Skip to content
← Jeremiah

Chapter 36 · Amharic

Jeremiah

1እንዲህም፡ኾነ፤በይሁዳ፡ንጉሥ፡በኢዮስያስ፡ልጅ፡በኢዮአቄም፡በአራተኛው፡ዓመት፡ይህ፡ቃል፡ ከእግዚአብሔር፡ዘንድ፡ወደ፡ኤርምያስ፡መጣ፦

2አንድ፡የመጽሐፍ፡ክርታስ፡ውሰድ፥ለአንተም፡ከተናገርኹበት፡ቀን፡ከኢዮስያስ፡ዘመን፡ዠምሮ፡እስከ፡ዛሬ፡ ድረስ፡በእስራኤልና፡በይሁዳ፡ላይ፡በአሕዛብም፡ዅሉ፡ላይ፡የተናገርኹኽን፡ቃል፡ዅሉ፡ጻፍበት።

3ምናልባት፡የይሁዳ፡ቤት፦እኔ፡አደርግባቸዋለኹ፡ያልኹትንና፡ያሰብኹትን፡ክፉ፡ነገር፡ዅሉ፡ይሰሙ፡ ይኾናል፥ከክፉ፡መንገዳቸው፡ይመለሱ፡ዘንድ፡እኔም፡በደላቸውንና፡ኀጢአታቸውን፡ይቅር፡እል፡ዘንድ።

4ኤርምያስም፡የኔርያን፡ልጀ፡ባሮክን፡ጠራ፥ባሮክም፡እግዚአብሔር፡ለርሱ፡የተናገረውን፡ቃል፡ዅሉ፡ ከኤርምያስ፡አፍ፡በመጽሐፉ፡ክርታስ፡ጻፈ።

5ኤርምያስም፡ባሮክን፡እንዲህ፡ሲል፡አዘዘው፦እኔ፡ተግዤያለኹ፤ወደእግዚአብሔር፡ቤት፡እገባ፡ዘንድ፡ አልችልም።

6አንተ፡ግን፡ኺድ፥ከአፌም፡የጻፍኸውን፡የእግዚአብሔርን፡ቃል፡በጾም፡ቀን፡በእግዚአብሔር፡ቤት፡ በሕዝቡ፡ዦሮ፡በክርታሱ፡አንብ፟፤ደግሞም፡ከከተማዎቻቸው፡በሚወጡ፡በይሁዳ፡ሰዎች፡ዅሉ፡ዦሮ፡አንበ፟ው።

7እግዚአብሔር፡በዚህ፡ሕዝብ፡ላይ፡የተናገረው፡ቍጣውና፡መዓቱ፡ታላቅ፡ነውና፥ምናልባት፡ጸሎታቸው፡ በእግዚአብሔር፡ፊት፡ትወድቅ፡ይኾናል፥ዅሉም፡ከክፉ፡መንገዱ፡ይመለስ፡ይኾናል።

8የኔርያም፡ልጅ፡ባሮክ፡ነቢዩ፡ኤርምያስ፡ያዘዘውን፡ዅሉ፡አደረገ፥በእግዚአብሔርም፡ቤት፡የእግዚአብሔርን፡ ቃል፡በመጽሐፉ፡አነበበ።

9እንዲህም፡ኾነ፤በይሁዳ፡ንጉሥ፡በኢዮስያስ፡ልጅ፡በኢዮአቄም፡በዐምስተኛው፡ዓመት፡በዘጠነኛው፡ወር፡ በኢየሩሳሌም፡የተቀመጡ፡ሕዝብ፡ዅሉ፡ከይሁዳም፡ከተማዎች፡ወደ፡ኢየሩሳሌም፡የመጡ፡ሕዝብ፡ዅሉ፡ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org በእግዚአብሔር፡ፊት፡ለመጾም፡ዐዋጅ፡ነገሩ።

10ባሮክም፡የኤርምያስን፡ቃል፡በእግዚአብሔር፡ቤት፡በላይኛው፡አደባባይ፡በእግዚአብሔር፡ቤት፡በዐዲሱ፡ በር፡መግቢያ፡ባለው፡በጸሓፊው፡በሳፋን፡ልጅ፡በገማርያ፡ጓዳ፡በሕዝቡ፡ዅሉ፡ዦሮ፡በመጽሐፉ፡አነበበ።

11የሳፋንም፡ልጅ፡የገማርያ፡ልጅ፡ሚክያስ፡የእግዚአብሔርን፡ቃል፡ዅሉ፡ከመጽሐፉ፡በሰማ፡ጊዜ፥

12ወደንጉሡ፡ቤት፡ወደጸሓፊው፡ጓዳ፡ወረደ፤እንሆም፥አለቃዎች፡ዅሉ፥ጸሓፊው፡ኤሊሳማ፥የሸማያ፡ ልጅ፡ድላያ፥የዓክቦር፡ልጅ፡ኤልናታን፥የሳፋን፡ልጅ፡ገማርያ፥የሐናንያ፡ልጅ፡ሴዴቅያስ፡አለቃዎቹም፡ዅሉ፡ በዚያ፡ተቀምጠው፡ነበር።

13ሚክያስም፡ባሮክ፡በሕዝቡ፡ዦሮ፡በመጽሐፉ፡ባነበበ፡ጊዜ፡የሰማውን፡ቃል፡ዅሉ፡ነገራቸው።

14አለቃዎቹም፡ዅሉ፦በሕዝቡ፡ዦሮ፡ያነበብኸውን፡ክርታስ፡በእጅኽ፡ይዘኽ፡ና፡የሚል፡መልእክት፡በኵሲ፡ ልጅ፡በሰሌምያ፡ልጅ፡በናታንያ፡ልጅ፡በይሁዲ፡እጅ፡ወደ፡ባሮክ፡ላኩ።የኔርያም፡ልጅ፡ባሮክ፡ክርታሱን፡ በእጁ፡ይዞ፡ወደ፡እነርሱ፡መጣ።

15እነርሱም፦እስኪ፡ተቀመጥ፥በዦሯችንም፡አንብ፟፡አሉት።ባሮክም፡በዦሯቸው፡አነበበው።

16ቃሉንም፡ዅሉ፡በሰሙ፡ጊዜ፡ፈርተው፡ርስ፡በርሳቸው፡ተመካከሩ፥ባሮክንም፦ይህን፡ቃል፡ዅሉ፡ በርግጥ፡ለንጉሡ፡እንናገራለን፡አሉት።

17ባሮክንም፦ይህን፡ቃል፡ዅሉ፡ከአፉ፡እንዴት፡እንደ፡ጻፍኸው፡ንገረን፡ብለው፡ጠየቁት።

18ባሮክም፦ይህን፡ቃል፡ከአፉ፡ይነግረኝ፡ነበር፥እኔም፡በመጽሐፉ፡ላይ፡በቀለም፡እጽፍ፡ነበር፡ብሎ፡ መለሰላቸው።

19አለቃዎቹም፡ባሮክን፦አንተና፡ኤርምያስ፡ኺዱ፥ተሸሸጉ፥ወዴትም፡እንደ፡ኾናችኹ፡ማንም፡አይወቅ፡ አሉት።

20ወደ፡ንጉሡም፡ወደ፡አደባባይ፡ገቡ፥ክርታሱንም፡በጸሓፊው፡በኤሊሳማ፡ጓዳ፡አኑረውት፡ነበር፤ቃሉንም፡ ዅሉ፡በንጉሡ፡ዦሮ፡ተናገሩ።

21ንጉሡም፡ክርታሱን፡ያመጣ፡ዘንድ፡ይሁዲን፡ላከ፥ርሱም፡ከጸሓፊው፡ከኤሊሳማ፡ጓዳ፡ ወሰደው፤ይሁዲም፡በንጉሡና፡በንጉሡ፡አጠገብ፡በቆሙት፡አለቃዎች፡ዅሉ፡ዦሮ፡አነበበው።

22ንጉሡም፡በዘጠነኛው፡ወር፡በክረምት፡ቤት፡ተቀምጦ፡ነበር፥በፊቱም፡በምድጃ፡ውስጥ፡እሳት፡ይነድ፟፡ ነበር።

23ይሁዲም፡ሦስት፡ወይም፡አራት፡ዐምድ፡ያኽል፡ባነበበ፡ቍጥር፥ንጉሡ፡በካራ፡ቀደደው፤ክርታሱም፡ በምድጃ፡ውስጥ፡ባለው፡እሳት፡ፈጽሞ፡እስኪቃጠል፡ድረስ፡በምድጃ፡ውስጥ፡ወዳለው፡እሳት፡ጣለው።

24ንጉሡም፡ይህንም፡ቃል፡ዅሉ፡የሰሙ፡ባሪያዎቹ፡ዅሉ፡አልፈሩም፡ልብሳቸውንም፡አልቀደዱም።

25ነገር፡ግን፥ኤልናታንና፡ድላያ፡ገማርያም፡ክርታሱን፡እንዳያቃጥል፡ንጉሡን፡ለመኑት፥ርሱ፡ግን፡ አልሰማቸውም።

26ንጉሡም፡ጸሓፊውን፡ባሮክንና፡ነቢዩን፡ኤርምያስን፡ይይዙ፡ዘንድ፡የንጉሡን፡ልጅ፡ይረሕምኤልንና፡ የዓዝርኤልን፡ልጅ፡ሰራያን፡የዓብድኤልንም፡ልጅ፡ሰሌምያን፡አዘዘ፥እግዚአብሔር፡ግን፡ሰወራቸው።

27ንጉሡም፡ክርታሱንና፡ባሮክ፡ከኤርምያስ፡አፍ፡የጻፈውን፡ቃል፡ካቃጠለ፡በዃላ፡የእግዚአብሔር፡ቃል፡ ወደ፡ኤርምያስ፡እንዲህ፡ሲል፡መጣ፦

28ዳግመኛም፡ሌላ፡ክርታስ፡ውሰድ፥የይሁዳም፡ንጉሥ፡ኢዮአቄም፡ባቃጠለው፡ክርታስ፡ላይ፡የነበረውን፡ የቀድሞውን፡ቃል፡ዅሉ፡ጻፍበት።

29የይሁዳንም፡ንጉሥ፡ኢዮአቄምን፡እንዲህ፡በለው፦እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦አንተ፦የባቢሎን፡ ንጉሥ፡በርግጥ፡ይመጣል፡ይህችንም፡አገር፡ያፈርሳታል፡ከሰውና፡ከእንስሳም፡ባዶ፡ያደርጋታል፡ብለኽ፡ለምን፡ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org ጻፍኽበት፧ብለኽ፡ይህን፡ክርታስ፡አቃጥለኻል።

30ስለዚህም፡ስለይሁዳ፡ንጉሥ፡ስለ፡ኢዮአቄም፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦በዳዊት፡ዙፋን፡ላይ፡ ተቀማጭ፡አይኖርለትም፥ሬሳውም፡በቀን፡ለትኵሳት፡በሌሊትም፡ለውርጭ፡ይጣላል።

31ስለ፡ኀጢአታቸውም፡ርሱንና፡ዘሩን፡ባሪያዎቹንም፡እቀጣለኹ፤እነርሱም፡አልሰሙምና፡የተናገርኹባቸውን፡ ክፉ፡ነገር፡ዅሉ፡በእነርሱ፡ላይና፡በኢየሩሳሌም፡በሚቀመጡ፡በይሁዳም፡ሰዎች፡ላይ፡አመጣለኹ። ኤርምያስም፡ሌላ፡ክርታስ፡ወሰደ፡ለኔርያም፡ልጅ፡ለጸሓፊው፡ለባሮክ፡ሰጠው፤ርሱም፡የይሁዳ፡ንጉሥ፡ ኢዮአቄም፡በእሳት፡ያቃጠለውን፡የመጽሐፉን፡ቃል፡ዅሉ፡ከኤርምያስ፡አፍ፡ጻፈበት፥ደግሞም፡እንደ፡ ቀድሞው፡ያለ፡ቃል፡ብዙ፡ቃል፡ተጨመረበት።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source