Skip to content
← Job

Chapter 7 · Amharic

Job

1በምድር፡ላይ፡የሰው፡ሕይወት፡ብርቱ፡ሰልፍ፡አይደለምን፧ ወራቱም፡እንደ፡ምንደኛ፡ወራት፡አይደለምን፧

2አገልጋይ፡ጥላ፡እንደሚመኝ፥ ምንደኛም፡ደመ፡ወዙን፡እንደሚጠብቅ፥

3እንዲሁ፡ዕጣዬ፡የከንቱ፡ወራት፡ኾነብኝ፥ የድካምም፡ሌሊት፡ተወሰነችልኝ።

4በተኛኹ፡ጊዜ፦መቼ፡እነሣለኹ፧እላለኹ። ሌሊቱ፡ግን፡ይረዝማል፥ እስኪነጋ፡ድረስም፡እገለባበጣለኹ።

5ሥጋዬ፡ትልና፡ጓል፡ለብሷል፤ ቍርበቴ፡ያፈከፍካል፡እንደ፡ገናም፡ይመግላል።

6ዘመኔ፡ከሸማኔ፡መወርወሪያ፡ይልቅ፡ይቸኵላል፥ ያለ፡ተስፋም፡ያልቃል።

7ሕይወቴ፡እስትንፋስ፡እንደ፡ኾነ፡ዐስብ፤ ዐይኔ፡መልካም፡ነገርን፡ከእንግዲህ፡ወዲህ፡አያይም።

8የሚያየኝ፡ሰው፡ዐይን፡ከእንግዲህ፡ወዲህ፡አያየኝም፤ ዐይንኽ፡በእኔ፡ላይ፡ይኾናል፥እኔም፡አልገኝም።

9ደመና፡ተበትኖ፡እንደሚጠፋ፥ እንዲሁ፡ወደ፡ሲኦል፡የሚወርድ፡ዳግመኛ፡አይወጣም።

10ወደ፡ቤቱ፡ዳግመኛ፡አይመለስም፥ ስፍራውም፡ዳግመኛ፡አያውቀውም።

11ስለዚህም፡አፌን፡አልከለክልም፤ በመንፈሴ፡ጭንቀትን፡እናገራለኹ፤ በነፍሴ፡ምሬት፡በሐዘን፡አንጐራጕራለኹ።

12ጠባቂ፡ታስነሣብኝ፡ዘንድ፥ እኔ፡ባሕር፡ወይስ፡ዐንበሪ፡ነኝን፧

13እኔም፦ዐልጋዬ፡ያጽናናኛል፥ መኝታዬም፡የሐዘን፡እንጕርጕሮዬን፡ያቀልልኛል፡ባልኹ፡ጊዜ፥

14አንተ፡በሕልም፡ታስፈራራኛለኽ፥ በራእይም፡ታስደነግጠኛለኽ፤

15ነፍሴም፡ከዐጥንቴ፡ይልቅ፡ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org መታነቅንና፡ሞትን፡መረጠች።

16ሕይወቴን፡ናቅዃት፤ለዘለዓለም፡ልኖር፡አልወድ፟ም። የሕይወቴ፡ዘመን፡እስትንፋስ፡ነውና፥ተወኝ።

17ሰው፡ምንድር፡ነው፡ታከብረው፡ዘንድ፥ ልብኽንስ፡ትጥልበት፡ዘንድ፥

18ማለዳ፡ማለዳስ፡ትጐበኘው፡ዘንድ፥ ዅልጊዜስ፡ትፈታተነው፡ዘንድ፧

19የማትተወኝ፡እስከ፡መቼ፡ነው፧ ምራቄንስ፡እስክውጥ፡ድረስ፡የማትለቀ፟ኝ፡እስከ፡መቼ፡ነው፧

20ሰውን፡የምትጠብቅ፡ሆይ፥በድዬስ፡እንደ፡ኾነ፡ምን፡ላድርግልኽ፧ ስለ፡ምን፡እኔን፡ለአንተ፡ዐላማ፡አደረግኸኝ፧ ስለ፡ምን፡እኔ፡ሸክም፡ኾንኩብኽ፧

21ስለ፡ምን፡መተላለፌን፡ይቅር፡አትልም፧ ኀጢአቴንስ፡ስለ፡ምን፡አታስወግድልኝም፧ አኹን፡በምድር፡ውስጥ፡እተኛለኹ፤ ማለዳ፡ትፈልገኛለኽ፥አታገኘኝም።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source