Skip to content
← Jeremiah

Chapter 42 · Amharic

Jeremiah

1የጭፍራ፡አለቃዎችም፡ዅሉ፡የቃሬያም፡ልጅ፡ዮሐናን፡የሆሻያም፡ልጅ፡ያእዛንያ፡ሕዝብም፡ዅሉ፡ከታናሹ፡ ዠምሮ፡እስከ፡ታላቁ፡ድረስ፡ቀረቡ፥ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org 2-

3ነቢዩንም፡ኤርምያስን፦ዐይኖችኽ፡እንዳዩን፡ከብዙ፡ጥቂት፡ቀርተናልና፥ልመናችን፥እባክኽ፥በፊትኽ፡ ትድረስ፤አምላክኽም፡እግዚአብሔር፡የምንኼድበትን፡መንገድና፡የምናደርገውን፡ነገር፡ያሳየን፡ዘንድ፡ስለ፡ እኛ፥ስለዚህ፡ቅሬታ፡ዅሉ፥ወደ፡አምላክኽ፡ወደ፡እግዚአብሔር፡ጸልይ፡አሉት።

4ነቢዩም፡ኤርምያስ፦ሰምቻችዃለኹ፤እንሆ፥እንደ፡ቃላችኹ፡ወደ፡አምላካችኹ፡ወደ፡እግዚአብሔር፡ እጸልያለኹ፤እግዚአብሔርም፡የሚመልስላችኹን፡ዅሉ፡እነግራችዃለኹ፥ከእናንተም፡ምንም፡አልሸሽግም፡ አላቸው።

5ኤርምያስንም፦አምላክኽ፡እግዚአብሔር፡ባንተ፡እጅ፡ወደ፡እኛ፡የላከውን፡ነገር፡ዅሉ፡ ባናደርግ፥እግዚአብሔር፡በመካከላችን፡እውነተኛና፡ታማኝ፡ምስክር፡ይኹን።

6የአምላካችንን፡የእግዚአብሔርን፡ቃል፡በመስማታችን፡መልካም፡እንዲኾንልን፥መልካም፡ወይም፡ክፉ፡ ቢኾን፥አንተን፡ወደ፡ርሱ፡የምንልክኽ፡የአምላካችንን፡የእግዚአብሔርን፡ቃል፡እንሰማለን፡አሉት።

7ከዐሥር፡ቀን፡በዃላ፡የእግዚአብሔር፡ቃል፡ወደ፡ኤርምያስ፡መጣ።

8የቃሬያንም፡ልጅ፡ዮሐናንን፡ከርሱም፡ጋራ፡የነበሩትን፡የጭፍራ፡አለቃዎች፡ዅሉ፡ከታናሹ፡ዠምሮ፡እስከ፡ ታላቁ፡ድረስ፡ሕዝቡንም፡ዅሉ፡ጠራ፥እንዲህም፡አላቸው፦

9ጸሎታችኹን፡በፊቱ፡አቀርብ፡ዘንድ፡ወደ፡ርሱ፡የላካችኹኝ፡የእስራኤል፡አምላክ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ ይላል፦

10ስላደረግኹባችኹ፡ክፉ፡ነገር፡ተጸጽቻለኹና፡በዚች፡ምድር፡ብትቀመጡ፡እሠራችዃለኹ፡እንጂ፡ አላፈርሳችኹም፥እተክላችዃለኹ፡እንጂ፡አልነቅላችኹም።

11ከምትፈሩት፡ከባቢሎን፡ንጉሥ፡አትፍሩ፤አድናችኹ፡ዘንድ፡ከእጁም፡አስጥላችኹ፡ዘንድ፡እኔ፡ከእናንተ፡ ጋራ፡ነኝና፡አትፍሩ፥ይላል፡እግዚአብሔር።

12ርሱ፡እንዲምራችኹ፡ወደ፡አገራችኹም፡እንዲመልሳችኹ፡እኔ፡እምራችዃለኹ።

13እናንተ፡ግን፦በዚች፡ምድር፡አንቀመጥም፡ብትሉ፡የአምላካችኹንም፡የእግዚአብሔርን፡ቃል፡ባትሰሙ፥

14እናንተም፦አይደለም፤ሰልፍ፡ወደማናይባት፡የመለከትም፡ድምፅ፡ወደማንሰማባት፡ወደማንራብባትም፡ ወደግብጽ፡ምድር፡እንኼዳለን፡በዚያም፡እንቀመጣለን፡ብትሉ፥

15እናንተ፡የይሁዳ፡ቅሬታ፡ሆይ፥አኹን፡እንግዲህ፡የእግዚአብሔርን፡ቃል፡ስሙ፤የእስራኤል፡አምላክ፡ የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ወደ፡ግብጽ፡ትገቡ፡ዘንድ፡በዚያም፡ትቀመጡ፡ዘንድ፡ ፊታችኹን፡ብታቀኑ፥

16የምትፈሩት፡ሰይፍ፡በዚያ፡በግብጽ፡ምድር፡ያገኛችዃል፥ስለ፡ርሱም፡የምትደነግጡበት፡ራብ፡በዚያ፡ በግብጽ፡ይደርስባችዃል፥በዚያም፡ትሞታላችኹ።

17ወደ፡ግብጽም፡ይገቡ፡ዘንድ፡በዚያም፡ይቀመጡ፡ዘንድ፡ፊታቸውን፡በሚያቀኑ፡ሰዎች፡ዅሉ፡እንዲህ፡ ይኾንባቸዋል፤በሰይፍና፡በራብ፡በቸነፈርም፡ይሞታሉ፤እኔም፡ከማመጣባቸው፡ክፉ፡ነገር፡ማንም፡ አይቀርም፥ማንም፡አያመልጥም።

18የእስራኤል፡አምላክ፡የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላልና፦ቍጣዬና፡መዓቴ፡በኢየሩሳሌም፡ በሚኖሩ፡ላይ፡እንደ፡ፈሰሰ፥እንዲሁ፡ወደ፡ግብጽ፡በገባችኹ፡ጊዜ፡መዓቴ፡ይፈስ፟ባችዃል፤እናንተም፡ ለጥላቻና፡ለመደነቂያ፡ለመረገሚያና፡ለመሰደቢያ፡ትኾናላችኹ፥ይህንም፡ስፍራ፡ከእንግዲህ፡ወዲህ፡አታዩትም።

19እናንተ፡የይሁዳ፡ቅሬታ፡ሆይ፥እግዚአብሔር፦ወደ፡ግብጽ፡አትግቡ፡ብሎ፡ተናግሮባችዃልና፥ዛሬ፡ እንዳስጠነቀቅዃችኹ፡በርግጥ፡ዕወቁ።

20እናንተ፦ስለ፡እኛ፡ወደ፡አምላካችን፡ወደ፡እግዚአብሔር፡ጸልይ፥አምላካችንም፡እግዚአብሔር፡ የሚናገርኽን፡ዅሉ፡ንገረን፡እኛም፡እናደርገዋለን፡ብላችኹ፡ወደ፡እግዚአብሔር፡ወደ፡አምላካችኹ፡ ልካችኹኝ፡ነበርና፥ራሳችኹን፡አታላ፟ችዃል። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org

21እኔም፡ዛሬ፡ነግሬያችዃለኹ፥ወደ፡እናንተም፡በላከኝ፡ነገር፡ዅሉ፡የአምላካችኹን፡የእግዚአብሔርን፡ቃል፡ አልሰማችኹም።

22አኹንም፡ኼዳችኹ፡እንድትቀመጡ፡በወደዳችኹበት፡ስፍራ፡በሰይፍና፡በራብ፡በቸነፈርም፡እንድትሞቱ፡ በርግጥ፡ዕወቁ።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source