1ከዚያም፡በዃላ፡ኢዮብ፡አፉን፡ከፍቶ፡የተወለደበትን፡ቀን፡ረገመ።
2ኢዮብም፡መለሰ፡እንዲህ፡አለ፦
3ያ፡የተወለድኹበት፡ቀን፡ይጥፋ፥ ያም፦ወንድ፡ልጅ፡ተፀነሰ፡የተባለበት፡ሌሊት።
4ያ፡ቀን፡ጨለማ፡ይኹን፤ እግዚአብሔር፡ከላይ፡አይመልከተው፥ ብርሃንም፡አይብራበት።
5ጨለማና፡የሞት፡ጥላ፡የራሳቸው፡ገንዘብ፡ያድርጉት፤ ዳመናም፡ይረፍበት፤ የቀን፡ጨለማ፡ዅሉ፡ያስፈራው።
6ያን፡ሌሊት፡ጨለማ፡ይያዘው፤ በዓመቱ፡ቀኖች፡መካከል፡ደስ፡አይበለው፤ በወሮች፡ውስጥ፡ገብቶ፡አይቈጠር።
7እንሆ፥ያ፡ሌሊት፡መካን፡ይኹን፤ እልልታ፡አይግባበት።
8ሌዋታንን፡ለማንቀሳቀስ፡የተዘጋጁ፡ ቀኑን፡የሚረግሙ፡ይርገሙት።
9አጥቢያ፡ኮከቦች፡ይጨልሙ፤ ብርሃንን፡ቢጠባበቅ፡አያግኘው፥ የንጋትንም፡ቅንድብ፡አይይ፤
10የእናቴን፡ማሕፀን፡ደጅ፡አልዘጋምና፥ መከራንም፡ከዐይኔ፡አልሰወረምና።
11በማሕፀን፡ሳለኹ፡ስለ፡ምን፡አልሞትኹም፧ ከሆድስ፡በወጣኹ፡ጊዜ፡ፈጥኜ፡ስለ፡ምን፡አልጠፋኹም፧
12ጕልበቶች፡ስለ፡ምን፡ተቀበሉኝ፧ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org ጡትስ፡ስለ፡ምን፡ጠባኹ፧
13አኹን፡ተኝቼ፡ዝም፡ባልኹ፡ነበር፤ አንቀላፍቼ፡ባረፍኹ፡ነበር፤
14የፈረሰውን፡ለራሳቸው፡ከሚሠሩት፡ ከምድር፡ነገሥታትና፡መካሮች፡ጋራ፥
15ወይም፡ቤታቸውን፡ብር፡ከሞሉ፡ ወርቅም፡ካላቸው፡መኳንንት፡ጋራ፥
16ወይም፡እንደ፡ተቀበረ፡ጭንጋፍ፥ ብርሃንም፡እንዳላዩ፡ሕፃናት፡በኾንኹ፡ነበር።
17ክፉዎች፡በዚያ፡መናደዳቸውን፡ይተዋሉ፤ በዚያም፡ደካማዎች፡ያርፋሉ።
18በዚያ፡ግዞተኛዎች፡በአንድነት፡ተዘልለው፡ተቀምጠዋል፤ የአስጨናቂውን፡ድምፅ፡አይሰሙም።
19ታናሽና፡ታላቅ፡በዚያ፡አሉ፤ ባሪያም፡ከጌታው፡ነጻ፡ወጥቷል።
20በመከራ፡ላሉት፡ብርሃን፥ ነፍሳቸው፡መራራ፡ለኾነችባቸው፥
21የተሰወረ፡ሀብትን፡ከሚቈፍሩ፡ይልቅ፡ ሞትን፡ለሚጠብቁ፡ለማያገኙትም፥
22መቃብርን፡ባገኙ፡ጊዜ፡ በእልልታ፡ደስ፡ለሚላቸው፥ሐሤትንም፡ለሚያደርጉ፡ ሕይወት፡ስለ፡ምን፡ተሰጠ፧
23መንገዱ፡ለተሰወረበት፡ሰው፥ እግዚአብሔርም፡በዐጥር፡ላጠረው፡ ብርሃን፡ስለ፡ምን፡ተሰጠ፧
24ከእንጀራዬ፡በፊት፡ልቅሶዬ፡መጥቷልና፥ ጩኸቴም፡እንደ፡ውሃ፡ፈስሷል።
25የፈራኹት፡ነገር፡መጥቶብኛልና፥ የደነገጥኹበትም፡ደርሶብኛል።
26ተዘልዬ፡አልተቀመጥኹም፥አልተማመንኹም፥አላረፍኹም፤ ነገር፡ግን፡መከራ፡መጣብኝ።