1ነዕማታዊውም፡ሶፋር፡መለሰ፥እንዲህም፡አለ፦
2በእውኑ፡ለቃል፡ብዛት፡መልስ፡መስጠት፡አይገ፟ባ፟ምን፧ ወይስ፡ተናጋሪ፡ሰው፡እንደ፡ጻድቅ፡ይቈጠራልን፧
3ትምክሕትኽስ፡ሰዎችን፡ዝም፡ያሠኛቸዋልን፧ ብትሳለቅስ፡የሚያሳፍርኽ፡የለምን፧
4አንተ፦ትምህርቴ፡የተጣራ፡ነው፥ በዐይንኽም፡ፊት፡ንጹሕ፡ነኝ፡ትላለኽ።
5ምነው፡እግዚአብሔር፡ቢናገርኽ! ባንተም፡ላይ፡ከንፈሩን፡ቢከፍት! http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org
6የጥበቡን፡ምስጢር፡ቢገልጥልኽ! ማስተዋሉ፡ብዙ፡ነውና። እግዚአብሔር፡ለበደልኽ፡ከሚገ፟ባ፟ው፡አሳንሶ፡እንደሚያስከፍልኽ፡ዕወቅ።
7የእግዚአብሔርን፡ጥልቅ፡ነገር፡ልትመረምር፡ትችላለኽን፧ ወይስ፡ዅሉን፡የሚችል፡አምላክ፡ፈጽመኽ፡ልትመረምር፡ትችላለኽን፧
8ከሰማይ፡ይልቅ፡ከፍ፡ይላል፤ምን፡ልታደርግ፡ትችላለኽ፧ ከሲኦልም፡ይልቅ፡ይጠልቃል፤ምን፡ልታውቅ፡ትችላለኽ፧
9ርዝመቱ፡ከምድር፡ይልቅ፡ይረዝማል፥ ከባሕርም፡ይልቅ፡ይሰፋል።
10ርሱ፡ቢያልፍ፥ቢዘጋም፥ጉባኤንም፡ቢሰበስብ፥ የሚከለክለው፡ማን፡ነው፧
11ምናምንቴዎችን፡ሰዎች፡ያውቃልና፥ በደልንም፡ሲያይ፡ዝም፡ብሎ፡አይመለከትም።
12የሜዳ፡አህያ፡ግልገል፡ሰው፡ኾኖ፡ቢወለድ፥ ያን፡ጊዜ፡ከንቱ፡ሰው፡ጥበብን፡ያገኛል።
14በእጅኽ፡በደል፡ቢኖር፡አርቀው፤ በድንኳንኽም፡ኀጢአት፡አይኑር፤ አንተ፡ልብኽን፡ቅን፡ብታደርግ፥ እጅኽንም፡ወደ፡ርሱ፡ብትዘረጋ፥
15በዚያን፡ጊዜ፡በእውነት፡ፊትኽን፡ያለነውር፡ታነሣለኽ፤ ትበረታለኽ፥አትፈራምም።
16መከራኽንም፡ትረሳለኽ፤ እንዳለፈ፡ውሃ፡ታስበዋለኽ።
17ከቅትር፡ይልቅ፡ሕይወትኽ፡ይበራል፤ ጨለማም፡ቢኾን፡እንደ፡ጧት፡ይኾናል።
18ተስፋም፡ስለ፡አለኽ፡ተዘልለኽ፡ትቀመጣለኽ፤ በዙሪያኽ፡ትመለከታለኽ፥በደኅንነትም፡ታርፋለኽ።
19ትተኛለኽ፥የሚያስፈራኽም፡የለም፤ ብዙ፡ሰዎችም፡ልመና፡ያቀርቡልኻል።
20የክፉዎች፡ዐይን፡ግን፡ትጨልማለች፤ የሚሸሹበትንም፡ያጣሉ፥ ተስፋቸውም፡ነፍሳቸውን፡ማውጣት፡ነው። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org