Skip to content
← Job

Chapter 8 · Amharic

Job

1ሹሐዊውም፡በልዳዶስ፡መለሰ፡እንዲህም፡አለ፦

2እስከ፡መቼ፡ይህን፡ትናገራለኽ፧ የአፍኽስ፡ቃል፡እስከ፡መቼ፡እንደ፡ዐውሎ፡ነፋስ፡ይኾናል፧

3በእውኑ፡እግዚአብሔር፡ፍርድን፡ያጣምማልን፧ ዅሉንም፡የሚችል፡አምላክ፡ጽድቅን፡ያጣምማልን፧

4ልጆችኽ፡በድለውት፡እንደ፡ኾነ፥ ርሱ፡በበደላቸው፡እጅ፡ጥሏቸዋል።

5እግዚአብሔርን፡ብትገሠግሥ፥ ዅሉንም፡የሚችለውን፡አምላክ፡ብትለምን፥

6ንጹሕና፡ቅን፡ብትኾን፥ በእውነት፡አኹን፡ስለ፡አንተ፡ይነቃል፥ የጽድቅኽንም፡መኖሪያ፡ያከናውንልኻል።

7ዥማሬኽ፡ታናሽ፡ቢኾንም፡እንኳ፡ ፍጻሜኽ፡እጅግ፡ይበዛል።

9ዘመናችን፡በምድር፡ላይ፡እንደ፡ጥላ፡ነውና፥ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org እኛ፡የትናንት፡ብቻ፡ነን፤ምንም፡አናውቅም፤ ስለዚህ፡የቀደመውን፡ትውልድ፡ጠይቅ፥ አባቶቻቸውም፡ለመረመሩት፡ነገር፡ትጋ፤

10እነርሱ፡የሚያስተምሩኽና፡የሚነግሩኽ፥ ቃልንም፡ከልባቸው፡የሚያወጡ፡አይደሉምን፧

11በእውኑ፡ደንገል፡ረግረግ፡በሌለበት፡መሬት፡ይበቅላልን፧ ወይስ፡ቄጠማ፡ውሃ፡በሌለበት፡ቦታ፡ይለመልማልን፧

12ገና፡ሲለመልም፡ሳይቈረጥም፥ ከአትክልት፡ዅሉ፡በፊት፡ይደርቃል።

13እግዚአብሔርን፡የሚረሱ፡ዅሉ፡ፍጻሜያቸው፡እንዲሁ፡ነው፤ የዝንጉም፡ሰው፡ተስፋ፡ይጠፋል።

14ተስፋው፡ይቈረጣል፥ እምነቱም፡እንደ፡ሸረሪት፡ቤት፡ይኾናል።

15ቤቱን፡ይደግፈዋል፥አይቆምለትም፤ ይይዘውማል፥አይጸናለትም።

16ፀሓይም፡ሳይተኵስ፡ይለመልማል፥ ጫፉም፡በአታክልቱ፡ቦታ፡ይወጣል።

17በድንጋይ፡ክምር፡ላይ፡ሥሩ፡ይጠመጠማል፤ የድንጋዮቹን፡ቦታ፡ይመለከታል።

18ከቦታው፡ቢጠፋ። አላየኹኽም፡ብሎ፡ይክደዋል።

19እንሆ፥የመንገዱ፡ደስታ፡እንዲህ፡ነው፤ ሌላዎችም፡ከመሬት፡ይበቅላሉ።

20እንሆ፥እግዚአብሔር፡ፍጹሙን፡ሰው፡አይጥለውም፥ የኀጢአተኛዎችንም፡እጅ፡አያበረታም።

21አፍኽን፡እንደ፡ገና፡ሣቅ፡ይሞላል፥ ከንፈሮችኽንም፡እልልታ፡ይሞላል።

22የሚጠሉኽ፡ዕፍረት፡ይለብሳሉ፤ የኀጢአተኛዎችም፡ድንኳን፡አይገኝም።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source