Skip to content
← Job

Chapter 2 · Amharic

Job

1ከዕለታት፡አንድ፡ቀን፡እንዲህ፡ኾነ፤የአምላክ፡ልጆች፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡ለመቆም፡መጡ፥ሰይጣን፡ ደግሞ፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡ለመቆም፡በመካከላቸው፡መጣ።

2እግዚአብሔርም፡ሰይጣንን፦ከወዴት፡መጣኽ፧አለው።ሰይጣንም፦በምድር፡ላይ፡ዞርኹ፥በርሷም፡ ተመላለስኹ፡ብሎ፡ለእግዚአብሔር፡መለሰ።

3እግዚአብሔርም፡ሰይጣንን፦በእውኑ፡ባሪያዬን፡ኢዮብን፡ተመለከትኸውን፧በምድር፡ላይ፡እንደ፡ርሱ፡ ፍጹምና፡ቅን፥እግዚአብሔርንም፡የሚፈራ፥ከክፋትም፡የራቀ፡ሰው፡የለም፤በከንቱም፡አጠፋው፡ዘንድ፡አንተ፡ በርሱ፡ላይ፡ምንም፡ብታንቀሳቅሰኝ፥እስከ፡አኹን፡ፍጹምነቱን፡ይዟል።

4ሰይጣንም፡መልሶ፡እግዚአብሔርን፦ቍርበት፡ስለ፡ቍርበት፡ነው፤ሰው፡ያለውን፡ዅሉ፡ስለ፡ሕይወቱ፡ ይሰጣል።

5ነገር፡ግን፥አኹን፡እጅኽን፡ዘርግተኽ፡ዐጥንቱንና፡ሥጋውን፡ዳብስ፤በእውነት፡በፊትኽ፡ይሰድብኻል፡ አለው።

6እግዚአብሔርም፡ሰይጣንን፦ሕይወቱን፡ተወው፡እንጂ፥እንሆ፥ርሱ፡በእጅኽ፡ነው፡አለው።

7ሰይጣንም፡ከእግዚአብሔር፡ፊት፡ወጣ፥ኢዮብንም፡ከእግሩ፡ጫማ፡ዠምሮ፡እስከ፡ዐናቱ፡ድረስ፡በክፉ፡ ቍስል፡መታው።

8ሥጋውንም፡ይፍቅበት፡ዘንድ፡ገል፡ወሰደ፥በዐመድም፡ላይ፡ተቀመጠ።

9ሚስቱም፦እስከ፡አኹን፡ፍጹምነትኽን፡ይዘኻልን፧እግዚአብሔርን፡ስደብና፡ሙት፡አለችው። (የሚቀጥለው፡ከግሪክ፡የተጨመረ፡ነው)፡ ዳግመኛ፡እግዚአብሔርን፡ጥቂት፡ወራት፡ደጅ፡እጠናዋለኹ፤ዳግመኛም፡መከራውን፡እታገሠዋለኹ፥የቀድሞ፡ ኑሮዬንም፡ተስፋ፡አደርገዋለኹ፡ትላለኽን፧አለችው።እንደዚህሳ፡እንዳትል፡ከዚህ፡ዓለም፥እንሆ፥ስም፡ አጠራርኽ፡ጠፋ፤ሴቶች፡ልጆቼና፡ወንዶች፡ልጆቼም፡ሞቱ፡እኔስ፡ዘጠኝ፡ወር፡ሳረግዝ፡ሳምጥ፡ስወልድ፡ ሳይረቡኝ፡ሳይጠቅሙኝ፡በከንቱ፡ደከምኹ፡አለች።አንተም፡በመግል፡ተውጠኽ፡በትል፡ተከበ፟ኽ፡ ትኖራለኽ፤ሌሊቱን፡ዅሉ፡ስትዛብር፡ታድራለኽ።እኔ፡ግን፡እየዞርኹ፡እቀላውጣለኹ።ከአንዱ፡አገር፡ወደ፡ አንዱ፡አገር፡ከአንዱ፡ቤት፡ወደ፡አንዱ፡ቤት፡እኼዳለኹ፤ከድካሜ፡በእኔ፡ላይ፡ካለ፡ከችግሬም፡ዐርፍ፡ ዘንድ፡ከጧት፡ዠምሮ፡ፀሓይ፡እስኪገባ፡ድረስ፡እጠብቃለኹ፤አኹን፡ግን፡እግዚአብሔርን፡የማይገ፟ባ፟፡ቃል፡ ተናግረኸው፡ሙት፡አለች።

10ርሱ፡ግን፡አንቺ፡ከሰነፎች፡ሴቶች፡እንደ፡አንዲቱ፡ተናገርሽ፤ከእግዚአብሔር፡እጅ፡መልካሙን፡ ተቀበልን፥ክፉ፡ነገርንስ፡አንቀበልምን፧አላት።በዚህ፡ዅሉ፡ኢዮብ፡በከንፈሩ፡አልበደለም። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org

11ሦስቱም፡የኢዮብ፡ወዳጆች፡ይህን፡የደረሰበትን፡ክፉ፡ነገር፡ዅሉ፡ሰምተው፡ከየአገራቸው፡ መጡ፤እነርሱም፡ቴማናዊው፡ኤልፋዝ፥ሹሐዊው፡በልዳዶስ፥ነዕማታዊው፡ሶፋር፡ነበሩ።እነርሱም፡ ሊያዝኑለትና፡ሊያጽናኑት፡በአንድነት፡ወደ፡ርሱ፡ለመምጣት፡ተስማሙ።

12ከሩቅም፡ኾነው፡ዐይናቸውን፡ባነሡ፡ጊዜ፡አላወቁትም፤ድምፃቸውንም፡አሰምተው፡ አለቀሱ፤እያንዳንዳቸውም፡መጐናጸፊያቸውን፡ቀደዱ፥ወደ፡ላይም፡ወደ፡ራሳቸው፡ላይ፡ትቢያ፡ነሰነሱ።

13ሰባት፡ቀንና፡ሰባት፡ሌሊትም፡ከርሱ፡ጋራ፡በምድር፡ላይ፡ተቀመጡ፤ሕመሙም፡እጅግ፡እንደ፡በዛ፡ አይተዋልና፥ከነርሱ፡አንድ፡ቃል፡የሚናገረው፡አልነበረም።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source