Skip to content
← Job

Chapter 23 · Amharic

Job

1ኢዮብም፡መለሰ፡እንዲህም፡አለ፦

2ዛሬም፡ደግሞ፡የሐዘን፡እንጕርጕሮዬ፡ገና፡መራራ፡ነው፤ እጁ፡በልቅሶ፡ጩኸቴ፡ላይ፡ከብዳለች።

3ርሱን፡ወዴት፡እንዳገኘው፡ምነው፡ባወቅኹ! ወደተቀመጠበትስ፡ስፍራ፡ምነው፡በደረስኹ!

4በፊቱ፡ሙግቴን፡አዘጋጅ፡ነበር፥ አፌንም፡በማስረጃ፡እሞላው፡ነበር።

5የሚመልስልኝም፡ቃል፡ምን፡እንደ፡ኾነ፡ዐውቅ፡ነበር፥ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org የሚለኝንም፡አስተውል፡ነበር።

6በኀይሉ፡ብዛት፡ከእኔ፡ጋራ፡ይሟገት፡ነበርን፧ እንኳን! ያደምጠኝ፡ነበር።

7ቅን፡ሰው፡ከርሱ፡ጋራ፡በዚያ፡ይከራከር፡ነበር፤ እኔም፡ከፈራጄ፡ለዘለዓለም፡እድን፡ነበር።

8እንሆ፥ወደ፡ፊት፡እኼዳለኹ፥ርሱም፡የለም፤ ወደ፡ዃላም፡እኼዳለኹ፥እኔም፡አላስተውለውም፤

9ወደሚሠራበት፡ወደ፡ግራ፡ብኼድ፡አልመለከተውም፤ በቀኜም፡ይሰወራል፥አላየውምም፤

10የምኼድበትን፡መንገድ፡ያውቃል፤ ከፈተነኝም፡በዃላ፡እንደ፡ወርቅ፡እወጣለኹ።

11እግሬ፡ወደ፡ርምጃው፡ተጣብቋል፤ መንገዱንም፡ጠብቄያለኹ፥ፈቀቅም፡አላልኹም።

12ከከንፈሩ፡ትእዛዝ፡አልተመለስኹም፤ የአፉን፡ቃል፡በልቤ፡ሰውሬያለኹ።

13ርሱ፡ግን፡ብቻውን፡ነው፤ርሱንስ፡የሚመስለው፡ማን፡ነው፧ ነፍሱም፡የወደደችውን፡ያደርጋል።

14በእኔ፡ላይ፡የተወሰነውን፡ይፈጽማል፤ እንደዚህም፡ያለ፡ብዙ፡ነገር፡በርሱ፡ዘንድ፡አለ።

15ስለዚህ፥በፊቱ፡ደነገጥኹ፤ ባሰብኹም፡ጊዜ፡ከርሱ፡ፈራኹ።

16እግዚአብሔር፡ልቤን፡አባብቶታልና፥ ዅሉንም፡የሚችል፡አምላክ፡አስደንግጦኛል።

17ከጨለማው፡የተነሣ፥ ድቅድቁም፡ጨለማ፡ፊቴን፡ከመክደኑ፡የተነሣ፡አልደነገጥኹም።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source