1ነፍሴ፡ሕይወቴን፡ሰለቸቻት፤ የሐዘን፡እንጕርጕሮዬን፡እለቀዋለኹ፤ በነፍሴም፡ምሬት፡እናገራለኹ።
2እግዚአብሔርን፡እንዲህ፡እለዋለኹ። አትፍረድብኝ፤የምትከራከረኝ፡ለምን፡እንደ፡ኾነ፡ንገረኝ።
3ልታስጨንቅና፡የእጅኽን፡ሥራ፡ልትንቅ፡ የኃጥኣንንስ፡ምክር፡ልታበራ፡ ባንተ፡ዘንድ፡መልካም፡ነውን፧
4በእውኑ፡የሥጋ፡ዐይን፡አለኽን፧ ወይስ፡ሰው፡እንደሚያይ፡ታያለኽን፧
6ወይስ፡ክፋቴን፡ትፈላለግ፡ዘንድ፥ ኀጢአቴንም፡ትመረምር፡ዘንድ፥ ዘመንኽ፡እንደ፡ሰው፡ዘመን፡ነውን፧ ወይስ፡ዓመታትኽ፡እንደ፡ሰው፡ዓመታት፡ናቸውን፧
7ከዚህም፡በላይ፡በደለኛ፡እንዳልኾንኹ፥ ከእጅኽም፡የሚያድን፡እንደሌለ፡አንተ፡ታውቃለኽ።
8እጅኽ፡ለወሰችኝ፥ሠራችኝም፤ ከዚያም፡በዃላ፡ዞረኽ፡ታጠፋኝ፡ዘንድ፡ፈለግኽ።
9እንደ፡ጭቃ፡አድርገኽ፡እንደ፡ለወስኸኝ፡ዐስብ፤ ወደ፡ትቢያም፡ትመልሰኛለኽን፧
10በእውኑ፡እንደ፡ወተት፡አላፈሰስኸኝምን፧ እንደ፡ርጎስ፡አላረጋኸኝምን፧
11ቍርበትና፡ሥጋ፡አለበስኸኝ፥ በዐጥንትና፡በዥማትም፡አጠነከርኸኝ።
12ሕይወትና፡ቸርነት፡አደረግኽልኝ፤ መጐብኘትኽም፡መንፈሴን፡ጠበቀች።
13እነዚህንም፡ነገሮች፡በልብኽ፡ውስጥ፡ሰወርኽ። ይህ፡ዅሉ፡በዐሳብኽ፡እንዳለ፡ዐውቃለኹ። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org
14ኀጢአት፡ብሠራ፡አንተ፡ትመለከተኛለኽ፤ ከኀጢአቴም፡ንጹሕ፡አታደርገኝም።
15በደለኛ፡ብኾን፡ወዮልኝ፤ ጻድቅም፡ብኾን፡ራሴን፡አላነሣም፤ ጕስቍልናን፡ተሞልቻለኹ፥ መከራዬንም፡ተመልክቻለኹ።
16ራሴም፡ከፍ፡ከፍ፡ቢል፡እንደ፡አንበሳ፡ታድነኛለኽ፤ ተመልሰኽም፡ድንቅ፡ነገር፡ታደርግብኛለኽ፡
17ምስክሮችኽን፡ታድስብኛለኽ፤ ቍጣኽንም፡ታበዛብኛለኽ፤ ጭፍራ፡በጭፍራ፡ላይ፡ትጨምርብኛለኽ።
18ስለ፡ምን፡ከማሕፀን፡አወጣኸኝ፧ ዐይን፡ሳያየኝ፡ምነው፡በሞትኹ።
19እንዳልነበረ፡በኾንኹ፤ ከማሕፀንም፡ወደ፡መቃብር፡በወሰዱኝ።
20የሕይወቴ፡ዘመን፡ጥቂት፡አይደለምን፧
21ወደማልመለስበት፡ስፍራ፥ ወደ፡ጨለማና፡ወደሞት፡ጥላ፡ምድር፥
22እንደ፡ጨለማም፡ወደጨለመች፥ ሥርዐትም፡ወደሌለባት፡ወደሞት፡ጥላ፥ ብርሃኗም፡እንደ፡ጨለማ፡ወደ፡ኾነ፡ምድር፡ሳልኼድ፥ ጥቂት፡እጽናና፡ዘንድ፡ተወኝ፥ልቀቀኝም።