1ሹሐዊውም፡በልዳዶስ፡መለሰ፡እንዲህም፡አለ፦
2እስከ፡መቼ፡ቃልን፡ታጠምዳለኽ፧ አስተውል፥ከዚያም፡በዃላ፡እንናገራለን።
3ስለ፡ምንስ፡እንደ፡እንስሳዎች፡ተቈጠርን፧ ስለ፡ምንስ፡በዐይንኽ፡ፊት፡ረከስን፧
4ቍጣ፡ወርሶኻል፤አንተስ፡የሞትኽ፡እንደ፡ኾነ፥ ምድር፡ስለ፡አንተ፡ባድማ፡ትኾናለችን፧ ወይስ፡አለት፡ከስፍራው፡ይነቀላልን፧ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org
5የኀጢአተኛ፡መብራት፡ይጠፋል፥ የእሳቱም፡ነበልባል፡ብልጭ፡አይልም።
6ብርሃን፡በድንኳኑ፡ውስጥ፡ይጨልማል፥ መብራቱም፡በላዩ፡ይጠፋል።
7የኀይሉም፡ርምጃ፡ትጠባ፟ለች፥ ምክሩም፡ትጥለዋለች።
8እግሩ፡በወጥመድ፡ትያዛለች፥ በመረብም፡ላይ፡ይኼዳል።
9አሽክላ፡ሰኰናውን፡ይይዛል፥ ወስፈንጠርም፡ይበረታበታል።
10በምድር፡ላይ፡የሸምቀቆ፡ገመድ፥ በመንገዱም፡ላይ፡ወጥመድ፡ለርሱ፡ተሰውራለች።
11ድንጋጤ፡በዙሪያው፡ታስፈራዋለች፥ በስተዃላውም፡ኾና፡ታባርራቸዋለች።
12ኀይሉ፡በራብ፡ትደክማለች፥ መቅሠፍትም፡እስኪሰናከል፡ተዘጋጅቶለታል።
13የሰውነቱ፡ብልቶች፡ይጠፋሉ፤ የሞትም፡በኵር፡ልጅ፡ብልቶቹን፡ይበላል።
14ከሚታመንበት፡ድንኳን፡ይነቀላል፤ ወደ፡ድንጋጤም፡ንጉሥ፡ያስቸኵሉታል።
15በድንኳኑ፡ውስጥ፡ለርሱ፡የማይኾነው፡ይኖራል፤ በመኖሪያውም፡ላይ፡ዲን፡ይበተናል።
16ሥሩ፡ከበታቹ፡ይደርቃል፥ ጫፉም፡ከበላይ፡ይረግፋል።
17መታሰቢያው፡ከምድር፡ላይ፡ይጠፋል፥ በሜዳም፡ስም፡አይቀርለትም።
18ከብርሃን፡ወደ፡ጨለማ፡ያፈልሱታል፥ ከዓለምም፡ያሳድዱታል።
19ዘርም፡ትውልድም፡በሕዝቡ፡መካከል፡አይኾንለትም፤ በመኖሪያውም፡ውስጥ፡የሚቀመጥ፡ሰው፡አይቀርለትም።
20የፊተኛዎች፡ሰዎች፡እንደ፡ደነገጡ፥ እንዲሁ፡የዃለኛዎች፡ሰዎች፡ስለ፡ዘመኑ፡ይደነቃሉ።
21በእውነት፡የኀጢአተኛዎች፡ቤት፡እንዲሁ፡ናት፥ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org እግዚአብሔርንም፡የማያውቅ፡ሰው፡ስፍራ፡ይህ፡ነው።