1ኢዮብም፡መለሰ፡እንዲህም፡አለ።
2ትካዜዬ፡ምነው፡በተመዘነ፡ኖሮ! መከራዬም፡ዅሉ፡ምነው፡በሚዛን፡ላይ፡በተደረገ፡ኖሮ!
3ከባሕር፡አሸዋ፡ይልቅ፡ይከብድ፡ነበርና፤ ስለዚህ፡ቃሌ፡ደፋር፡ኾኗል።
4ዅሉን፡የሚችል፡የአምላክ፡ፍላጻ፡በሥጋዬ፡ውስጥ፡ነው፥ መርዙንም፡ነፍሴ፡ትጠጣለች፤ የእግዚአብሔር፡ድንጋጤ፡በላዬ፡ተሰልፏል።
5በእውኑ፡የሜዳ፡አህያ፡ሣር፡ሳለው፡ይጮኻልን፧ ወይስ፡በሬ፡ገለባ፡ሳለው፡ይጮኻልን፧
6የማይጣፍጥስ፡ነገር፡ያለጨው፡ይበላልን፧ ወይስ፡የዕንቍላል፡ውሃ፡ይጥማልን፧
7ሰውነቴ፡ትነካው፡ዘንድ፡እንቢ፡አለችው፤ እንደሚያስጸይፍ፡መብል፡ኾነብኝ።
8ልመናዬ፡ምነው፡በደረሰልኝ! እግዚአብሔርም፡ምኞቴን፡ምነው፡በሰጠኝ!
9እግዚአብሔርም፡ያደቀኝ፡ዘንድ፡ እጁንም፡ለቆ፟፡ያጠፋኝ፡ዘንድ፡ወዶ፟፡ቢኾን፡ኖሮ!
10መጽናናት፡በኾነልኝ፡ነበር፤ በማይራራ፡ሕመም፡ሐሤት፡ባደረግኹ፡ነበር፥ የቅዱሱን፡ቃል፡አልካድኹምና።
11እጠብቅ፡ዘንድ፡ጕልበቴ፡ምንድር፡ነው፧ እታገሥም፡ዘንድ፡ፍጻሜዬ፡ምንድር፡ነው፧
12ጕልበቴ፡የድንጋይ፡ጕልበት፡ነውን፧ ሥጋዬስ፡እንደ፡ናስ፡ነውን፧
13በእውኑ፡ረድኤት፡በእኔ፡እንደሌለ፡ ጥበብም፡ዅሉ፡ከእኔ፡ዘንድ፡እንደ፡ተባረረ፡አይደለምን፧
14ዅሉን፡የሚችለውን፡የአምላክን፡መፍራት፡ ለሚተው፥ለመዛል፡ለቀረበው፡ስንኳ፡ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org ወዳጁ፡ቸርነትን፡ሊያሳይ፡ይገ፟ባ፟ል።
15ወንድሞቼ፡እንደ፡ፈፋ፥ እንደሚያልፍ፡ፈፋ፡ሐሰተኛዎች፡ኾኑብኝ።
16ከበረዶ፡የተነሣ፡ደፈረሱ፥ ዐመዳይም፡ተሰወረባቸው፤
17ፀሓይ፡በተኰሰች፡ጊዜ፡ይደርቃሉ፤ በሙቀትም፡ጊዜ፡ከስፍራቸው፡ይጠፋሉ።
18በየዳርቻቸውም፡የሚኼዱ፡ነጋዴዎች፡ፈቀቅ፡ይላሉ፤ ወደ፡በረሓ፡ወጥተው፡ይጠፋሉ።
19የቴማን፡ነጋዴዎች፡ተመለከቱ፥ የሳባ፡መንገደኛዎችም፡ተጠባበቋቸው።
20ተስፋ፡አድርገዋቸው፡ነበርና፥ዐፈሩ፤ ወደዚያ፡ደረሱ፥ዕፍረትም፡ያዛቸው።
21አኹንም፡እናንተ፡እንደዚሁ፡ኾናችዃል፤ መከራዬን፡አይታችኹ፡ፈራችኹ።
22በእውኑ፦አንዳች፡ነገር፡አምጡልኝ፤ ወይስ፦ከብልጥግናችኹ፡ስጦታ፡አቅርቡልኝ፤
23ወይስ፦ከጠላቴ፡እጅ፡አስጥሉኝ፤ ወይስ፦ካስጨናቂው፡እጅ፡አድኑኝ፡አልዃችኹን፧
24አስተምሩኝ፥እኔም፡ዝም፡እላለኹ፤ የተሳሳትኹትንም፡ንገሩኝ።
25የቅንነት፡ቃል፡እንዴት፡ኀይለኛ፡ነው! የእናንተ፡ሙግት፡ግን፡ምን፡ይገሥጻል፧
26ተስፋ፡የሌለው፡ሰው፡ንግግር፡እንደ፡ነፋስ፡ነውና፥ ቃሌን፡ትገሥጹ፡ዘንድ፡ታስባላችኹን፧
27በድኻ፡አደጉ፡ላይ፡ዕጣ፡ትጣጣላላችኹ፤ ለወዳጆቻችኹም፡ጕድጓድ፡ትቈፍራላችኹ።
28አኹንም፥እባካችኹ፥ወደ፡እኔ፡ተመልከቱ፤ በፊታችኹም፡ሐሰት፡አልናገርም።
29እባካችኹ፥ተመለሱ፤በደል፡አይኹን፤ ጽድቄ፡በዚህ፡ነገር፡ነውና፥አንድ፡ጊዜ፡ተመለሱ።
30በእውኑ፡በአንደበቴ፡በደል፡ይገኛልን፧ አፌስ፡ተንኰልን፡ይለይ፡ዘንድ፡አይችልምን፧ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org