Skip to content
← Jeremiah

Chapter 46 · Amharic

Jeremiah

1ስለ፡አሕዛብ፡ወደ፡ነቢዩ፡ወደ፡ኤርምያስ፡የመጣው፡የእግዚአብሔር፡ቃል፡ይህ፡ነው፦

2ስለ፡ግብጽ፤በኤፍራጥስ፡ወንዝ፡አጠገብ፡በከርከሚሽ፡ስለነበረው፥በይሁዳ፡ንጉሥ፡በኢዮስያስ፡ልጅ፡ በኢዮአቄም፡በአራተኛው፡ዓመት፡የባቢሎን፡ንጉሥ፡ናቡከደነጾር፡ስለመታው፡ስለግብጽ፡ንጉሥ፡ስለፈርዖን፡ ኒካዑ፡ሰራዊት።

3ጋሻ፡ጦር፡አዘጋጁ፡ወደ፡ሰልፍም፡ቅረቡ።

4ፈረሰኛዎች፡ሆይ፥ፈረሶችን፡ለጕሙና፡ውጡ፥ራስ፡ቍርንም፡ደፍታችኹ፡ቁሙ፤ጦርንም፡ሰንግሉ፡ ጥሩርንም፡ልበሱ።

5ፈርተው፡ወደ፡ዃላ፡ሲመለሱ፥ኀያላናቸውም፡ሲደበደቡ፡ወደ፡ዃላቸውም፡ሳይመለከቱ፡ፈጥነው፡ሲሸሹ፡ ለምን፡አየኹ፧በዚህና፡በዚያ፡ድንጋጤ፡አለ፥ይላል፡እግዚአብሔር።

6ፈጣኑ፡አያመልጥም፡ኀያሉም፡አይድንም፤በሰሜን፡በኤፍራጥስ፡ወንዝ፡በኩል፡ተሰናክለው፡ወደቁ።

7ይህ፡እንደ፡ግብጽ፡ወንዝ፡የሚነሣ፥ውሃውም፡እንደ፡ወንዝ፡የሚናወጥ፡ማን፡ነው፧

8ግብጽ፡እንደ፡ግብጽ፡ወንዝ፡ይነሣል፡ውሃውም፡እንደ፡ወንዙ፡ይናወጣል፤ርሱም፦እነሣለኹ፡ምድርንም፡ ዅሉ፡እከድናለኹ፤ከተማዎችንና፡የሚኖሩባቸውን፡አጠፋለኹ፡ብሏል።

9ፈረሶች፡ሆይ፥ውጡ፤ሠረገላዎችም፡ሆይ፥ንጐዱ፤ጋሻም፡የሚያነግቡ፡የኢትዮጵያና፡የፋጥ፡ ኀያላን፥ቀስትንም፡ይዘው፡የሚስቡ፡የሉድ፡ኀያላን፡ይውጡ።

10ያ፡ቀን፡ጠላቶቹን፡የሚበቀልበት፡የሰራዊት፡ጌታ፡የእግዚአብሔር፡የበቀል፡ቀን፡ነው፤ሰይፍ፡በልቶ፡ ይጠግባል፡በደማቸውም፡ይሰክራል፥ለሰራዊት፡ጌታ፡ለእግዚአብሔር፡በሰሜን፡ምድር፡በኤፍራጥስ፡ወንዝ፡ አጠገብ፡መሥዋዕት፡አለውና።

11ድንግሊቱ፡የግብጽ፡ልጅ፡ሆይ፥ወደ፡ገለዓድ፡ውጪ፥የሚቀባንም፡መድኀኒት፡ውሰጂ፤መድኀኒትን፡ ያበዛሽው፡በከንቱ፡ነው፤መዳን፡የለሽም።

12ኀያሉ፡በኀያሉ፡ላይ፡ተሰናክሎ፡ኹለቱ፡በአንድነት፡ወድቀዋልና፥አሕዛብ፡ጕስቍልናሽን፡ ሰምተዋል፥ልቅሶሽም፡ምድርን፡ሞልቷታል።

13የባቢሎን፡ንጉሥ፡ናቡከደነጾር፡እንዲመጣና፡የግብጽን፡ምድር፡እንዲመታ፡እግዚአብሔር፡ለነቢዩ፡ ለኤርምያስ፡የተናገረው፡ቃል፡ይህ፡ነው፦

14በግብጽ፡ተናገሩ፥በሚግዶልም፡አሰሙ፥በሜምፎስና፡በጣፍናስ፡አሰሙ፤ሰይፍ፡በዙሪያኽ፡ያለውን፡ በልቷልና፦ተነሥ፡ተዘጋጅም፡በሉ።

15ኀይለኛዎችኽ፡ስለ፡ምን፡ተወገዱ፧እግዚአብሔር፡ስላደከማቸው፡አልቆሙም።

16ብዛታቸውም፡ተሰናከለ፥ሰውም፡አንዱ፡በአንዱ፡ላይ፡ወደቀ፤እነርሱም፦ተነሡ፥ከሚያስጨንቅ፡ሰይፍ፡ ፊት፡ወደ፡ወገናችን፡ወደተወለድንባት፡ምድር፡እንመለስ፡አሉ።

17በዚያም፡የግብሥ፡ንጉሥ፡ፈርዖንን፦ሰዓቱን፡የሚያሳልፍ፡ጕረኛ፡ብለው፡ጠሩት።

18እኔ፡ሕያው፡ነኝና፡በተራራዎች፡መካከል፡እንዳለ፡እንደ፡ታቦር፥በባሕርም፡አጠገብ፡እንዳለ፡እንደ፡ ቀርሜሎስ፥እንዲሁ፡በእውነት፡ይመጣል፥ይላል፡ስሙ፡የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡የተባለው፡ንጉሥ። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org

19አንቺ፡በግብጽ፡የምትቀመጪ፡ልጅ፡ሆይ፥ሜምፎስ፡ባድማ፡ ትኾናለችና፥ትቃጠልማለችና፥የሚቀመጥባትም፡አይገኝምና፡ለምርኮ፡የሚኾን፡ዕቃ፡አዘጋጂ።

20ግብጽ፡የተዋበች፡ጊደር፡ናት፤ጥፋት፡ግን፡ይመጣል፥ከሰሜን፡በኩል፡ይመጣባታል።

21በርሷም፡ያሉ፡የተቀጠሩ፡ሠራተኛዎች፡እንደ፡ሰቡ፡ወይፈኖች፡ናቸው፤የጥፋታቸው፡ቀንና፡ የመጐብኘታቸው፡ጊዜ፡መጥቶባቸዋልና፥ተመለሱ፥በአንድነትም፡ሸሹ፥አልቆሙምም።

22ከሰራዊትም፡ጋራ፡ይኼዳሉና፥ድምፅ፡እንደ፡እባብ፡ይተማ፟ል፤እንደ፡ዕንጨት፡ቈራጮችም፡በምሣር፡ ይመጡባታል።

23ይቈጠሩ፡ዘንድ፡የማይቻሉትን፡የዱሯን፡ዛፎች፡ይቈርጣሉ፥ይላል፡እግዚአብሔር፤ከአንበጣ፡ይልቅ፡ በዝተዋልና፥ቍጥርም፡የላቸውምና።

24የግብጽ፡ልጅ፡ታፍራለች፤በሰሜን፡ሕዝብ፡እጅ፡ዐልፋ፡ትሰጣለች።

25የእስራኤል፡አምላክ፡የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦እንሆ፥የኖእ፡ ዐሞንን፥ፈርዖንንም፥ግብጽንም፥አማልክቷንና፡ነገሥታቷንም፥ፈርዖንና፡በርሱም፡የሚታመኑትን፡እቀጣለኹ፤

26ነፍሳቸውንም፡በሚፈልጉ፡ሰዎች፡እጅ፥በባቢሎንም፡ንጉሥ፡በናቡከደነጾር፡እጅ፥በባሪያዎቹም፡እጅ፡ አሳልፌ፡እሰጣቸዋለኹ፤ከዚያም፡በዃላ፡እንደ፡ቀድሞው፡ዘመን፡የሰው፡መኖሪያ፡ትኾናለች፥ይላል፡ እግዚአብሔር።

27ነገር፡ግን፥አንተ፡ባሪያዬ፡ያዕቆብ፡ሆይ፥አትፍራ፥አንተም፡እስራኤል፡ ሆይ፥አትደንግጥ፤እንሆ፥አንተን፡ከሩቅ፡ዘርኽንም፡ከተማረከባት፡ምድር፡አድናለኹ፤ያዕቆብም፡ተመልሶ፡ ያርፋል፡ተዘልሎም፡ይቀመጣል፥ማንም፡አያስፈራውምም።

28አንተ፡ባሪያዬ፡ያዕቆብ፡ሆይ፥እኔ፡ከአንተ፡ጋራ፡ነኝና፡አትፍራ፥ይላል፡እግዚአብሔር፤አንተንም፡ ያሰደድኹባቸውን፡አሕዛብን፡ዅሉ፡ፈጽሜ፡አጠፋለኹና፥አንተን፡ግን፡ፈጽሜ፡አላጠፋኽም፤በመጠን፡ እቀጣኻለኹ፥ያለቅጣትም፡አልተውኽም።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source