1ኢየሩሳሌምም፡በተያዘች፡ጊዜ፥በይሁዳ፡ንጉሥ፡በሴዴቅያስ፡በዘጠነኛው፡ዓመት፡በዐሥረኛው፡ወር፡ የባቢሎን፡ንጉሥ፡ናቡከደነጾርና፡ሰራዊቱ፡ዅሉ፡ወደ፡ኢየሩሳሌም፡መጥተው፡ከበቧት፤
2በሴዴቅያስም፡በዐሥራ፡አንደኛው፡ዓመት፡በአራተኛው፡ወር፡ከወሩም፡በዘጠነኛው፡ቀን፡ከተማዪቱ፡ ተሰበረች። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org
3የባቢሎንም፡ንጉሥ፡አለቃዎች፡ዅሉ፥ኤርጌል፡ሳራስር፥ሳምጋርናቦ፥ሠርሰኪም፥ራፌስ፥ኤርጌል፡ ሳራስር፥ራብማግ፥ከቀሩት፡ከባቢሎን፡ንጉሥ፡አለቃዎች፡ዅሉ፡ጋራ፡ገብተው፡በመካከለኛው፡በር፡ውስጥ፡ ተቀመጡ።
4የይሁዳ፡ንጉሥ፡ሴዴቅያስ፡ሰልፈኛዎቹም፡ዅሉ፡ባይዋቸው፡ጊዜ፡ኰበለሉ፥በሌሊትም፡በንጉሡ፡አትክልት፡ መንገድ፡በኹለቱ፡ቅጥር፡መካከል፡ከነበረው፡ደጅ፡ከከተማዪቱ፡ወጡ፤በዐረባም፡መንገድ፡ወጡ።
5የከለዳውያንም፡ሰራዊት፡ተከታተላቸው፥ሴዴቅያስንም፡በኢያሪኮ፡ሜዳ፡አገኙት፤ይዘውም፡በሐማት፡ምድር፡ ወዳለችው፡ወደ፡ሪብላ፡ወደባቢሎን፡ንጉሥ፡ወደ፡ናቡከደነጾር፡አመጡት፡ርሱም፡ፍርድን፡በርሱ፡ላይ፡ ተናገረ።
6የባቢሎንም፡ንጉሥ፡የሴዴቅያስን፡ልጆች፡በዐይኑ፡ፊት፡በሪብላ፡ገደላቸው፤የባቢሎንም፡ንጉሥ፡የይሁዳን፡ ከበርቴዎች፡ዅሉ፡ገደለ።
7የሴዴቅያስንም፡ዐይን፡አወጣ፥ወደ፡ባቢሎንም፡ይወስደው፡ዘንድ፡በሰንሰለት፡አሰረው።
8ከለዳውያንም፡የንጉሡንና፡የሕዝቡን፡ቤቶች፡በእሳት፡አቃጠሉ፥የኢየሩሳሌምንም፡ቅጥር፡አፈረሱ።
9የዘበኛዎቹም፡አለቃ፡ናቡዘረዳን፡በከተማዪቱ፡የቀሩትን፡ሕዝብ፡ወደ፡ርሱም፡የኰበለሉትን፡ሰዎች፡ የቀረውንም፡የሕዝቡን፡ቅሬታ፡ወደ፡ባቢሎን፡ማረካቸው።
10አንዳች፡ከሌላቸው፡ከሕዝቡ፡ድኻዎች፡ግን፡የዘበኛዎቹ፡አለቃ፡ናቡዘረዳን፡በይሁዳ፡አገር፡ ተዋቸው፥የወይኑን፡ቦታና፡ዕርሻውን፡በዚያን፡ጊዜ፡ሰጣቸው። 11-
12የባቢሎንም፡ንጉሥ፡ናቡከደነጾር፡ስለ፡ኤርምያስ፦ውሰደውና፡በመልካም፡ተመልከተው፥የሚሻውንም፡ ነገር፡አድርግለት፡እንጂ፡ክፉን፡ነገር፡አታድርግበት፡ብሎ፡የዘበኛዎቹን፡አለቃ፡ናቡዘረዳንን፡አዘዘ።
13የዘበኛዎቹም፡አለቃ፡ናቡዘረዳን፡ላከ፥ናቡሽዝባንም፡ራፋስቂስም፡ኤርጌል፡ሳራስርም፡ራብማግም፡ የባቢሎንም፡ንጉሥ፡ዋና፡ዋና፡አለቃዎች፡ዅሉ፡ላኩ፤
14ኤርምያስንም፡ከግዞት፡ቤት፡አደባባይ፡አወጡት፥ወደ፡ቤቱም፡ይወስደው፡ዘንድ፡ለሳፋን፡ልጅ፡ ለአኪቃም፡ልጅ፡ለጎዶልያስ፡ሰጡት፤እንዲህም፡በሕዝብ፡መካከል፡ተቀመጠ።
15በግዞትም፡ቤት፡አደባባይ፡ታስሮ፡ሳለ፡የእግዚአብሔር፡ቃል፡እንዲህ፡ሲል፡ወደ፡ኤርምያስ፡መጣ፦
16ኺድ፡ለኢትዮጵያዊውም፡ለአቢሜሌክ ፡እንዲህ፡በለው፦የእስራኤል፡አምላክ፡የሰራዊት፡ጌታ፡ እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦እንሆ፥ለበጎነት፡ሳይኾን፡ለክፋት፡ቃሌን፡በዚች፡ከተማ፡ላይ፡ አመጣለኹ፤በዚያም፡ቀን፡በፊትኽ፡ይፈጸማል።
17በዚያ፡ቀን፡አድንኻለኹ፥ይላል፡እግዚአብሔር፤በምትፈራቸው፡ሰዎች፡እጅ፡አልሰጥኽም።
18ፈጽሜ፡አድንኻለኹ፡ነፍስኽም፡እንደ፡ምርኮ፡ትኾንልኻለች፡እንጂ፡በሰይፍ፡አትወድቅም፥በእኔ፡ ታምነኻልና፥ይላል፡እግዚአብሔር።