Skip to content
← Job

Chapter 13 · Amharic

Job

1እንሆ፥ይህን፡ዅሉ፡ዐይኔ፡አየች፤ ዦሮዬም፡ሰምታ፡አስተዋለችው።

2እናንተ፡የምታውቁትን፡እኔ፡ደግሞ፡ዐውቃለኹ፤ ከእናንተ፡የማንስ፡አይደለኹም።

3ነገር፡ግን፥ዅሉን፡ለሚችል፡አምላክ፡መናገር፡እፈልጋለኹ፥ ከእግዚአብሔርም፡ጋራ፡ለመዋቀስ፡እሻለኹ።

4እናንተ፡ግን፡በሐሰት፡ለባጮች፡ናችኹ፤ ዅላችኹ፡የማትጠቅሙ፡ባለመድኀኒቶች፡ናችኹ።

5ምነው፡ዝም፡ብላችኹ፡ብትኖሩ! ይህ፡ጥበብ፡በኾነላችኹ፡ነበር።

6አኹንም፡ክርክሬን፡ስሙ፥ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org የከንፈሬንም፡ሙግት፡አድምጡ።

7በእውኑ፡ስለ፡እግዚአብሔር፡ሐሰትን፡ትናገራላችኹን፧ ስለ፡ርሱም፡ሽንገላን፡ታወራላችኹን፧

8ለፊቱስ፡ታደላላችኹን፧ ስለ፡እግዚአብሔርስ፡ትከራከራላችኹን፧

9ቢመረምራችኹስ፡መልካም፡ይኾንላችዃልን፧ ወይስ፡በሰው፡እንደምትሣለቁ፡ትሣለቁበታላችኹን፧

10በስውር፡ለሰው፡ፊት፡ብታደሉ፡ ዘለፋ፡ይዘልፋችዃል።

11ክብሩስ፡አያስፈራችኹምን፧ ግርማውስ፡አይወድቅባችኹምን፧

12ምስሌዎቻችኹ፡የዐመድ፡ምሳሌዎች፡ናቸው፤ ምሽጎቻችኹ፡የጭቃ፡ምሽጎች፡ናቸው።

13ዝም፡በሉ፥እናገርም፡ዘንድ፡ተዉኝ፤ የኾነው፡ነገር፡ይምጣብኝ።

14ሥጋዬን፡በጥርሴ፡እይዛለኹ፥ ሕይወቴንም፡በእጄ፡አኖራለኹ።

15እንሆ፥ቢገድለኝ፡ስንኳ፡ርሱን፡በትዕግሥት፡እጠባበቃለኹ፤ ነገር፡ግን፡መንገዴን፡በፊቱ፡አጸናለኹ።

16ዝንጉ፡ሰው፡በፊቱ፡አይገባምና፡ ርሱ፡መድኀኒት፡ይኾንልኛል።

17ነገሬን፡ተግታችኹ፡ስሙ፥ ምስክርነቴንም፡በዦሯችኹ፡አድምጡ።

18እንሆ፥ሙግቴን፡አዘጋጅቻለኹ። እንደምጸድቅም፡ዐውቃለኹ።

19ከእኔስ፡ጋራ፡የሚፋረድ፡ማን፡ነው፧ አኹን፡እኔ፡ዝም፡ብል፡እሞታለኹ።

20ነገር፡ግን፥ኹለት፡ነገር፡አታድርግብኝ፤ የዚያን፡ጊዜ፡ከፊትኽ፡አልሰወርም፤

21እጅኽን፡ከእኔ፡አርቅ፤ ግርማኽም፡አታስደንግጠኝ።

22ከዚያም፡በዃላ፡ጥራኝ፥እኔም፡እመልስልኻለኹ። ወይም፡እኔ፡ልናገር፥አንተም፡መልስልኝ። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org

23ያለብኝስ፡በደልና፡ኀጢአት፡ምን፡ያኽል፡ነው፧ መተላለፌንና፡ኀጢአቴን፡አስታውቀኝ።

24ፊትኽን፡ከእኔ፡የሰወርኽ፥ እንደ፡ጠላትኽም፡የቈጠርኸኝ፡ስለ፡ምን፡ነው፧

25የረገፈውን፡ቅጠል፡ታስጨንቃለኽን፧ ወይስ፡የደረቀውን፡ዕብቅ፡ታሳድዳለኽን፧

26የመረረ፡ነገር፡ጽፈኽብኛልና፤ የሕፃንነቴንም፡ኀጢአት፡ታወርሰኛለኽ።

27እግሬንም፡በእግር፡ግንድ፡አግብተኻል፥ መንገዴንም፡ዅሉ፡መርምረኻል፤ የእግሬን፡ፍለጋ፡ወስነኻል።

28እኔ፡እንደሚጠፋ፡በስባሳ፡ነገር፥ ብልም፡እንደሚበላው፡ልብስ፡ነኝ።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source