Skip to content
← Nahum

Chapter 2 · Amharic

Nahum

1የሚቀጠቅጥ፡ባንተ፡ላይ፡ወጥቷል፤ምሽግን፡ጠብቅ፥መንገድንም፡ሰልል፤ወገብኽን፡አጽና፥ኀይልኽንም፡ እጅግ፡አበርታ።

2ዘራፊዎች፡ዘርፈዋቸዋልና፥የወይናቸውንም፡ዐረግ፡አጥፍተዋልና፥እግዚአብሔር፡የያዕቆብን፡ክብር፡እንደ፡ እስራኤል፡ክብር፡ይመልሳል። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org

3የኀያላኑ፡ጋሻ፡ቀልቷል፥ጽኑዓንም፡ቀይ፡ልብስ፡ለብሰዋል።ርሱም፡በሚያዘጋጅበት፡ቀን፡ሠረገላዎች፡ እንደ፡እሳት፡ይንቦገቦጋሉ፤የጦሩም፡ሶማያ፡ይወዛወዛል።

4ሠረገላዎች፡በመንገድ፡ላይ፡ይነጕዳሉ፥አደባባይም፡ይጋጫሉ፤መልካቸው፡እንደ፡ፋና፡ነው፥እንደ፡ መብረቅም፡ይከንፋሉ።

5መሳፍንቱን፡ያስባል፤በአረማመዳቸው፡ይሰናከላሉ፤ፈጥነው፡በቅጥሯ፡ላይ፡ይወጣሉ፥መጠጊያም፡ ተዘጋጀለት።

6የወንዞቹም፡መዝጊያዎች፡ተከፈቱ፥የንጉሡ፡ቤትም፡ቀለጠች።

7ንግሥት፡ተገለጠች፥ተማረከችም፥ሴቶች፡ባሪያዎቿም፡እንደ፡ርግብ፡እየጮኹና፡ደረታቸውን፡እየመቱ፡ ዋይ፡ዋይ፡ይላሉ።

8ነነዌ፡ግን፡ከዱሮ፡ዘመን፡ዠምራ፡እንደ፡ተከማቸ፡ውሃ፡ነበረች፤አኹን፡ግን፡ ይሸሻሉ፤እነርሱም፦ቁሙ፥ቁሙ፡ይላሉ፥ነገር፡ግን፥የሚመለስ፡የለም።

9መዝገቧ፡መጨረሻ፡የለውምና፥የከበረውም፡የዕቃዋ፡ዅሉ፡ብዛት፡አይቈጠርምና፡ብሩን፡ በዝብዙ፥ወርቁንም፡በዝብዙ።

10ባዶና፡ባድማ፡ምድረ፡በዳም፡ኾናለች፤ልብ፡ቀልጧል፥ጕልበቶችም፡ተብረክርከዋል፤በወገብም፡ዅሉ፡ ሕማም፡አለ፥የሰዎችም፡ዅሉ፡ፊት፡ጠቍሯል።

11የአንበሳዎችም፡መደብ፥የአንበሳዎችም፡ደቦል፡የሚሰማራበት፥አንበሳውና፡አንበሳዪቱ፡ግልገሉም፡ሳይፈሩ፡ የሚኼዱት፡ስፍራ፡ወዴት፡ነው፧

12አንበሳው፡ለልጆቹ፡የሚበቃውን፡ነጠቀ፥ለእንስቶቹም፡ሰበረላቸው፡ዋሻውን፡በንጥቂያ፥መደቡንም፡ በቅሚያ፡ሞልቶታል።

13እንሆ፥ባንቺ፡ላይ፡ነኝ፥ይላል፡የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፤ሠረገላዎቿንም፡አቃጥዬ፡ አጤሳለኹ፥ሰይፍም፡የአንበሳ፡ደቦሎችሽን፡ይበላቸዋል፤ንጥቂያሽንም፡ከምድር፡አጠፋለኹ፥የመልክተኛዎችሽን፡ ድምፅ፡ከእንግዲህ፡ወዲህ፡አይሰማም።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source