Skip to content
← Job

Chapter 12 · Amharic

Job

1ኢዮብም፡መለሰ፡እንዲህም፡አለ፦

2በርግጥ፡እናንተ፡ዐይነተኛዎች፡ሰዎች፡ናችኹ፤ ጥበብም፡ከእናንተ፡ጋራ፡ይሞታል።

3ነገር፡ግን፥እኔ፡ደግሞ፡እንደናንተ፡ማስተዋል፡አለኝ፤ ከእናንተም፡የማንስ፡አይደለኹም፤ እንደዚህ፡ያለውን፡ነገር፡የማያውቅ፡ማን፡ነው፧

4እግዚአብሔርን፡የጠራኹ፡ርሱም፡የመለሰልኝ፡እኔ፡ ለባልንጀራው፡መሳለቂያ፡እንደሚኾን፡ሰው፡ኾኛለኹ፤ ጻድቅና፡ፍጹም፡ሰው፡መሳለቂያ፡ኾኗል።

5ተዘልሎ፡በሚቀመጥ፡ሰው፡ዐሳብ፡መከራ፡ይናቃል፤ ነገር፡ግን፡እግሩን፡ሊያድጠው፡ተዘጋጅቷል።

6የቀማኛዎች፡ድንኳን፡በደኅንነት፡ይኖራል፥ እግዚአብሔርንም፡የሚያስቈጡ፡ተዘልለው፡ተቀምጠዋል፤ እግዚአብሔር፡ዅሉን፡በእጃቸው፡አምጥቶላቸዋል።

7አኹን፡ግን፡እንስሳዎችን፡ጠይቅ፥ያስተምሩኽማል፤ የሰማይንም፡ወፎች፡ጠይቅ፥ይነግሩኽማል።

8ወይም፡ለምድር፡ተናገር፥ርሷም፡ታስተምርኻለች፤ የባሕርም፡ዓሣዎች፡ይነግሩኻል።

9የእግዚአብሔር፡እጅ፡ይህን፡እንዳደረገ፡ ከነዚህ፡ዅሉ፡የማያውቅ፡ማን፡ነው፧

10የሕያዋን፡ዅሉ፡ነፍስ፡ የሰውም፡ዅሉ፡መንፈስ፡በእጁ፡ናት።

11ምላስ፡መብልን፡እንደሚቀምስ፥ ዦሮ፡ቃልን፡የሚለይ፡አይደለምን፧

12በሽምግልና፡ጊዜ፡ጥበብ፥ በዘመንስ፡ርዝመት፡ማስተዋል፡ይገኛል።

13በእግዚአብሔር፡ዘንድ፡ጥበብና፡ኀይል፡አለ፤ ለርሱ፡ምክርና፡ማስተዋል፡አለው።

14እንሆ፥ይፈርሳል፥የፈረሰውም፡ተመልሶ፡አይሠራም፤ በሰውም፡ቢዘጋበት፡የሚከፍትለት፡የለም።

15እንሆ፥ውሃዎቹን፡ይከለክላል፥እነርሱም፡ይደርቃሉ፤ እንደ፡ገና፡ይሰዳ፟ቸዋል፥ምድሪቱንም፡ይገለብጣሉ። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org

16ኀይልና፡ጥበብ፡በርሱ፡ዘንድ፡ናቸው፤ የሚስተውና፡የሚያስተው፡ለርሱ፡ናቸው።

17መካሮችንም፡እንደ፡ዘረፋ፡ይወስዳቸዋል፥ ፈራጆችንም፡ያሳብዳል።

18የነገሥታትንም፡እስራት፡ይፈታል፥ ወገባቸውንም፡በመታጠቂያ፡ያስራቸዋል።

19ካህናትን፡እንደ፡ዘረፋ፡ይወስዳቸዋል፥ ኀያላንንም፡ይገለብጣቸዋል።

20ከታመኑ፡ሰዎችም፡ቋንቋን፡ያርቃል፥ የሽማግሌዎችንም፡ማስተዋል፡ይወስድባቸዋል።

21በአለቃዎች፡ላይ፡ንቀትን፡ያፈሳ፟ል፥ የብርቱዎችንም፡መታጠቂያ፡ያላላል።

22ጥልቅ፡ነገር፡ከጨለማ፡ይገልጣል፥ የሞትንም፡ጥላ፡ወደ፡ብርሃን፡ያወጣል።

23አሕዛብን፡ከፍ፡ከፍ፡ያደርጋል፥እነርሱንም፡ያጠፋል፤ አሕዛብንም፡ያሰፋል፥እነርሱንም፡ያፈልሳቸዋል።

24ከምድር፡አሕዛብ፡አለቃዎች፡ዘንድ፡ማስተዋልን፡ይወስዳል፥ መንገድም፡በሌለበት፡በረሓ፡ያቅበዘብዛቸዋል።

25ብርሃንም፡ሳይኖር፡በጨለማ፡ይርመሰመሳሉ፤ እንደ፡ሰካራም፡ይቅበዘበዛሉ።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source