Skip to content
← Job

Chapter 9 · Amharic

Job

1ኢዮብም፡መለሰ፡እንዲህም፡አለ፦

2በእውነት፡እንዲህ፡እንደ፡ኾነ፡ዐወቅኹ፤ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org ሰውስ፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡ጻድቅ፡መኾን፡እንዴት፡ይችላል፧

3ከርሱ፡ጋራ፡ይከራከር፡ዘንድ፡ቢወድ፟፥ ከሺሕ፡ነገር፡አንዱን፡መመለስ፡አይችልም።

4ልቡ፡ጠቢብ፥ኀይሉም፡ታላቅ፡ነው፤ ደፍሮትስ፡በደኅና፡የኼደ፡ማን፡ነው፧

5ተራራዎችን፡ይነቅላል፤አያውቁትም፤ በቍጣውም፡ይገለብጣቸዋል።

6ምድርን፡ከስፍራው፡ያናውጣታል፥ ምሰሶዎቿም፡ይንቀጠቀጣሉ።

7ፀሓይን፡ያዛ፟ታል፥አትወጣምም፤ ከዋክብትንም፡ያትማል።

8ሰማያትን፡ብቻውን፡ይዘረጋል፥ በባሕሩም፡ማዕበል፡ላይ፡ይረግጣል።

9ድብ፡የሚባለውን፡ኮከብና፡ኦሪዮን ፡የሚባለውን፡ኮከብ፥ሰባቱንም፡ከዋክብት፥ በደቡብም፡በኩል፡ያሉትን፡የከዋክብት፡ማደሪያዎች፡ሠርቷል።

10የማይመረመረውን፡ታላላቅ፡ነገር፥ የማይቈጠረውንም፡ተኣምራት፡ያደርጋል።

11እንሆ፥ቢመጣብኝ፡አላየውም፤ ቢያልፍብኝም፡አላውቀውም።

12እንሆ፥ፈጥኖ፡ቢነጥቅ፡የሚከለክለው፡ማን፡ነው፧ ርሱንስ፦ምን፡ታደርጋለኽ፧የሚለው፡ማን፡ነው፧

13እግዚአብሔር፡ቍጣውን፡አይመልስም፤ ከርሱ፡በታች፡ረዓብን፡የሚረዱ፡ይዋረዳሉ።

14ይልቁንስ፡እመልስለት፡ዘንድ፥ ቃሌንስ፡በፊቱ፡እመርጥ፡ዘንድ፡እኔ፡ማን፡ነኝ፧

15ጻድቅ፡ብኾን፡ኖሮ፡አልመልስለትም፡ነበር፤ ወደ፡ፈራጄም፡እለምን፡ነበር።

16ብጠራው፡ርሱም፡ቢመልስልኝ፡ኖሮ፥ ቃሌን፡እንደ፡ሰማ፡አላምንም፡ነበር።

17በዐውሎ፡ነፋስ፡ይሰብረኛል፥ ቍስሌንም፡ያለምክንያት፡ያበዛል።

18እተነፍስ፡ዘንድ፡አይተወኝም፥ 256 ጽር.፥ኦሬዎን፡(አርዮብ፥ጉቡኣን፡ከዋክብት•ታላቅ፡ኮከብ፥ካራቱ፡ዐበይት፡ከዋክብት፡አንዱ፥ከ.ወ.ክ.፥ገ.241)። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org ነገር፡ግን፡መራራን፡ነገር፡አጥግቦኛል።

19የኀይል፡ነገር፡ቢኾን፡ርሱ፡ኀያል፡ነው፤ የፍርድ፡ነገር፡ቢኾን፦ጊዜን፡ወሳኙ፡ማን፡ነው፧ይላል።

20ጻድቅ፡ብኾን፡አፌ፡ይወቅሰኛል፤ ፍጹምም፡ብኾን፡ጠማማ፡ያደርገኛል።

21ፍጹም፡ነኝ፡ራሴንም፡አልመለከትም፤ ሕይወቴንም፡እንቃታለኹ።

22ይህ፡ዅሉ፡አንድ፡ነው፤ስለዚህ፦ ፍጹማንንና፡ክፉዎችን፡ያጠፋል፡እላለኹ።

23መቅሠፍቱ፡ፈጥኖ፡ቢገድል፥ በንጹሓን፡ፈተና፡ይሳለቃል።

24ምድር፡በኃጥኣን፡እጅ፡ተሰጥታለች፤ የፈራጆቿን፡ፊት፡ሸፍኗል፤ ርሱ፡ካልኾነ፡ማን፡ነው፧

25ዘመኔ፡ከሚሮጥ፡ሰው፡ይልቅ፡ይፈጥናል፤ ይሸሻል፥መልካምንም፡አያይም።

26የደንገል፡ታንኳ፡እንደሚፈጥን፥ ንስርም፡ወደ፡ንጥቂያው፡እንደሚበር፟፡ያልፋል።

27እኔ፦የሐዘን፡እንጕርጕሮዬን፡እረሳለኹ፤ ፊቴን፡መልሼ፡እጽናናለኹ፡ብል፥

28ንጹሕ፡እንደማታደርገኝ፡እኔ፡ዐውቃለኹና፡ ከመከራዬ፡ዅሉ፡እፈራለኹ።

29በደለኛ፡እንደሚኾን፡ሰው፡እኾናለኹ፤ ስለ፡ምንስ፡በከንቱ፡እደክማለኹ፧

30በዐመዳይ፡ውስጥ፡ብታጠብ፥ እጆቼንም፡እጅግ፡ባነጻ፥

31በዐዘቅት፡ውስጥ፡ታሰጥመኛለኽ፥ ልብሴም፡ይጸየፈኛል።

32እንድመልስለት፡ዐብረን፡ወደ፡ፍርድ፡እንገባ፡ዘንድ፥ ርሱ፡እንደ፡እኔ፡ሰው፡አይደለም።

33እጁን፡በኹለታችን፡ላይ፡የሚያኖር፡ዳኛ፡ በመካከላችን፡ምነው፡በተገኘ!

34በትሩን፡ከእኔ፡ላይ፡ያርቅ፥ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org ግርማውም፡አያስፈራኝ፤

35እናገርም፡ነበር፥አልፈራውምም፡ነበር፤ በራሴ፡እንዲህ፡አይደለኹምና።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source