1ናዕማታዊውም፡ሶፋር፡መለሰ፡እንዲህም፡አለ፦ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org
2ስለዚህ፥በውስጤ፡ስላለው፡ችኰላ፡ዐሳቤ፡ትመልስልኛለች።
3የሚያሳፍረኝንም፡ተግሣጽ፡ሰምቻለኹ፥ የማስተዋሌም፡መንፈስ፡ይመልስልኛል።
4ሰው፡በምድር፡ላይ፡ከተቀመጠ፥ከዱሮ፡ዘመን፡ዠምሮ፥
5የኀጢአተኛ፡ፉከራ፡ዐጪር፡መኾኑን፡ የዝንጉዎችም፡ደስታ፡ቅጽበት፡መኾኑን፡አታውቁምን፧
6ከፍታው፡ወደ፡ሰማይ፡ቢወጣ፥ ራሱም፡እስከ፡ደመና፡ቢደርስ፥
7እንደ፡ፋንድያ፡ለዘለዓለም፡ይጠፋል፤ ያዩትም፦ወዴት፡ነው፧ይላሉ።
8እንደ፡ሕልም፡ይበራ፟ል፥ርሱም፡አይገኝም፤ እንደ፡ሌሊትም፡ራእይ፡ይሰደዳል።
9ያየችውም፡ዐይን፡ዳግመኛ፡አታየውም፤ ስፍራውም፡ከእንግዲህ፡ወዲህ፡አይመለከተውም።
10ልጆቹ፡ድኻዎቹን፡ያቈላምጣሉ፤ እጁ፡ሀብቱን፡ይመልሳል።
11ዐጥንቶቹ፡ብላቴንነቱን፡ሞልተዋል፤ ነገር፡ግን፡ከርሱ፡ጋራ፡በመሬት፡ውስጥ፡ይተኛል።
12ክፋት፡በአፉ፡ውስጥ፡ቢጣፍጥ፥ ከምላሱም፡በታች፡ቢሰውረው፥
13ቢጠብቀውም፡ባይተወውም፥ በጕረሮውም፡ቢይዘው፥
14መብሉ፡በአንዠቱ፡ውስጥ፡ይገላበጣል፤ እንደ፡እፍኝትም፡ሐሞት፡በውስጡ፡ይኾናል።
15የዋጠውን፡ሀብት፡ይተፋዋል፤ እግዚአብሔርም፡ከሆዱ፡ውስጥ፡ያወጣዋል።
16የእፍኝትን፡መርዝ፡ይጠባል፤ የእባብም፡ምላስ፡ይገድለዋል።
17የማሩንና፡የቅቤውን፡ፈሳሽ፡ ወንዞቹንም፡አይመለከትም።
18የድካሙን፡ፍሬ፡ሳይውጠው፡ይመልሰዋል፤ እንደ፡ንግዱም፡ትርፍ፡አይደሰትም።
19ድኻውን፡አስጨንቋል፥ትቶታልም፤ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org ያልሠራውንም፡ቤት፡በዝብዟል።
20ሆዱ፡ዕረፍትን፡አላወቀምና፡ የወደደው፡ነገር፡አላዳነውም።
21ርሱ፡ከበላ፡በዃላ፡ምንም፡አልተረፈም፤ ስለዚህ፡በረከቱ፡አይከናወንለትም።
22በጠገበ፡ጊዜ፡ይጨነቃል፤ የችግረኛዎችም፡ዅሉ፡እጅ፡ታገኘዋለች።
23ሆዱን፡ሳያጠግብ፡ እግዚአብሔር፡የቍጣውን፡ትኵሳት፡ይሰድ፟በታል፥ ሲበላም፡ያዘንብበታል።
24ከብረት፡መሣሪያም፡ይሸሻል፥ የናስም፡ቀስት፡ይወጋዋል።
25ርሱም፡ይመዘ፟ዋል፥ከሥጋውም፡ይወጣል፤ ከሐሞቱም፡ብልጭ፡ብሎ፡ይሠርጻል፤ ፍርሀትም፡ይወድቅበታል።
26ጨለማ፡ዅሉ፡ስለከበረው፡ዕቃ፡ተዘጋጅቷል፤ በሰው፡አፍ፡እፍ፡የማትባል፡እሳት፡ትበላዋለች፤ በድንኳኑ፡ውስጥ፡የቀረው፡ይጨነቅባታል።
27ሰማይ፡ኀጢአቱን፡ይገልጥበታል፥ ምድርም፡ትነሣበታለች።
28የቤቱም፡ባለጠግነት፡ይኼዳል፤ በቍጣው፡ቀን፡እንደ፡ፈሳሽ፡ውሃ፡ያልፋል።
29ከእግዚአብሔር፡ዘንድ፡የበደለኛ፡ሰው፡ዕድል፡ፈንታ፥ ከእግዚአብሔርም፡የተመደበ፡ርስቱ፡ይህ፡ነው።