Skip to content
← Jeremiah

Chapter 40 · Amharic

Jeremiah

1ወደ፡ባቢሎን፡በተማረኩት፡በኢየሩሳሌምና፡በይሁዳ፡ምርኮኛዎች፡መካከል፡የዘበኛዎቹ፡አለቃ፡ናቡዘረዳን፡ በሰንሰለት፡አስሮ፡በወሰደው፡ጊዜ፡ከራማ፡ከለቀቀው፡በዃላ፡ከእግዚአብሔር፡ዘንድ፡ወደ፡ኤርምያስ፡የመጣ፡ ቃል፡ይህ፡ነው።

2የዘበኛዎቹም፡አለቃ፡ኤርምያስን፡ወሰደው፡እንዲህም፡አለው፦አምላክኽ፡እግዚአብሔር፡ይህን፡ክፉ፡ነገር፡ በዚህ፡ስፍራ፡ላይ፡ተናገረ፤

3እግዚአብሔርም፡አመጣው፡እንደ፡ተናገረውም፡አደረገ፤በእግዚአብሔርም፡ላይ፡ኀጢአት፡ 261 ዕብ.፥ዐበድመለክ፡(የንጉሥ፡አገልጋይ)። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org ሠርታችዃልና፥ቃሉንም፡አልሰማችኹምና፡ይህ፡ነገር፡ኾነባችኹ።

4አኹንም፥እንሆ፥በእጅኽ፡ካለችው፡ሰንሰለት፡ዛሬ፡ፈታኹኽ።ከእኔ፡ጋራ፡ወደ፡ባቢሎን፡መምጣት፡ መልካም፡መስሎ፡ቢታይኽ፥ና፥እኔም፡በመልካም፡አይኻለኹ፤ከእኔ፡ጋራ፡ወደ፡ባቢሎን፡መምጣት፡ መልካም፡መስሎ፡ባይታይኽ፡ግን፥ተቀመጥ፤እንሆ፥አገሪቱ፡ዅሉ፡በፊትኽ፡ናት፤ትኼድ፡ዘንድ፡መልካም፡ መስሎ፡ወደሚታይኽ፡ደስ፡ወደሚያሠኝኽም፡ስፍራ፡ኺድ።

5ርሱም፡ገና፡ሳይመለስ።የባቢሎን፡ንጉሥ፡በይሁዳ፡ከተማዎች፡ላይ፡ወደሾመው፡ወደሳፋን፡ልጅ፡ ወደአኪቃም፡ልጅ፡ወደ፡ጎዶልያስ፡ተመለስ፥ከርሱም፡ጋራ፡በሕዝቡ፡መካከል፡ተቀመጥ፤ወይም፡ትኼድ፡ ዘንድ፡ደስ፡ወደሚያሠኝኽ፡ስፍራ፡ኺድ፡አለው።የዘበኛዎቹም፡አለቃ፡ሥንቅና፡ስጦታ፡ሰጥቶ፡አሰናበተው።

6ኤርምያስም፡የአኪቃም፡ልጅ፡ጎዶልያስ፡ወዳለበት፡ወደ፡ምጽጳ፡ኼደ፥ከርሱም፡ጋራ፡በአገሩ፡ውስጥ፡ በቀሩት፡ሕዝብ፡መካከል፡ተቀመጠ።

7በየሜዳውም፡የነበሩት፡የጭፍራ፡አለቃዎችና፡ሰዎቻቸው፡ዅሉ፡የባቢሎን፡ንጉሥ፡የአኪቃምን፡ልጅ፡ ጎዶልያስን፡በምድር፡ላይ፡እንደ፡ሾመ፥ወንዶችንና፡ሴቶችን፡ልጆችንም፥ወደ፡ባቢሎን፡ያልተማረኩትን፡ የምድርን፡ድኻዎች፥እንዳስጠበቀ፡በሰሙ፡ጊዜ፡የናታንያ፡ልጅ፡እስማኤል፥

8የቃሬያም፡ልጅ፡ዮሐናንና፡ዮናታን፥የተንሑሜትም፡ልጅ፡ሰራያ፥የነጦፋዊውም፡የዮፌ፡ልጆች፡ የማዕካታዊውም፡ልጅ፡ያእዛንያ፡ከሰዎቻቸው፡ጋራ፡ወደ፡ጎዶልያስ፡ወደ፡ምጽጳ፡መጡ።

9የሳፋንም፡ልጅ፡የአኪቃም፡ልጅ፡ጎዶልያስ፡ለእነርሱና፡ለሰዎቻቸው፡እንዲህ፡ብሎ፡ማለ።ለከለዳውያን፡ ትገዙ፡ዘንድ፡አትፍሩ፤በምድር፡ተቀመጡ፡ለባቢሎንም፡ንጉሥ፡ተገዙ፥መልካምም፡ይኾንላችዃል።

10እኔም፥እንሆ፥ወደ፡እኛ፡በሚመጡት፡ከለዳውያን፡ፊት፡እቆም፡ዘንድ፡በምጽጳ፡እኖራለኹ፤እናንተ፡ ግን፡ወይንንና፡የበጋ፡ፍሬ፡ዘይትንም፡አከማቹ፥በየዕቃችኹም፡ውስጥ፡ክተቱ፥በያዛችዃቸውም፡ ከተማዎቻችኹ፡ተቀመጡ።

11በሞዐብም፡በዐሞንም፡ልጆች፡መካከል፡በኤዶምያስም፡በምድርም፡ዅሉ፡ላይ፡የነበሩ፡አይሁድ፡ዅሉ፡ የባቢሎን፡ንጉሥ፡የይሁዳን፡ቅሬታ፡እንዳስቀረ፥የሳፋንንም፡ልጅ፡የአኪቃምን፡ልጅ፡ጎዶልያስን፡በላያቸው፡ እንደ፡ሾመው፡በሰሙ፡ጊዜ፥

12አይሁድ፡ዅሉ፡ከተሰደዱበት፡ስፍራ፡ዅሉ፡ተመለሱ፥ወደይሁዳም፡አገር፡ጎዶልያስ፡ወዳለበት፡ወደ፡ ምጽጳ፡መጡ፥ወይንና፡የበጋንም፡ፍሬ፡እጅግ፡ብዙ፡አከማቹ።

13የቃሬያም፡ልጅ፡ዮሐናን፡በየሜዳውም፡የነበሩ፡የጭፍራ፡አለቃዎች፡ዅሉ፡ወደ፡ጎዶልያስ፡ወደ፡ምጽጳ፡ መጥተው፦

14የዐሞን፡ልጆች፡ንጉሥ፡በዓሊስ፡ይገድልኽ፡ዘንድ፡የናታንያን፡ልጅ፡እስማኤልን፡እንደ፡ሰደደ፡ ታውቃለኽን፧አሉት።የአኪቃም፡ልጅ፡ጎዶልያስ፡ግን፡አላመናቸውም።

15የቃሬያም፡ልጅ፡ዮሐናን፦እባክኽ፥ልኺድ፤ማንም፡ሳያውቅ፡የናታንያን፡ልጅ፡እስማኤልን፡ ልግደለው፤ወዳንተ፡የተሰበሰቡ፡አይሁድ፡ዅሉ፡እንዲበተኑ፡የይሁዳም፡ቅሬታ፡እንዲጠፋ፡ነፍስኽን፡ስለ፡ምን፡ ይገድላል፧ብሎ፡በምጽጳ፡በቈይታ፡ለጎዶልያስ፡ተናገረ።

16የአኪቃም፡ልጅ፡ጎዶልያስ፡ግን፡የቃሬያን፡ልጅ፡ዮሐናንን፦በእስማኤል፡ላይ፡ሐሰት፡ ተናግረኻልና፥ይህን፡ነገር፡አታድርግ፡አለው።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source