Skip to content
← Job

Chapter 15 · Amharic

Job

1ቴማናዊውም፡ኤልፋዝ፡መለሰ፡እንዲህም፡አለ፦

2በእውኑ፡ጠቢብ፡ሰው፡እንደ፡ነፋስ፡በኾነ፡ዕውቀት፡ይመልሳልን፧ በሆዱስ፡የምሥራቅን፡ነፋስ፡ይሞላልን፧

3ከማይረባ፡ነገር፥ ወይስ፡ከማይጠቅም፡ንግግር፡ጋራ፡ይዋቀሳልን፧

4አንተም፡እግዚአብሔርን፡መፍራት፡ታፈርሳለኽ፤ በእግዚአብሔር፡ፊት፡አምልኮን፡ታስቀራለኽ።

5በደልኽ፡አፍኽን፡ያስተምረዋል፥ የተንኰለኛዎችንም፡አንደበት፡ትመርጣለኽ።

6የሚፈርድብኽ፡አፍኽ፡ነው፡እንጂ፡እኔ፡አይደለኹም። ከንፈሮችኽም፡ይመሰክሩብኻል።

7በእውኑ፡መዠመሪያ፡የተወለድኽ፡ሰው፡አንተ፡ነኽን፧ ወይስ፡ከተራራዎች፡በፊት፡ተፀነስኽን፧

8የእግዚአብሔርንስ፡ምስጢር፡ሰምተኻልን፧ ወይስ፡ጥበብን፡ለብቻኽ፡አድርገኻልን፧

9እኛ፡የማናውቀውን፡አንተ፡የምታወቀው፡ምንድር፡ነው፧ ከእኛ፡ዘንድስ፡የሌለው፡የምታስተውለው፡ምንድር፡ነው፧

10በዕድሜ፡ከአባትኽ፡የሚበልጡ፡ ሽበትም፡ያላቸው፡ሽማግሌዎችም፡ከእኛ፡ጋራ፡አሉ።

11በእውኑ፡የእግዚአብሔር፡ማጽናናት፥ በየውሀትም፡የተነገረኽ፡ቃል፡ጥቂት፡ነውን፧

12ልብኽስ፡ለምን፡ይወስድኻል፧ ዐይኖችኽስ፡ለምን፡ይገለምጣሉ፧

13በእግዚአብሔር፡ላይ፡መንፈስኽን፡እስከ፡ማንሣት፡ደርሰኽ፤ ይህንም፡ቃል፡ከአፍኽ፡እስከ፡ማውጣት፡ደርሰኽ።

14ንጹሕ፡ይኾን፡ዘንድ፡ሰው፡ምንድር፡ነው፧ ጻድቅስ፡ይኾን፡ዘንድ፡ከሴት፡የተወለደ፡ምንድር፡ነው፧

15እንሆ፥በቅዱሳኑ፡ስንኳ፡አይታመንም፤ ሰማያትም፡በፊቱ፡ንጹሓን፡አይደሉም።

16ይልቁንስ፡አስጸያፊና፡የረከሰ፥ ኀጢአትንም፡እንደ፡ውሃ፡የሚጠጣ፡ሰው፡ምንኛ፡ያንስ፧

18ምድሪቱ፡ለብቻቸው፡ተሰጥታ፡የነበር፥

19በመካከላቸውም፡እንግዳ፡ያልገባባቸው፡ጠቢባን። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org ከአባቶቻቸው፡ተቀብለው፡የተናገሩትን፡ያልሸሸጉትንም፥ እገልጥልኻለኹ፥ስማኝ፤ያየኹትንም፡እነግርኻለኹ።

20ክፉ፡ሰው፡ዕድሜውን፡ሙሉ፥ ከግፈኛ፡በተመደቡለት፡በዓመታት፡ዅሉ፡በሕመም፡ይጣጣራል።

21የሚያስደነግጥ፡ድምፅ፡በዦሮው፡ነው፤ በደኅንነቱም፡ሳለ፡ቀማኛ፡ይመጣበታል።

22ከጨለማ፡ተመልሶ፡እንዲወጣ፡አያምንም፥ ሰይፍም፡ይሸምቅበታል።

23ተቅበዝብዞም፦ወዴት፡አለ፧እያለ፡እንጀራ፡ይለምናል፤ የጨለማ፡ቀን፡እንደ፡ቀረበበት፡ያውቃል።

24መከራና፡ጭንቀት፡ያስፈራሩታል፤ ለሰልፍ፡እንደ፡ተዘጋጀ፡ንጉሥ፡ያሸንፉታል፤

25እጁን፡በእግዚአብሔር፡ላይ፡ዘርግቷልና፥ ዅሉንም፡በሚችል፡አምላክ፡ላይ፡ደፍሯልና፥

26በደንዳና፡ዐንገቱና፡በወፍራሙ፡በጋሻው፡ ጕብጕብ፡እየሰገገ፡ይመጣበታልና፥

27በስብም፡ፊቱን፡ከድኗልና፥ ስቡንም፡በወገቡ፡ላይ፡አድርጓልና፥

28በተፈቱም፡ከተማዎች፡ውስጥ፥ ሰውም፡በሌለባቸው፥ ክምር፡ለመኾን፡በተመደቡ፡ቤቶች፡ውስጥ፡ተቀምጧልና፥

29ባለጠጋ፡አይኾንም፥ሀብቱም፡አይጸናም፤ ጥላውንም፡በምድር፡ላይ፡አይጥልም፤

30ከጨለማ፡አይወጣም፤ ነበልባሉም፡ቅርንጫፎቹን፡ያደርቃቸዋል፥ አበባዎቹም፡ይረግፋሉ።

31ዋጋው፡ከንቱ፡ነገር፡ይኾናልና፥ ራሱን፡እያሳተ፡በከንቱ፡ነገር፡አይታመን።

32ቀኑ፡ሳይደርስ፡ጊዜው፡ይፈጸማል፥ ቅርንጫፉም፡አይለመልምም።

33እንደ፡ወይን፡ያልበሰለውን፡ዘለላ፡ያረግፋል፤ እንደ፡ወይራ፡አበባውን፡ይጥላል።

34የዝንጉዎች፡ጉባኤ፡ዅሉ፡ለጥፋት፡ይኾናል፥ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org የጕቦ፡ተቀባዮችንም፡ድንኳን፡እሳት፡ትበላለች።

35ጕዳትን፡ይፀንሳሉ፥በደልንም፡ይወልዳሉ፥ ሆዳቸውም፡ተንኰልን፡ያዘጋጃል።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source