1ኢዮብም፡መለሰ፡እንዲህም፡አለ፦
2ስሙ፥ቃሌን፡ስሙ፤ ይህም፡መጽናናታችኹ፡ይኹን።
3እናገር፡ዘንድ፡ተዉኝ፤ ከተናገርኹም፡በዃላ፡ተሣለቁ።
4በእውኑ፡የሐዘን፡እንጉርጕሮዬ፡ለሰው፡እናገራለኹን፧ አለመታገሥ፡ስለ፡ምን፡አይገ፟ባ፟ኝም፧ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org
5ወደ፡እኔ፡ተመልከቱ፥ተደነቁም፤ እጃችኹንም፡በአፋችኹ፡ላይ፡አኑሩ።
6እኔ፡ባሰብኹ፡ቍጥር፡እጨነቃለኹ፥ ጻዕርም፡ሥጋዬን፡ይይዛል።
7ስለ፡ምን፡ኀጢአተኛዎች፡በሕይወት፡ይኖራሉ፧ ስለ፡ምንስ፡ያረጃሉ፧በባለጠግነትስ፡ስለ፡ምን፡ይበረታሉ፧
8ዘራቸው፡ከነርሱ፡ጋራ፡ጸንቶ፡ይኖራል፥ ልጆቻቸውም፡በዐይናቸው፡ፊት፡ናቸው።
9ቤታቸው፡ከፍርሀት፡ወጥቶ፡የታመነ፡ነው፥ የእግዚአብሔርም፡በትር፡የለባቸውም።
10ኰርማቸው፡ይወልዳል፥ዘሩንም፡አይጥለውም፤ ላማቸውም፡ትወልዳለች፥አትጨነግፍም።
11ሕፃናታቸውን፡እንደ፡መንጋ፡ያወጣሉ፥ ልጆቻቸውም፡ይዘፍናሉ።
12ከበሮና፡መሰንቆ፡ወስደው፡ይዘምራሉ፥ በእንቢልታ፡ድምፅ፡ደስ፡ይላቸዋል።
13ዕድሜያቸውንም፡በተድላ፡ይፈጽማሉ፤ ድንገትም፡ወደ፡ሲኦል፡ይወርዳሉ።
14እግዚአብሔርንም፦ከእኛ፡ዘንድ፡ራቅ፤ መንገድኽን፡እናውቅ፡ዘንድ፡አንወድ፟ም።
15እናመልከውስ፡ዘንድ፡ዅሉን፡የሚችል፡አምላክ፡ማን፡ነው፧ ወይስ፡ወደ፡ርሱ፡ብንጸልይ፡ምን፡ይጠቅመናል፧ይላሉ።
16እንሆ፥ሀብታቸው፡በእጃቸው፡ውስጥ፡አይደለምን፧ የኃጥኣን፡ምክር፡ከእኔ፡ዘንድ፡የራቀች፡ናት።
17የኃጥኣን፡መብራት፡የጠፋው፥ መቅሠፍትም፡የመጣባቸው፥ እግዚአብሔርም፡በቍጣው፡መከራ፡የከፈላቸው፥
18በነፋስ፡ፊት፡እንደ፡ገለባ፥ ዐውሎ፡ነፋስም፡እንደሚወስደው፡ትቢያ፡የኾኑ፡ስንት፡ጊዜ፡ነው፧
19እናንተ፦እግዚአብሔር፡በደላቸውን፡ለልጆቻቸው፡ይጠብቃል፡ብላችዃል። እነርሱ፡ያውቁ፡ዘንድ፡ፍዳን፡ለራሳቸው፡ይክፈል።
20ዐይኖቻቸው፡ጥፋታቸውን፡ይዩ፥ ዅሉን፡ከሚችል፡አምላክ፡ቍጣ፡ይጠጡ። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org
21የወራታቸውስ፡ቍጥር፡ቢቈረጥ፥ ከነርሱ፡በዃላ፡የቤታቸው፡ደስታ፡ምን፡ይኾናቸዋል፧
22ከፍ፡ከፍ፡ባሉትስ፡ላይ፡ለሚፈርድ፡ለእግዚአብሔር፡ በእውኑ፡ሰው፡ዕውቀትን፡ያስተምራልን፧
23አንድ፡ሰው፡በሰላም፡ተዘልሎ፡ሲቀመጥ፡ በሙሉ፡ኀይሉ፡ሳለ፡ይሞታል።
24በአንዠቱ፡ውስጥ፡ስብ፡ሞልቷል፥ የዐጥንቶቹም፡ቅልጥም፡ረጥቧል።
25ሌላውም፡ሰው፡መልካምን፡ነገር፡ከቶ፡ሳይቀምስ፡ በተመረረች፡ነፍስ፡ይሞታል።
26በዐፈር፡ውስጥ፡ባንድ፡ላይ፡ይተኛሉ፥ ትልም፡ይከድናቸዋል።
27እንሆ፥ዐሳባችኹን፥ የመከራችኹብኝንም፡ክፉ፡ምክር፡ዐውቄዋለኹ።
28እናንተ፦የከበርቴው፡ቤት፡የት፡ነው፧ ኀጢአተኛውም፡ያደረበት፡ድንኳን፡የት፡ነው፧ብላችዃል።
29መንገድ፡ዐላፊዎችን፡አልጠየቃችኹምን፧ ምልክታቸውን፡አታውቁምን፧
30ኀጢአተኛው፡በመቅሠፍት፡ቀን፡እንደ፡ተጠበቀ፥ በቍጣው፡ቀን፡እንደሚድን።
31መንገዱን፡በፊቱ፡የሚናገር፡ማን፡ነው፧ የሠራውንስ፡የሚመልስበት፡ማን፡ነው፧
32ርሱን፡ግን፡ወደ፡መቃብር፡ይሸከሙታል፥ ሰዎቹም፡በመቃብሩ፡ላይ፡ይጠብቃሉ።
33የሸለቆው፡ጓል፡ይጣፍጥለታል፤ በዃላውም፡ሰው፡ዅሉ፡ይሳባል፥ በፊቱም፡ቍጥር፡የሌለው፡ጉባኤ፡አለ።
34የምትመልሱልኝ፡ውስልትና፡ነውና፥ በከንቱ፡እንዴት፡ታጽናኑኛላችኹ፧