Skip to content
← Job

Chapter 5 · Amharic

Job

1አኹንም፡ጥራ፤የሚመልስልኽ፡አለን፧ ከቅዱሳንስ፡ወደ፡ማናቸው፡ትዞራለኽ፧

2ሰነፉን፡ሰው፡ቍጣ፡ይገድለዋል፥ ሰነፉንም፡ቅንአት፡ያጠፋዋል።

3ሰነፍ፡ሰው፡ሥር፡ሰዶ፟፡አየኹት፥ ድንገትም፡መኖሪያውን፡ረገምኹ።

4ልጆቹም፡ከደኅንነት፡ርቀዋል፥ በበርም፡ውስጥ፡ተረግጠዋል፥ የሚታደጋቸውም፡የለም።

5የሰበሰበውንም፡ራብተኛ፡ይበላዋል፥ ከሾኽም፡ውስጥ፡እንኳ፡ያወጣዋል፤ የተጠማ፡ሀብታቸውን፡ዋጠ።

6ችግር፡ከትቢያ፡አይመጣም፥ መከራም፡ከመሬት፡አይበቅልም፤

7የአሞራ፡ግልገሎች፡ግን፡ወደ፡ላይ፡እየበረሩ፡ከፍ፡እንዲሉ፥ ሰው፡እንዲሁ፡ለመከራ፡ተወልዷል።

8እኔ፡ግን፡እግዚአብሔርን፡እለምን፡ነበር፥ ነገሬንም፡ወደ፡እግዚአብሔር፡አቀርብ፡ነበር።

9የማይመረመረውን፡ታላቅ፡ነገርና፡ የማይቈጠረውን፡ተኣምራት፡ያደርጋል።

10በምድር፡ላይ፡ዝናብን፡ይሰጣል፥ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org በዕርሻም፡ላይ፡ውሃ፡ይልካል።

11የተዋረዱትን፡ወደ፡ላይ፡ያወጣል፥ ሐዘንተኛዎችንም፡ለደኅንነት፡ከፍ፡ከፍ፡ያደርጋቸዋል።

12እጃቸውም፡ምክራቸውን፡እንዳይፈጽም፡ የተንኰለኛዎችን፡ዐሳብ፡ከንቱ፡ያደርገዋል።

13ጠቢባንን፡በተንኰላቸው፡ይይዛቸዋል፤ የጠማማዎችንም፡ምክር፡ይዘረዝራል።

14በቀን፡ጨለማን፡ያገኛሉ፥ በቀትርም፡ጊዜ፡በሌሊት፡እንዳሉ፡ይርመሰመሳሉ።

15ድኻውንም፡ከአፋቸው፡ሰይፍ፡ ከኀያሉም፡እጅ፡ያድነዋል።

16ለምስኪኑም፡ተስፋ፡አለው፤ ክፋት፡ግን፡አፏን፡ትዘጋለች።

17እንሆ፥እግዚአብሔር፡የሚገሥጸው፡ሰው፡ምስጉን፡ነው፤ ስለዚህ፡ዅሉን፡የሚችለውን፡የአምላክን፡ተግሣጽ፡አትናቅ።

18ርሱ፡ይሰብራል፥ይጠግንማል፤ ያቈስላል፥እጆቹም፡ይፈውሳሉ።

19በስድስት፡ክፉ፡ነገር፡ውስጥ፡ያድንኻል፥ በሰባትም፡ውስጥ፡ክፋት፡አትነካኽም።

20በራብ፡ጊዜ፡ከሞት፥ በሰልፍም፡ከሰይፍ፡እጅ፡ያድንኻል።

21ከምላስ፡ጅራፍ፡ትሰወራለኽ፤ ጥፋትም፡ሲመጣ፡አትፈራም።

22በጥፋትና፡በራብ፡ላይ፡ትሥቃለኽ፤ ከምድረ፡በዳ፡አራዊትም፡አትፈራም፤

23ቃል፡ኪዳንኽ፡ከምድረ፡በዳ፡ድንጋይ፡ጋራ፡ይኾናልና፤ የምድረ፡በዳም፡አራዊት፡ከአንተ፡ጋራ፡ይስማማሉና።

24ድንኳንኽም፡በሰላም፡እንዲኾን፡ታውቃለኽ፤ በረትኽን፡ትጐበኛለኽ፡አንዳችም፡አይጐድልብኽም።

25ዘርኽም፡ታላቅ፡እንዲኾን፥ ትውልድኽም፡እንደምድር፡ሣር፡እንዲኾን፡ታውቃለኽ።

26በወራቱ፡የእኽሉ፡ነዶ፡ወደ፡ዐውድማ፡እንዲገባ፥ በረዥም፡ዕድሜ፡ወደ፡መቃብር፡ትገባለኽ። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org

27እንሆ፥ይህችን፡መረመርን፥የሰማነውም፡ይህ፡ነው፤ አንተ፡ግን፡አንዳች፡ሠርተኽ፡እንደ፡ኾነ፡ለራስኽ፡ዕወቀው።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source