Skip to content
← Job

Chapter 19 · Amharic

Job

1ኢዮብም፡መለሰ፡እንዲህም፡አለ፦

2ነፍሴን፡የምትነዘንዙ፥ በቃልስ፡የምታደቁ፟ኝ፡እስከ፡መቼ፡ነው፧

3ይኸው፡ስትሰድቡኝ፡ዐሥር፡ጊዜ፡ነው፤ ስታሻክሩኝም፡አላፈራችኹም።

4በእውነትም፡የሳትኹ፡እንደ፡ኾነ፥ ስሕተቴ፡ከእኔ፡ጋራ፡ትኖራለች።

5በእውነትም፡ብትጓደዱብኝ፥ መዋረዴን፡በእኔ፡ላይ፡ብትከራከሩ፥

6እንግዲህ፡እግዚአብሔር፡እንደ፡ገለበጠኝ፥ በመረቡም፡እንደ፡ከበበኝ፡ዕወቁ።

7እንሆ፥ስለተደረገብኝ፡ግፍ፡ብጮኽ፡ማንም፡አይመልስልኝም፤ አሰምቼም፡ብጠራ፡ፍርድ፡የለኝም።

8እንዳላልፍ፡መንገዴን፡ዘግቶታል፥ በጐዳናዬም፡ጨለማ፡አኑሮበታል።

9ክብሬን፡ገፈፈኝ፥ ዘውዴንም፡ከራሴ፡ላይ፡ወሰደ።

10በዚህና፡በዚያም፡አፈረሰኝ፥እኔም፡ኼድኹ፤ ተስፋዬንም፡እንደ፡ዛፍ፡ነቀለው፤

11ቍጣውንም፡አነደደብኝ፥ እንደ፡ጠላቱም፡ቈጠረኝ።

12ሰራዊቱ፡ዐብረው፡መጡ፥ መንገዳቸውንም፡በላዬ፡አዘጋጁ፥ በድንኳኔም፡ዙሪያ፡ሰፈሩ።

13ወንድሞቼን፡ከእኔ፡ዘንድ፡አራቀ፥ የሚያውቁኝም፡አጥብቀው፡ተለዩኝ።

14ዘመዶቼ፡ተቋረጡ፥ ወዳጆቼም፡ረሱኝ።

15ቤተ፡ሰቦቼና፡ሴቶች፡ባሪያዎቼ፡እንደ፡መጻተኛ፡ቈጠሩኝ፤ በዐይናቸውም፡እንደ፡እንግዳ፡ኾንኹ። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org

16ባሪያዬን፡ብጠራ፥በአፌም፡ባቈላምጥ፡አይመልስልኝም።

17ሚስቴ፡እስትንፋሴን፡ጠላች፥ የእናቴም፡ማሕፀን፡ልጆች፡ልመናዬን፡ጠሉ።

18ሕፃናት፡እንኳ፡አጠቁኝ፤ ብነሣም፡በእኔ፡ላይ፡ይናገራሉ።

19አማካሪዎቼ፡ዅሉ፡ተጸየፉኝ፤ እኔ፡የምወዳ፟ቸው፡በላዬ፡ተገለበጡ።

20ዐጥንቴ፡ከቍርበቴና፡ከሥጋዬ፡ጋራ፡ተጣበቀ፤ ድድ፡ብቻ፡ቀርቶልኝ፡አመለጥኹ።

21እናንተ፡ወዳጆቼ፡ሆይ፥ማሩኝ፤ የእግዚአብሔር፡እጅ፡መትታኛለችና፡ማሩኝ።

22ስለ፡ምን፡እናንተ፡እንደ፡እግዚአብሔር፡ታሳድዱኛላችኹ፧ ከሥጋዬስ፡ስለ፡ምን፡አትጠግቡም፧

23ምነው፡አኹን፡ቃሌ፡ቢጻፍ! ምነው፡በመጽሐፍ፡ውስጥ፡ቢታተም!

24ምነው፡በብረት፡ብርና፡በርሳስ፡ በአለቱ፡ላይ፡ለዘለዓለም፡ቢቀረጽ!

25እኔን፡ግን፡የሚቤዠኝ፡ሕያው፡እንደ፡ኾነ፥ በመጨረሻም፡ዘመን፡በምድር፡ላይ፡እንዲቆም፥

26ይህ፡ቍርበቴም፡ከጠፋ፡በዃላ፥ በዚያን፡ጊዜ፡ከሥጋዬ፡ተለይቼ፡እግዚአብሔርን፡እንዳይ፡ዐውቃለኹ።

27እኔ፡ራሴ፡አየዋለኹ፥ ዐይኖቼም፡ይመለከቱታል፥ ከእኔም፡ሌላ፡አይደለም። ልቤ፡በመናፈቅ፡ዝሏል።

28በእውነት፦እንዴት፡እናሳድደዋለን፧ የነገሩ፡ሥር፡በርሱ፡ዘንድ፡ተገኝቷል፡ብትሉ፥

29ፍርድ፡እንዳለ፡ታውቁ፡ዘንድ፡ ቍጣ፡የሰይፍን፡ቅጣት፡ያመጣልና፥ ከሰይፍ፡ፍሩ።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source