1በግብጽ፡ምድር፡በሚግዶልና፡በጣፍናስ፡በሜምፎስም፡በጳትሮስም፡አገር፡ስለተቀመጡ፡አይሁድ፡ዅሉ፡ ወደ፡ኤርምያስ፡የመጣ፡ቃል፡ይህ፡ነው፦
2የእስራኤል፡አምላክ፡የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦በኢየሩሳሌምና፡በይሁዳ፡ከተማዎች፡ ዅሉ፡ያመጣኹትን፡ክፉ፡ነገር፡ዅሉ፡አይታችዃል፤እንሆ፥ዛሬ፡ባድማ፡ኾነዋል፥የሚቀመጥባቸውም፡የለም። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org
3ይህም፡የኾነው፡ያስቈጡኝ፡ዘንድ፡ስላደረጉት፡ክፋት፥ለማያውቋቸውም፡ለሌላዎች፡አማልክት፡ያጥኑ፡ ዘንድ፡ያመልኳቸውም፡ዘንድ፡ስለ፡ኼዱ፡ነው።
4በማለዳም፡ተነሥቼ፡ባሪያዎቼን፡ነቢያትን፡ዅሉ፡ሰደድኹባችኹና፦እንደዚህ፡እንደ፡ጠላኹት፡ያለ፡ርኩስ፡ ነገር፡አታድርጉ፡አልዃችኹ።
5ነገር፡ግን፥አልሰሙም፡ከክፋታቸውም፡ተመልሰው፡ለሌላዎች፡አማልክት፡እንዳያጥኑ፡ዦሯቸውን፡ አላዘነበሉም።
6ስለዚህ፥መዓቴና፡ቍጣዬ፡ፈሰሱ፥በይሁዳም፡ከተማዎችና፡በኢየሩሳሌም፡አደባባይ፡ነደዱ፤ዛሬም፡ እንደኾነው፡ፈረሱ፡ባድማም፡ኾኑ።
7አኹንም፡የእስራኤል፡አምላክ፡የሰራዊት፡አምላክ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ከይሁዳ፡ወገን፡ቅሬታ፡ እንዳይቀርላችኹ፥ወንድንና፡ሴትን፥ብላቴናንና፡ሕፃንን፡ከመካከላችኹ፡ታጠፉ፡ዘንድ፡ይህን፡ታላቅ፡ክፋት፡ በራሳችኹ፡ላይ፡ለምን፡ታደርጋላችኹ፧
8ሰውነታችኹንም፡ታጠፉ፡ዘንድ፡በምድርም፡አሕዛብ፡ዅሉ፡መካከል፡መረገሚያና፡መሰደቢያ፡ትኾኑ፡ ዘንድ፥ለመቀመጥ፡በገባችኹባት፡በግብጽ፡ምድር፡ለሌላዎች፡አማልክት፡በማጠናችኹ፡በእጃችኹ፡ሥራ፡ ለምን፡ታስቈጡኛላችኹ፧
9በእውኑ፡በይሁዳ፡ምድርና፡በኢየሩሳሌም፡አደባባይ፡ያደረጉትን፡የአባቶቻችኹን፡ክፋት፥የይሁዳንም፡ ነገሥታት፡ክፋት፥የሚስቶቻቸውንም፡ክፋት፥የእናንተንም፡ክፋት፥የሚስቶቻችኹንም፡ክፋት፡ረስታችኹታልን፧
10እስከ፡ዛሬ፡ድረስ፡አልተዋረዱም፡አልፈሩምም፥በእናንተና፡በአባቶቻችኹም፡ፊት፡ባኖርኹት፡ሕጌና፡ ሥርዐቴ፡አልኼዱም።
11ስለዚህም፡የእስራኤል፡አምላክ፡የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦እንሆ፥ይሁዳን፡ዅሉ፡ አጠፋ፡ዘንድ፡ፊቴን፡ለክፋት፡በላያችኹ፡አደርጋለኹ።
12ወደ፡ግብጽም፡ይገቡ፡ዘንድ፡በዚያም፡ይቀመጡ፡ዘንድ፡ፊታቸውን፡ያቀኑትን፡የይሁዳን፡ቅሬታ፡ እወስዳለኹ፥ዅሉም፡ይጠፋሉ፥በግብጽም፡ምድር፡ይወድቃሉ፤በሰይፍና፡በራብ፡ይጠፋሉ፤ከታናሹም፡ዠምሮ፡ እስከ፡ታላቁ፡ድረስ፡በሰይፍና፡በራብ፡ይሞታሉ፤ለጥላቻና፡ለመደነቂያ፡ለመረገሚያና፡ለመሰደቢያ፡ይኾናሉ።
13ኢየሩሳሌምንም፡እንደ፡ቀጣኹ፥እንዲሁ፡በግብጽ፡ምድር፡የሚኖሩትን፡በሰይፍና፡በራብ፡በቸነፈርም፡ እቀጣለኹ።
14በዚያ፡ለመቀመጥ፡ወደግብጽ፡ምድር፡ከኼዱ፥ወደይሁዳ፡አገር፡ተመልሰው፡በዚያ፡ይቀመጡ፡ዘንድ፡ ከሚወዱ፡ከይሁዳ፡ቅሬታ፡ወገን፡የሚያመልጥና፡የሚቀር፡ወደዚያም፡የሚመለስ፡የለም፤ከሚያመልጥም፡በቀር፡ ማንም፡አይመለስም።
15ሚስቶቻቸውም፡ለሌላዎች፡አማልክት፡ማጠናቸውን፡ያወቁ፡ሰዎች፡ዅሉ፡በዚያም፡የቆሙ፡ሴቶች፡ ዅሉ፥በግብጽ፡ምድር፡በጳትሮስ፡የተቀመጡ፡ሕዝብ፡ዅሉ፥ታላቅ፡ጉባኤ፡ኾነው፡ለኤርምያስ፡መለሱለት፡ እንዲህም፡አሉ።
16አንተ፡በእግዚአብሔር፡ስም፡የነገርኸንን፡ቃል፡አንሰማኽም።
17ነገር፡ግን፥እኛና፡አባቶቻችን፡ነገሥታታችንም፡አለቃዎቻችንም፡በይሁዳ፡ከተማዎች፡በኢየሩሳሌም፡ አደባባይ፡እናደርገው፡እንደ፡ነበረ፥ለሰማይ፡ንግሥት፡እናጥን፡ዘንድ፡የመጠጥንም፡ቍርባን፡እናፈስ፟ላት፡ዘንድ፡ ከአፋችን፡የወጣውን፡ቃል፡ዅሉ፡በርግጥ፡እናደርጋለን፤በዚያን፡ጊዜም፡እንጀራ፡እንጠግብ፡ ነበር፥መልካምም፡ይኾንልን፡ክፉም፡አናይም፡ነበር።
18ለሰማይ፡ንግሥት፡ማጠንን፥ለርሷም፡የመጠጥን፡ቍርባን፡ማፍሰስን፡ከተውን፡ወዲህ፡ግን፥እኛ፡በዅሉ፡ ነገር፡ተቸግረናል፥በሰይፍና፡በራብ፡አልቀናል።
19እኛስ፡ለሰማይ፡ንግሥት፡ባጠን፟ላት፡የመጠጥንም፡ቍርባን፡ባፈሰስንላት፡ጊዜ፥በእውኑ፡ያለባሎቻችን፡ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org ምስሏን፡ለማብጀት፡ዕንጐቻ፡አድርገንላት፡ኖሯልን፧የመጠጥንም፡ቍርባን፡አፍሰ፟ንላት፡ኖሯልን፧
20ኤርምያስም፡ይህን፡ቃል፡ለመለሱለት፡ሕዝብ፡ዅሉ፥ለወንዶቹና፡ለሴቶቹ፡ለሕዝቡም፡ ዅሉ፥መለሰላቸው፡እንዲህም፡አለ።
21እናንተና፡አባቶቻችኹ፡ነገሥታታችኹም፡አለቃዎቻችኹም፡የምድርም፡ሕዝብ፡በይሁዳ፡ከተማዎችና፡ በኢየሩሳሌም፡አደባባይ፡ያጠናችኹትን፡ዕጣን፡እግዚአብሔር፡ያሰበው፡በልቡም፡ያኖረው፡አይደለምን፧
22እግዚአብሔርም፡ከእንግዲህ፡ወዲህ፡የሥራችኹን፡ክፋትና፡ያደረጋችኹትን፡ርኵሰት፡ይታገሥ፡ዘንድ፡ አልቻለም፤ስለዚህ፥ምድራችኹ፡ባድማ፣መደነቂያም፣መረገሚያም፡ኾናለች፥ዛሬም፡እንደ፡ኾነ፡የሚኖርባት፡ የለም።
23ስላጠናችኹ፥በእግዚአብሔርም፡ላይ፡ስለ፡በደላችኹ፥የእግዚአብሔርንም፡ቃል፡ስላልሰማችኹ፥በሕጉና፡ በሥርዐቱም፡በምስክሩም፡ስላልኼዳችኹ፥ስለዚህ፡ዛሬ፡እንደ፡ኾነ፡ይህች፡ክፉ፡ነገር፡አግኝታችዃለች።
24ኤርምያስም፡ለሕዝቡ፡ዅሉ፡ለሴቶቹም፡ዅሉ፡እንዲህ፡አለ፦በግብጽ፡ምድር፡የምትኖሩ፡ይሁዳ፡ ዅሉ፥የእግዚአብሔርን፡ቃል፡ስሙ።
25የእስራኤል፡አምላክ፡የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦እናንተና፡ሚስቶቻችኹ፡ በአፋችኹ።ለሰማይ፡ንግሥት፡እናጥን፡ዘንድ፡የመጠጥንም፡ቍርባን፡እናፈስ፟ላት፡ዘንድ፡የተሳልነውን፡ ስእለታችንን፡በርግጥ፡እንፈጽማለን፡አላችኹ፡በእጃችኹም፡አደረጋችኹት፤እንግዲህ፡ስእለታችኹን፡አጽኑ፡ ስእለታችኹንም፡ፈጽሙ።
26እናንተ፡በግብጽ፡ምድር፡የምትኖሩ፡ይሁዳ፡ዅሉ፥ስለዚህ፡የእግዚአብሔርን፡ቃል፡ስሙ፤በግብጽ፡ ምድር፡ዅሉ፡በሚኖር፡በይሁዳ፡ሰው፡ዅሉ፡አፍ፡ስሜ፡ከእንግዲህ፡ወዲህ።ሕያው፡እግዚአብሔርን! ተብሎ፡ እንዳይጠራ፥እንሆ፥በታላቅ፡ስሜ፡ምያለኹ፥ይላል፡እግዚአብሔር።
27እንሆ፥ለመልካም፡ሳይኾን፡ለክፋት፡እተጋባቸዋለኹ፤በግብጽም፡ምድር፡ያሉት፡የይሁዳ፡ሰዎች፡ዅሉ፡ እስኪጠፉ፡ድረስ፡በሰይፍና፡በራብ፡ያልቃሉ።
28ከሰይፍም፡የሚያመልጡ፡ጥቂት፡ሰዎች፡ኾነው፡ከግብጽ፡ምድር፡ወደይሁዳ፡ምድር፡ ይመለሳሉ፤ሊቀመጡም፡ወደግብጽ፡ምድር፡የገቡት፡የይሁዳ፡ቅሬታ፡ዅሉ፡ከእኔ፡ወይም፡ከነርሱ፡የማናችን፡ ቃል፡እንዲጸና፡ያውቃሉ።
29ቃሌም፡በላያችኹ፡ለክፋት፡እንዲጸና፡ታውቁ፡ዘንድ፡በዚች፡ስፍራ፡እንድቀጣችኹ፡ምልክታችኹ፡ይህ፡ ነው፥ይላል፡እግዚአብሔር።
30እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦የይሁዳን፡ንጉሥ፡ሴዴቅያስን፡ጠላቱ፡ለኾነው፡ነፍሱንም፡ለፈለገው፡ ለባቢሎን፡ንጉሥ፡ለናቡከደነጾር፡እጅ፡አሳልፌ፡እንደ፡ሰጠኹት፥እንዲሁ፥እንሆ፥የግብጹን፡ንጉሥ፡ፈርዖን፡ ሖፍራን፡ለጠላቶቹ፡ነፍሱንም፡ለሚፈልጉ፡እጅ፡አሳልፌ፡እሰጠዋለኹ።