Skip to content
← Job

Chapter 17 · Amharic

Job

1መንፈሴ፡ደከመ፥ዘመኔ፡አለቀ፥ መቃብርም፡ተዘጋጅቶልኛል።

2አላጋጮች፡በእኔ፡ዘንድ፡አሉ፥ ዐይኔም፡በማስቈጣታቸው፡ዐደረች።

3አኹንም፡አንተ፡መያዣ፡ኾነኽ፡ተዋሰኝ፤ ከእኔ፡ጋራ፡አጋና፡የሚመታ፡ማን፡ነው፧

4ልባቸውም፡እንዳያስተውል፡ከልክለኸዋል፤ ስለዚህ፡ከፍ፡ከፍ፡አታደርጋቸውም።

5ለብዝበዛ፡ባልንጀራዎቹን፡አሳልፎ፡የሚሰጥ፡ሰው፥ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org የልጆቹ፡ዐይን፡ይጨልማል።

6ለሕዝብም፡ምሳሌ፡አደረገኝ፤ በፊቱ፡ላይ፡ጺቅ፡እንደሚሉበት፡ሰው፡ኾንኹ።

7ዐይኔም፡ከሐዘን፡የተነሣ፡ፈዘዘች፥ ብልቶቼም፡ዅሉ፡እንደ፡ጥላ፡ኾኑ።

8ቅኖች፡ሰዎች፡በዚህ፡ነገር፡ይደነቃሉ፥ ንጹሕም፡በዝንጉው፡ላይ፡ይበሳጫል።

9ጻድቅ፡ግን፡መንገዱን፡ያጠነክራል፥ እጁም፡ንጹሕ፡የኾነ፡ሰው፡ኀይልን፡እየጨመረ፡ይኼዳል።

10ነገር፡ግን፥እናንተ፡ዅሉ፡ተመልሳችኹ፡ወደ፡እኔ፡ኑ፤ በእናንተም፡ዘንድ፡ብልኀተኛ፡አላገኝም።

11ዕድሜዬ፡ዐለፈች፤ ዐሳቤና፡የልቤ፡መሣሪያ፡ተቈረጠ።

12ሌሊቱን፡ወደ፡ቀን፡ይለውጣሉ፤ ብርሃኑም፡ወደ፡ጨለማ፡የቀረበ፡ይመስላቸዋል።

13ተስፋ፡ባደርግ፡ሲኦል፡ቤቴ፡ናት፤ ምንጣፌንም፡በጨለማ፡ዘርግቻለኹ።

14መበስበስን፦አንተ፡አባቴ፡ነኽ፤ ትልንም፦አንቺ፡እናቴ፣እኅቴም፡ነሽ፡ብያለኹ።

15እንግዲህ፡ተስፋዬ፡ወዴት፡ነው፧ ተስፋዬንስ፡የሚያይ፡ማን፡ነው፧

16ዐብረን፡በመሬት፡ውስጥ፡ስናርፍ፥ ወደ፡ሲኦል፡ይወርዳል።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source