Skip to content
← Jeremiah

Chapter 45 · Amharic

Jeremiah

1በይሁዳ፡ንጉሥ፡በኢዮስያስ፡ልጅ፡በኢዮአቄም፡በአራተኛው፡ዓመት፡የኔርያ፡ልጅ፡ባሮክ፡እነዚህን፡ቃሎች፡ ከኤርምያስ፡አፍ፡በመጽሐፍ፡በጻፋቸው፡ጊዜ፥ነቢዩ፡ኤርምያስ፡የተናገረው፡ቃል፡ይህ፡ነው፦

2ባሮክ፡ሆይ፥የእስራኤል፡አምላክ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይልኻል።

3አንተ፦እግዚአብሔር፡በሕመሜ፡ላይ፡ሐዘንን፡ጨምሮብኛልና፥ወዮልኝ! በልቅሶዬ፡ጩኸት፡ ደክሜያለኹ፥ዕረፍትንም፡አላገኘኹም፡ብለኻል።

4እንዲህ፡በለው፦እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦እንሆ፥የሠራኹትን፡አፈርሳለኹ፥የተከልኹትንም፡ እነቅላለኹ፤ይኸውም፡በምድር፡ዅሉ፡ነው። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org

5ለራስኽ፡ታላቅን፡ነገር፡ትፈልጋለኽን፧በሥጋ፡ለባሽ፡ዅሉ፡ላይ፥እንሆ፥ክፉ፡ነገርን፡አመጣለኹና፡ አትፈልገው፥ይላል፡እግዚአብሔር፤ነገር፡ግን፥በኼድኽበት፡ስፍራ፡ዅሉ፡ነፍስኽን፡እንደ፡ምርኮ፡አድርጌ፡ እሰጥኻለኹ።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source