡በነበረ፡ጊዜ፥ከእግዚአብሔር፡ዘንድ፡ወደ፡ ኤርምያስ፡የመጣ፡ቃል፡ይህ፡ነው፦
2የእስራኤል፡አምላክ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ኺድ፡ለይሁዳም፡ንጉሥ፡ለሴዴቅያስ፡ተናገር፡ እንዲህም፡በለው፦እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦እንሆ፥ይህችን፡ከተማ፡በባቢሎን፡ንጉሥ፡እጅ፡አሳልፌ፡ እሰጣለኹ፥በእሳትም፡ያቃጥላታል፤
3አንተም፡በርግጥ፡ትያዛለኽ፡በእጅም፡አልፈኽ፡ትሰጣለኽ፡እንጂ፡ከእጁ፡አታመልጥም፤ዐይንኽም፡ የባቢሎንን፡ንጉሥ፡ዐይን፡ታያለች፥ርሱም፡ከአንተ፡ጋራ፡አፍ፡ለአፍ፡ይናገራል፥ወደ፡ባቢሎንም፡ትገባለኽ።
4ነገር፡ግን፥የይሁዳ፡ንጉሥ፡ሴዴቅያስ፡ሆይ፥የእግዚአብሔርን፡ቃል፡ስማ፤እግዚአብሔር፡ስለ፡አንተ፡ እንዲህ፡ይላል፦በሰይፍ፡አትሞትም፥በሰላም፡ትሞታለኽ፡እንጂ፤
5ከአንተ፡በፊት፡እንደ፡ነበሩ፡እንደ፡ዱሮ፡ነገሥታት፡እንደ፡አባቶችኽ፡መቃጠል፥እንዲሁ፡ ያቃጥሉኻልና፦ወየው! ጌታ፡ሆይ፡እያሉ፡ያለቅሱልኻል፤እኔ፡ቃልን፡ተናግሬያለኹና፥ይላል፡እግዚአብሔር። 6-
7የባቢሎንም፡ንጉሥ፡ሰራዊት፡ኢየሩሳሌምንና፡የቀሩትን፡የይሁዳን፡ከተማዎች፡ዅሉ፥ከተመሸጉት፡ ከይሁዳ፡ከተማዎች፡የተረፉትን፡ለኪሶንና፡ዓዜቃን፡በወጋ፡ጊዜ፥ነቢዩ፡ኤርምያስ፡ይህን፡ቃል፡ዅሉ፡ለይሁዳ፡ ንጉሥ፡ለሴዴቅያስ፡በኢየሩሳሌም፡ነገረው። 8-
9ሰው፡ዅሉ፡ዕብራዊ፡የኾነውን፡ወንድ፡ባሪያውንና፡ዕብራዊት፡የኾነች፡ሴት፡ባሪያውን፡ሐራነት፡ እንዲያወጣ፥አይሁዳዊ፡ወንድሙንም፡ማንም፡እንዳይገዛ፥ስለ፡ሐራነታቸው፡ዐዋጅ፡እንዲነገር፡ንጉሡ፡ ሴዴቅያስ፡በኢየሩሳሌም፡ከነበሩ፡ሕዝብ፡ዅሉ፡ጋራ፡ቃል፡ኪዳን፡ካደረገ፡በዃላ፥ከእግዚአብሔር፡ዘንድ፡ወደ፡ ኤርምያስ፡የመጣው፡ቃል፡ይህ፡ነው፦
10ሰው፡ዅሉ፡ወንድ፡ባሪያውንና፡ሴት፡ባሪያውን፡ሐራነት፡እንዲያወጣ፡ከእንግዲህ፡ወዲህም፡ማንም፡ እንዳይገዛቸው፡ወደቃል፡ኪዳኑ፡የገቡ፡አለቃዎች፡ዅሉና፡ሕዝቡ፡ዅሉ፡ሰሙ፥ሐራነትም፡አወጧቸው።
11ነገር፡ግን፥ከዚያ፡በዃላ፡ተመልሰው፡ሐራነት፡ያወጧቸውን፡ወንዶችና፡ሴቶች፡ባሪያዎቻቸውን፡ አስመለሱ፥ወንዶችና፡ሴቶች፡ባሪያዎችም፡አድርገው፡ገዟቸው።
12ስለዚህ፥የእግዚአብሔር፡ቃል፡ከእግዚአብሔር፡ዘንድ፡ወደ፡ኤርምያስ፡እንዲህ፡ሲል፡መጣ፦
13የእስራኤል፡አምላክ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦አባቶቻችኹን፡ከባርነት፡ቤት፡ከግብጽ፡አገር፡ ባወጣዃቸው፡ቀን፡ከነርሱ፡ጋራ፡እንዲህ፡ብዬ፡ቃል፡ኪዳን፡አደረግኹ።
14ሰባት፡ዓመት፡በተፈጸመ፡ጊዜ፥የተሸጠላችኹን፡ስድስትም፡ዓመት፡የተገዛላችኹን፡ዕብራዊ፡ ወንድማችኹን፡እያንዳንዳችኹ፡ሐራነት፡ታወጡታላችኹ፥እያንዳንዱም፡ያወጣዋል፤አባቶቻችኹ፡ግን፡ አልሰሙኝም፡ዦሯቸውንም፡አላዘነበሉም።
15እናንተም፡ዛሬ፡ተመልሳችኹ፡ሰው፡ዅሉ፡ባልንጀራውን፡ሐራነት፡ለማውጣት፡ዐዋጅ፡በመንገር፡ለዐይኔ፡ ደስ፡የሚያሠኝን፡ነገር፡አድርጋችኹ፡ነበር፥በስሜም፡በሚጠራበት፡ቤት፡ውስጥ፡በፊቴ፡ቃል፡ኪዳን፡ አድርጋችኹ፡ነበር።
16ነገር፡ግን፥ተመልሳችኹ፡ስሜን፡አስነቀፋችኹ፥እያንዳንዳችኹም፡በፈቃዳቸው፡እንዲኼዱ፡ሐራነት፡ ያወጣችዃቸውን፡ወንድና፡ሴት፡ባሪያዎቻችኹን፡አስመለሳችኹ፥ወንዶችና፡ሴቶች፡ባሪያዎችም፡እንዲኾኑላችኹ፡ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org ገዛችዃቸው።
17ስለዚህ፥እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ሰው፡ዅሉ፡ለወንድሙና፡ለባልንጀራው፡የሐራነት፡ዐዋጅ፡ ለመንገር፡እኔን፡አልሰማችኹም፤እንሆ፥እኔ፡ለሰይፍና፡ለቸነፈር፡ለራብም፡የሐራነት፡ዐዋጅ፡ እናገርባችዃለኹ፥ይላል፡እግዚአብሔር፤በምድርም፡መንግሥታት፡ዅሉ፡መካከል፡እንድትበተኑ፡ አደርጋችዃለኹ።
18ቃል፡ኪዳኔንም፡የተላለፉትን፡ሰዎች፥እንቦሳውንም፡ቈርጠው፡በቍራጩ፡መካከል፡ባለፉ፡ጊዜ፡በፊቴ፡ ያደረጉትን፡የቃል፡ኪዳንን፡ቃል፡ያልፈጸሙትን፥
19የይሁዳን፡አለቃዎችና፡የኢየሩሳሌምን፡አለቃዎች፡ጃን፡ደረባዎችን፡ካህናትንም፡በእንቦሳም፡ቍራጭ፡ መካከል፡ያለፉትን፡የአገሩን፡ሕዝብ፡ዅሉ፥
20ለጠላቶቻቸው፡እጅ፡ነፍሳቸውንም፡ለሚሿት፡እጅ፡አሳልፌ፡እሰጣለኹ፤ሬሳቸውም፡ለሰማይ፡ወፎችና፡ ለምድር፡አራዊት፡መብል፡ይኾናል።
21የይሁዳንም፡ንጉሥ፡ሴዴቅያስንና፡አለቃዎቹን፡ለጠላቶቻቸው፡እጅ፡ነፍሳቸውንም፡ለሚሿት፡እጅ፡ ከእናንተም፡ለተመለሱት፡ለባቢሎን፡ንጉሥ፡ሰራዊት፡እጅ፡አሳልፌ፡እሰጣለኹ።
22እንሆ፥አዛ፟ለኹ፥ይላል፡እግዚአብሔር፥ወደዚችም፡ከተማ፡እመልሳቸዋለኹ፤ርሷንም፡ይወጋሉ፡ ይይዟትማል፡በእሳትም፡ያቃጥሏታል፤የይሁዳንም፡ከተማዎች፡ሰው፡የሌለበት፡ባድማ፡አደርጋቸዋለኹ።