1ኢዮብም፡መለሰ፡እንዲህም፡አለ፦
2እንደዚህ፡ያለ፡ዐይነት፡ነገር፡እጅግ፡ሰማኹ፤ እናንተ፡ዅላችኹ፡የምታደክሙ፡አጽናኞች፡ናችኹ።
3በእውኑ፡ከንቱ፡ቃል፡ይፈጸማልን፧ ወይስ፡ትመልስ፡ዘንድ፡ያነሣሣኽ፡ምንድር፡ነው፧
4እኔ፡ደግሞ፡እንደናንተ፡እናገር፡ዘንድ፡ይቻለኝ፡ነበር፤ ነፍሳችኹ፡በነፍሴ፡ፋንታ፡ቢኾን፡ኖሮ፥ እኔ፡በእናንተ፡ላይ፡ቃል፡ማሳካት፥ ራሴንም፡በእናንተ፡ላይ፡መነቅነቅ፡በተቻለኝ፡ነበር።
5በአፌም፡ነገር፡ባበረታዃችኹ፡ነበር፤ የከንፈሬን፡ማጽናናት፡ባልከለከልኹም፡ነበር።
6እኔ፡ብናገር፡ሕማሜ፡አይቀነስም፤ ዝምም፡ብል፡ከእኔ፡አይወገድም።
7አኹን፡ግን፡አድክሞኛል፤ ወገኔንም፡ዅሉ፡አፍርሰኻል።
8መጨማተሬ፡ይመሰክርብኛል፤ ክሳቴም፡ተነሥቶብኛል፤ በፊቴም፡ይመሰክርብኛል።
9በቍጣው፡ቀደደኝ፥ርሱም፡ጠላኝ፤ ጥርሶቹንም፡አፋጨብኝ፤ ጠላቴ፡ዐይኑን፡አፈጠጠብኝ፤
10እነርሱም፡አፋቸውን፡ከፈቱብኝ፤ እያላገጡ፡ጕንጬን፡ጠፈጠፉኝ፤ በአንድነትም፡ተሰበሰቡብኝ።
11እግዚአብሔር፡ለጠማማ፡ሰው፡አሳልፎ፡ሰጠኝ፥ በክፉዎችም፡እጅ፡ጣለኝ።
12ተዘልዬ፡ተቀምጬ፡ነበር፥ርሱም፡ሰበረኝ፤ ዐንገቴንም፡ይዞ፡ቀጠቀጠኝ፤ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org እንደ፡ዐላማ፡አድርጎ፡አቆመኝ።
13ቀስተኛዎቹ፡ከበቡኝ፤ ኵላሊቴንም፡ቈራረጠ፥ርሱም፡አልራራም፤ ሐሞቴን፡በምድር፡ላይ፡አፈሰሰ።
14በቍስል፡ላይ፡ቍስል፡ጨመረብኝ፤ እንደ፡ኀያል፡እየሰገገ፡ይሮጥብኛል።
15በቍርበቴ፡ላይ፡ማቅ፡ሰፋኹ፥ ቀንዴንም፡በመሬት፡ላይ፡አኖርኹ።
16ፊቴ፡ከልቅሶ፡የተነሣ፡ቀላ፤ የሞት፡ጥላ፡በዐይኖቼ፡ቆብ፡ላይ፡አለ፤
17ነገር፡ግን፥በእጄ፡ዐመፅ፡የለም፤ ጸሎቴም፡ንጹሕ፡ነው።
18ምድር፡ሆይ፥ደሜን፡አትክደኚ፥ ለጩኸቴም፡ማረፊያ፡አይኹን።
19አኹንም፥እንሆ፥ምስክሬ፡በሰማይ፡አለ፥ የሚመሰክርልኝም፡በአርያም፡ነው።
20ጸሎቴ፡ወደ፡እግዚአብሔር፡ይድረስ፥ ዐይኔም፡በፊቱ፡እንባ፡ታፍስ፟።
21የሰው፡ልጅ፡ከባልንጀራው፡ጋራ፡እንደሚሟገት፥ ሰው፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡ለመሟገት፡ምነው፡በቻለ!
22ጥቂቶች፡ዓመታት፡ካለፉ፡በዃላ፡ እኔ፡ወደማልመለስበት፡መንገድ፡እኼዳለኹ።