Skip to content
← Jeremiah

Chapter 41 · Amharic

Jeremiah

1በሰባተኛውም፡ወር፡ከመንግሥት፡ወገንና፡ከንጉሡ፡ዋና፡ዋና፡አለቃዎች፡አንዱ፡የኤሊሳማ፡ልጅ፡የናታንያ፡ ልጅ፡እስማኤል፡ከዐሥር፡ሰዎች፡ጋራ፡ወደ፡ምጽጳ፡ወደአኪቃም፡ልጅ፡ወደ፡ጎዶልያስ፡መጣ፤በዚያም፡ በምጽጳ፡ባንድ፡ላይ፡እንጀራ፡በሉ። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org

2የናታንያም፡ልጅ፡እስማኤል፡ከርሱም፡ጋራ፡የነበሩት፡ዐሥሩ፡ሰዎች፡ተነሥተው፡የሳፋንን፡ልጅ፡ የአኪቃምን፡ልጅ፡ጎዶልያስን፡በሰይፍ፡መቱ፥የባቢሎንም፡ንጉሥ፡በአገሩ፡ላይ፡የሾመውን፡ገደሉ።

3እስማኤልም፡ከጎዶልያስ፡ጋራ፡በምጽጳ፡የነበሩትን፡አይሁድ፡ዅሉ፥በዚያም፡የተገኙትን፡የከለዳውያንን፡ ሰልፈኛዎች፡ዅሉ፡ገደላቸው።

4ጎዶልያስን፡ከገደለ፡በዃላ፡ማንም፡ሳያውቅ፡በኹለተኛው፡ቀን፥

5ጢማቸውን፡ላጭተው፡ልብሳቸውንም፡ቀደ፟ው፡ገላቸውንም፡ነጭተው፥ወደእግዚአብሔር፡ቤት፡ያቀርቡ፡ ዘንድ፡የእኽል፡ቍርባንና፡ዕጣን፡በእጃቸው፡እየያዙ፥ሰማንያ፡ሰዎች፡ከሴኬምና፡ከሴሎ፡ከሰማርያም፡መጡ።

6የናታንያም፡ልጅ፡እስማኤል፡ከምጽጳ፡ወጥቶ፡እያለቀሰ፡ሊገናኛቸው፡ኼደ፤በተገናኛቸውም፡ ጊዜ፦ወደአኪቃም፡ልጅ፡ወደ፡ጎዶልያስ፡ኑ፡አላቸው።

7ወደከተማም፡መካከል፡በመጡ፡ጊዜ፡የናታንያ፡ልጅ፡እስማኤል፡ከርሱም፡ጋራ፡የነበሩ፡ሰዎች፡ ገደሏቸው፥በጕድጓድም፡መካከል፡ጣሏቸው።

8በመካከላቸውም፡እስማኤልን፦በሜዳ፡የተሸሸገ፡ስንዴና፡ገብስ፡ዘይትና፡ማርም፡አለንና፡አትግደለን፡ የሚሉት፡ዐሥር፡ሰዎች፡ተገኙ።ርሱም፡ተዋቸው፥ከወንድሞቻቸውም፡ጋራ፡አልገደላቸውም።

9እስማኤልም፡ከጎዶልያስ፡ጋራ፡የገደላቸውን፡የሰዎች፡ሬሳ፡ዅሉ፡የጣለበት፡ጕድጓድ፡ንጉሡ፡አሣ፡ የእስራኤልን፡ንጉሥ፡ባኦስን፡ስለ፡ፈራ፡የሠራው፡ጕድጓድ፡ነበረ፤የናታንያም፡ልጅ፡እስማኤል፡የገደላቸውን፡ ሞላበት።

10እስማኤልም፡በምጽጳ፡የነበረውን፡የሕዝቡን፡ቅሬታ፡ዅሉ፥የንጉሡን፡ሴቶች፡ልጆች፡የዘበኛዎቹም፡አለቃ፡ ናቡዘረዳን፡ለአኪቃም፡ልጅ፡ለጎዶልያስ፡የሰጠውን፡በምጽጳ፡የቀሩትን፡ሕዝብ፡ዅሉ፡ማረካቸው፤የናታንያም፡ ልጅ፡እስማኤል፡ማርኮ፡ወደዐሞን፡ልጆች፡ይኼድ፡ዘንድ፡ተነሣ።

11የቃሬያም፡ልጅ፡ዮሐናን፡ከርሱም፡ጋራ፡የነበሩ፡የጭፍራ፡አለቃዎች፡ዅሉ፡የናታንያ፡ልጅ፡እስማኤል፡ ያደረገውን፡ክፋት፡ዅሉ፡በሰሙ፡ጊዜ፥

12ሰዎቹን፡ዅሉ፡ይዘው፡ከናታንያ፡ልጅ፡ከእስማኤል፡ጋራ፡ሊዋጉ፡ኼዱ፥በገባዖንም፡ባለው፡በታላቁ፡ውሃ፡ አጠገብ፡አገኙት።

13ከእስማኤልም፡ጋራ፡የነበሩት፡ሕዝብ፡ዅሉ፡የቃሬያን፡ልጅ፡ዮሐናንን፡ከርሱም፡ጋራ፡የነበሩትን፡የጭፍራ፡ አለቃዎችን፡ዅሉ፡ባዩ፡ጊዜ፡ደስ፡አላቸው።

14እስማኤልም፡ከምጽጳ፡የማረካቸው፡ሕዝብ፡ዅሉ፡ዘወር፡ብለው፡ተመለሱ፥ወደቃሬያም፡ልጅ፡ወደ፡ ዮሐናን፡ኼዱ።

15የናታንያ፡ልጅ፡እስማኤል፡ግን፡ከስምንት፡ሰዎች፡ጋራ፡ከዮሐናን፡አመለጠ፡ወደዐሞንም፡ልጆች፡ኼደ።

16የቃሬያም፡ልጅ፡ዮሐናን፡ከርሱም፡ጋራ፡የነበሩት፡የጭፍራ፡አለቃዎች፡ዅሉ፡የአኪቃምን፡ልጅ፡ ጎዶልያስን፡በምጽጳ፡ከገደለው፡በዃላ፡ከናታንያ፡ልጅ፡ከእስማኤል፡ያስመለሷቸውን፡የሕዝቡን፡ቅሬታ፡ ዅሉ፥ከገባዖን፡ያስመለሷቸውን፡ሰልፈኛዎች፥ሴቶችንም፥ልጆችንም፥ጃን፡ደረባዎችንም፥ወሰዱ፤

17ተነሥተውም፡ወደ፡ግብጽ፡ይኼዱ፡ዘንድ፡በቤተ፡ልሔም፡አጠገብ፡ባለው፡በጌሮት፡ከመዓም፡ተቀመጡ፤

18እስማኤል፡የባቢሎን፡ንጉሥ፡በአገሩ፡ላይ፡የሾመውን፡የአኪቃምን፡ልጅ፡ጎዶልያስን፡ስለ፡ገደለው፡ ከለዳውያንን፡ፈርተዋልና።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source