Skip to content
← Job

Chapter 22 · Amharic

Job

1ቴማናዊውም፡ኤልፋዝ፡መለሰ፡እንዲህም፡አለ፦

2በእውኑ፡ሰው፡እግዚአብሔርን፡ይጠቅመዋልን፧ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org በእውነት፡ጥበበኛ፡ሰው፡ራሱን፡ይጠቅማል።

3ጻድቅ፡መኾንኽስ፡ዅሉን፡የሚችለውን፡አምላክ፡ደስ፡ያሠኘዋልን፧ መንገድኽን፡ማቅናትኽስ፡ይጠቅመዋልን፧

4ርሱንስ፡ስለ፡ፈራኽ፡ይዘልፍኻልን፧ ወደ፡ፍርድስ፡ከአንተ፡ጋራ፡ይገባልን፧

5ክፋትኽስ፡የበዛ፡አይደለምን፧ ለኀጢአትኽም፡ፍጻሜ፡የላትም።

6የወንድሞችኽን፡መያዣ፡በከንቱ፡ወስደኻል፥ የዕርዝተኛዎቹንም፡ልብስ፡ዘርፈኻል።

7ለደካማ፡ውሃ፡አላጠጣኽም፥ ለራብተኛም፡እንጀራን፡ከልክለኻል።

8በክንድ፡የበረታ፡ምድርን፡ገዛ፤ ከበርቴውም፡ሰው፡ተቀመጠባት።

9መበለቲቱን፡አንዳች፡አልባ፡ሰደ፟ኻታል፤ የድኻ፡አደጎችም፡ክንድ፡ተሰብሯል።

10ስለዚህ፥አሽክላ፡ከቦ፟ኻል፥ ድንገተኛ፡ፍርሀትም፡አናውጦኻል።

11እንዳታይ፡ብርሃን፡ጨለማ፡ኾነችብኽ፥ የውሃዎችም፡ብዛት፡አሰጠመኽ።

12እግዚአብሔር፡በሰማያት፡ከፍ፡ከፍ፡አይልምን፧ ከዋክብትም፡እንዴት፡ከፍ፡ከፍ፡እንዳሉ፡ተመልከት።

13አንተም፦እግዚአብሔር፡ምን፡ያውቃል፧ በድቅድቅ፡ጨለማ፡ውስጥ፡ኾኖ፡ሊፈርድ፡ይችላልን፧

14እንዳያይ፡የጠቈረ፡ደመና፡ጋርዶታል፤ በሰማይ፡ክበብ፡ላይ፡ይራመዳል፡ብለኻል።

15በእውኑ፡ኀጢአተኛዎች፡ሰዎች፡የረገጧትን፡ የዱሮዪቱን፡መንገድ፡ትጠብቃለኽን፧

16ጊዜያቸው፡ሳይደርስ፡ተነጠቁ፤ መሠረታቸውም፡እንደ፡ፈሳሽ፡ውሃ፡ፈሰሰ።

17እግዚአብሔርንም፦ከእኛ፡ዘንድ፡ራቅ፤ ዅሉንም፡የሚችል፡አምላክ፡ምን፡ሊያደርግልን፡ይችላል፧አሉት።

18ነገር፡ግን፥ቤታቸውን፡በመልካም፡ነገር፡ሞላ፤ የኃጥኣን፡ምክር፡ከእኔ፡ዘንድ፡የራቀች፡ናት። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org

19ጻድቃን፡ያዩታል፥ደስም፡ይላቸዋል፤ ንጹሓንም፡በንቀት፡ይሥቁባቸዋል።

20በእውነት፡ሀብታቸው፡ጠፋ፥ የቀረውንም፡እሳት፡በላች።

21አኹንም፡ከርሱ፡ጋራ፡ተስማማ፥ሰላምም፡ይኑርኽ፤ በዚያም፡በጎነት፡ታገኛለኽ።

22ከአፉም፡ሕጉን፡ተቀበል፥ በልብኽም፡ቃሉን፡አኑር፤

23ዅሉን፡ወደሚችል፡አምላክ፡ብትመለስ፥ብትዋረድም፥ ኀጢአትንም፡ከድንኳንኽ፡ብታርቅ፥

24የወርቅን፡ዕቃ፡በዐፈር፡ውስጥ፥ የኦፊርንም፡ወርቅ፡በጅረት፡ድንጋይ፡መካከል፡ብትጥል፥

25ዅሉን፡የሚችል፡አምላክ፡ወርቅና፡የሚብለጨለጭ፡ብር፡ይኾንልኻል።

26የዚያን፡ጊዜ፡ዅሉን፡በሚችል፡አምላክ፡ደስ፡ይልኻል፥ ፊትኽንም፡ወደ፡እግዚአብሔር፡ታነሣለኽ።

27ወደ፡ርሱም፡ትጸልያለኽ፥ርሱም፡ይሰማኻል፤ ስእለትኽንም፡ትሰጣለኽ።

28ነገርንም፡ትመክራለኽ፥ርሱም፡ይሳካልኻል፤ ብርሃንም፡በመንገድኽ፡ላይ፡ይበራል።

29ቢያዋርዱኽ፡አንተ፡ከፍ፡ከፍ፡ትላለኽ፤ ትሑቱንም፡ሰው፡ያድነዋል።

30ንጹሑን፡ሰው፡ያድነዋል፤ በእጅኽም፡ንጽሕና፡ትድናለኽ።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source