1የባቢሎንም፡ንጉሥ፡ናቡከደነጾር፡በይሁዳ፡ያነገሠው፡የኢዮስያስ፡ልጅ፡ሴዴቅያስ፡በኢዮአቄም፡ልጅ፡ በኢኮንያን፡ፋንታ፡ነገሠ።
2ርሱም፡ኾነ፡ባሪያዎቹ፡የአገሩም፡ሕዝብ፡በነቢዩ፡በኤርምያስ፡እጅ፡የተናገረውን፡የእግዚአብሔርን፡ቃል፡ አልሰሙም።
3ንጉሡም፡ሴዴቅያስ፦ወደ፡አምላካችን፡ወደ፡እግዚአብሔር፡ስለ፡እኛ፡ጸልይ፡ብሎ፡የሰሌምያን፡ልጅ፡ ዮካልንና፡ካህኑን፡የመዕሴያን፡ልጅ፡ሶፎንያስን፡ወደ፡ነቢዩ፡ወደ፡ኤርምያስ፡ላከ።
4ርሱንም፡በግዞት፡ቤት፡ገና፡አላገቡትም፡ነበርና፥ኤርምያስ፡በሕዝቡ፡መካከል፡ይወጣና፡ይገባ፡ነበር።
5የፈርዖንም፡ሰራዊት፡ከግብጽ፡ወጣ፤ኢየሩሳሌምንም፡ከበ፟ዋት፡የነበሩ፡ከለዳውያን፡ይህን፡ወሬ፡በሰሙ፡ ጊዜ፡ከኢየሩሳሌም፡ተመለሱ።
6የእግዚአብሔርም፡ቃል፡ወደ፡ነቢዩ፡ወደ፡ኤርምያስ፡እንዲህ፡ሲል፡መጣ፦
7የእስራኤል፡አምላክ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ከእኔ፡ትጠይቁ፡ዘንድ፡የላካችኹን፡የይሁዳን፡ንጉሥ፡ እንዲህ፡በሉት፦እንሆ፥ሊረዳችኹ፡የወጣው፡የፈርዖን፡ሰራዊት፡ወደ፡አገሩ፡ወደ፡ግብጽ፡ይመለሳል።
8ከለዳውያንም፡ተመልሰው፡ይህችን፡ከተማ፡ይዋጓታል፡ይይዟትማል፡በእሳትም፡ያቃጥሏታል።
9እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦አይኼዱምና፦ከለዳውያን፡በርግጥ፡ከእኛ፡ዘንድ፡ይኼዳሉ፡ብላችኹ፡ ራሳችኹን፡አታታልሉ።
10እናንተም፡የሚዋጉትን፡የከለዳውያንን፡ሰራዊት፡ዅሉ፡ብትመቱት፡ኖሮ፥ከነርሱም፡የተወጉት፡ብቻ፡ቢቀሩ፡ ኖሮ፥ዅሉ፡እያንዳንዱ፡በድንኳኑ፡ተነሥቶ፡ይህችን፡ከተማ፡በእሳት፡ባቃጠሏት፡ነበር።
11የከለዳውያንም፡ሰራዊት፡ከፈርዖን፡ሰራዊት፡ፊት፡የተነሣ፡ከኢየሩሳሌም፡በተመለሰ፡ጊዜ፥
12ኤርምያስ፡በሕዝቡ፡መካከል፡የርስቱን፡ዕድል፡ፈንታ፡ከዚያ፡ይቀበል፡ዘንድ፡ወደብንያም፡አገር፡ሊኼድ፡ ከኢየሩሳሌም፡ወጣ።
13በብንያምም፡በር፡በነበረ፡ጊዜ፡የሐናንያ፡ልጅ፡የሰሌምያ፡ልጅ፡የሪያ፡የተባለ፡የዘበኛዎች፡አለቃ፡በዚያ፡ ነበረ፤ርሱም፦ወደ፡ከለዳውያን፡መኰብለልኽ፡ነው፡ብሎ፡ነቢዩን፡ኤርምያስን፡ያዘው።
14ኤርምያስም፦ሐሰት፡ነው፤ወደ፡ከለዳውያን፡መኰብለሌ፡አይደለም፡አለ፤ርሱ፡ግን፡ አልሰማውም፥የሪያም፡ኤርምያስን፡ይዞ፡ወደ፡አለቃዎች፡አመጣው።
15አለቃዎችም፡ተቈጥተው፡ኤርምያስን፡መቱት፥የጸሓፊውንም፡የዮናታንን፡ቤት፡የግዞት፡ቤት፡አድርገውት፡ ነበርና፥በዚያ፡አኖሩት።
16ኤርምያስም፡ወደጕድጓድ፡ቤት፡ወደ፡ጓዳዎቹ፡ገባ፤ኤርምያስም፡በዚያ፡ብዙ፡ቀን፡ከተቀመጠ፡በዃላ፥ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org
17ንጉሡ፡ሴዴቅያስ፡ልኮ፡አስመጣው፥ንጉሡም፡በቤቱ።በእውኑ፡ከእግዚአብሔር፡ዘንድ፡የኾነ፡ቃል፡ አለን፧ብሎ፡በቈይታ፡ጠየቀው።ኤርምያስም፦አዎን፡አለ።ደግሞም፦በባቢሎን፡ንጉሥ፡እጅ፡አልፈኽ፡ ትሰጣለኽ፡አለ።
18ኤርምያስም፡ደግሞ፡ንጉሡን፡ሴዴቅያስን፡እንዲህ፡አለው፦በግዞት፡ቤት፡የጣላችኹኝ፡አንተን፡ወይስ፡ ባሪያዎችኽን፡ወይስ፡ሕዝብኽን፡ምን፡በድያችኹ፡ነው፧
19የባቢሎን፡ንጉሥ፡በእናንተና፡በዚች፡አገር፡አይመጣባችኹም፡ብለው፡ትንቢት፡ይናገሩላችኹ፡የነበሩ፡ ነቢያታችኹ፡ወዴት፡አሉ፧
20ንጉሡ፡ጌታዬ፡ሆይ፥እንድትሰማኝ፡አኹን፡እለምንኻለኹ፤እባክኽ፥ልመናዬ፡ወዳንተ፡ይድረስ፤በዚያ፡ እንዳልሞት፡ወደጸሓፊው፡ወደዮናታን፡ቤት፡አትመልሰኝ።
21ንጉሡም፡ሴዴቅያስ፡አዘዘ፥ኤርምያስንም፡በግዞት፡ቤት፡አደባባይ፡አኖሩት፥እንጀራም፡ዅሉ፡ከከተማ፡ እስኪጠፋ፡ድረስ፡ዕለት፡ዕለት፡አንድ፡አንድ፡እንጀራ፡ከጋጋሪዎች፡መንገድ፡ይሰጡት፡ነበር።እንዲሁም፡ ኤርምያስ፡በግዞት፡ቤት፡አደባባይ፡ተቀምጦ፡ነበር።