1ፈርዖንም፡ጋዛን፡ሳይመታ፡ስለ፡ፍልስጥኤማውያን፡ወደ፡ነቢዩ፡ወደ፡ኤርምያስ፡የመጣው፡የእግዚአብሔር፡ ቃል፡ይህ፡ነው፦
2እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦እንሆ፥ውሃ፡ከሰሜን፡ይነሣል፡የሚያጥለቀልቅም፡ፈሳሽ፡ ይኾናል፤በአገሪቱና፡በመላዋ፡ዅሉ፥በከተማዪቱና፡በሚኖሩባት፡ላይ፡ይጐርፋል፤ሰዎቹም፡ ይጮኻሉ፥በምድርም፡የሚኖሩ፡ዅሉ፡ያለቅሳሉ።
3ከኀይለኛዎች፡ፈረሶች፡ከኰቴያቸው፡መጠብጠብ፡ድምፅ፥ከሠረገላዎቹም፡መሸከርከር፥ከመንኰራኵሮቹም፡ መትመም፡የተነሣ፡አባቶች፡በእጃቸው፡ድካም፡ምክንያት፡ፊታቸውን፡መልሰው፡ወደ፡ልጆቻቸው፡ አይመለከቱም።
4ይህም፡የሚኾነው፡ፍልስጥኤማውያንን፡ዅሉ፡ያጠፋ፡ዘንድ፡የቀሩትንም፡ረዳቶች፡ዅሉ፡ከጢሮስና፡ከሲዶና፡ ይቈርጥ፡ዘንድ፡ስለሚመጣው፡ቀን፡ነው፤እግዚአብሔር፡ፍልስጥኤማውያንና፡የከፍቶርን፡ደሴት፡ቅሬታ፡ ያጠፋልና።
5ቡሓነት፡በጋዛ፡ላይ፡መጥቷል፤አስቀሎና፡ጠፋች፤የዔናቅ፡ቅሬታዎች፡ሆይ! እስከ፡መቼ፡ድረስ፡ ገላችኹን፡ትነጫላችኹ፧
6አንተ፡የእግዚአብሔር፡ሰይፍ፡ሆይ፥ዝም፡የማትለው፡እስከ፡መቼ፡ነው፧ወደ፡ሰገባኽ፡ግባ፡ጸጥ፡ ብለኽም፡ዕረፍ። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org
7እግዚአብሔር፡በአስቀሎናና፡በባሕር፡ዳር፡ላይ፡ትእዛዝ፡ሰጥቷልና፥በዚያም፡አዘጋጅቶታልና፥እንዴት፡ዝም፡ ትላለኽ፧