Skip to content
← Nehemiah

Chapter 10 · Amharic

Nehemiah

1ያተሙትም፡እነዚህ፡ናቸው፤የሐካልያ፡ልጅ፡ሐቴርሰታ፡ነሐምያ፥

2ሴዴቅያስ፥ሰራያ፥

3ዐዛርያስ፥ኤርምያስ፥ፋስኮር፥አማርያ፥መልክያ፥

5ሐጡስ፥ሰበንያ፥መሉክ፥ካሪም፥

6ሜሪሞት፥ዐብድዩ፥ዳንኤል፥ጌንቶን፥ባሮክ፥

8ሜሱላም፥አብያ፥ሚያሚን፥መዓዝያ፥ቤልጋል፥ሸማያ፤እነዚህ፡ካህናት፡ነበሩ።

9ሌዋውያኑም፤የአዛንያ፡ልጅ፡ኢያሱ፥ከኤንሐዳድ፡ልጆች፡ቢንዊ፥ቀድምኤል፤

10ወንድሞቻቸውም፡ሰባንያ፥ሆዲያ፥ቆሊጣስ፥

11ፌልያ፥ሐናን፥ሚካ፥ረአብ፥ሐሸብያ፥

13ዘኩር፥ሰራብያ፥ሰበንያ፥ሆዲያ፥ባኒ፥ብኒኑ።

14የሕዝቡ፡አለቃዎች፤ፋሮስ፥ፈሐት፡ሞዐብ፥

15ዔላም፥ዛቱዕ፥ባኒ፥ቡኒ፥ዓዝጋድ፥ቤባይ፥

17አዶንያስ፥በጉዋይ፥ዓዲን፥አጤር፥ሕዝቅያስ፥

18ዓዙር፥ሆዲያ፥ሐሱም፥ቤሳይ፥

19ሐሪፍ፥ዐናቶት፥ኖባይ፥

20መግጲዓስ፥ሜሱላም፥ኤዚር፥

21ሜሴዜቤል፥ሳዶቅ፥ያዱአ፥

22ፈላጥያ፥ሐናን፥ዐናያ፥

23ሆሴዕ፥ሐናንያ፥ዐሱብ፥

25አሎኤስ፥ፈልሃ፥ሶቤቅ፥ሬሁም፥ሐሰብና፥

27መዕሴያ፥አኪያ፥ሐናን፥ዐናን፥መሉክ፥ካሪም፥በዓና።

28የቀሩትም፡ሕዝብ፥ካህናቱም፥ሌዋውያኑም፥በረኛዎቹም፥መዘምራንም፥ናታኒምም፥ከምድርም፡አሕዛብ፡ ወደእግዚአብሔር፡ሕግ፡ራሳቸውን፡የለዩ፡ዅሉ፥ሚስቶቻቸውም፥ወንዶችና፡ሴቶች፡ ልጆቻቸውም፥የሚያውቁትና፡የሚያስተውሉትም፡ዅሉ፡ወደ፡ወንድሞቻቸው፡ወደ፡ታላላቆቻቸው፡ተጠጉ፤

29በእግዚአብሔርም፡ባሪያ፡በሙሴ፡እጅ፡በተሰጠው፡በእግዚአብሔር፡ሕግ፡ይኼዱ፡ዘንድ፥የጌታችንንም፡ የእግዚአብሔርን፡ትእዛዝ፡ዅሉ፡ፍርዱንም፡ሥርዐቱንም፡ይጠብቁና፡ያደርጉ፡ዘንድ፡ርግማንና፡መሐላውን፡ አደረጉ።

30ሴቶች፡ልጆቻችንንም፡ለምድር፡አሕዛብ፡አንሰጥም፥ሴቶች፡ልጆቻቸውንም፡ለልጆቻችን፡አንወስድም፤

31የምድርን፡አሕዛብ፡ሸቀጥና፡ልዩ፡ልዩ፡እኽል፡ሊገበዩ፡በሰንበት፡ቀን፡ቢያመጡ፥በሰንበት፡ወይም፡ በተቀደሰው፡ቀን፡ከነርሱ፡አንገዛም፤የሰባተኛውንም፡ዓመት፡ፍሬና፡ዕዳን፡ማስከፈል፡እንተዋለን፡ብለው፡ማሉ።

33ስለአምላካችንም፡ቤት፡አገልግሎት፥ስለ፡ገጸ፡ኅብስትም፥ዘወትርም፡በሰንበትና፡በመባቻ፡ስለ፡ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org ማቅረብ፡ስለእኽሉ፡ቍርባንና፡ስለሚቃጠል፡መሥዋዕት፥ስለ፡በዓላትም፥ስለ፡ተቀደሱትም፡ ነገሮች፥ለእስራኤልም፡ስለሚያስተሰርየው፡ስለኀጢአት፡መሥዋዕት፥ስለአምላካችንም፡ቤት፡ሥራ፡ዅሉ፡ በየዓመቱ፡የሰቅል፡ሢሶ፡እናመጣ፡ዘንድ፡ትእዛዝ፡በራሳችን፡ላይ፡አደረግን።

34እኛም፥ካህናቱና፡ሌዋውያኑ፡ሕዝቡም፥እንደ፡አባቶቻችን፡ቤቶች፡በተወሰነ፡ጊዜ፡በየዓመቱ፡ ወደአምላካችን፡ቤት፡አምጥተን፡በሕጉ፡እንደ፡ተጻፈ፡በአምላካችን፡በእግዚአብሔር፡መሠዊያ፡ላይ፡ይቃጠል፡ ዘንድ፡ስለዕንጨት፡ቍርባን፡ዕጣ፡ተጣጣልን፤

35በየዓመቱም፡የመሬታችንን፡በኵራት፡የዅሉ፡ዐይነት፡ዛፍ፡የፍሬ፡ዅሉ፡በኵራት፡ዅሉ፡ወደእግዚአብሔር፡ ቤት፡እናመጣ፡ዘንድ፥

36በሕጉም፡እንደ፡ተጻፈ፡የልጆቻችንና፡የእንስሳዎቻችንን፡በኵራት፥የበሬዎቻችንንና፡የበጎቻችንን፡በኵራት፡ በአምላካችን፡ቤት፡ወደሚያገለግሉት፡ካህናት፡ወደአምላካችን፡ቤት፡እናመጣ፡ዘንድ፥

37የእኽላችንንም፡በኵራት፥የእጅ፡ማንሣታችንን፡ቍርባን፥የዛፍ፡ዅሉ፡ፍሬ፥ወይኑንና፡ዘይቱንም፡ወደ፡ ካህናቱ፡ወደአምላካችን፡ቤት፡ጓዳዎች፡እናመጣ፡ዘንድ፥ሌዋውያኑም፡ከከተማዎቻችን፡ዕርሻ፡ዅሉ፡ዓሥራት፡ ይቀበላሉና፡የመሬታችንን፡ዓሥራት፡ወደ፡ሌዋውያን፡እናመጣ፡ዘንድ፡ማልን።

38ሌዋውያኑም፡ዓሥራቱን፡በተቀበሉ፡ጊዜ፡የአሮን፡ልጅ፡ካህኑ፡ከሌዋውያን፡ጋራ፡ይኹን፤ሌዋውያኑም፡ የዓሥራቱን፡ዓሥራት፡ወደአምላካችን፡ቤት፡ወደ፡ጓዳዎች፡ወደዕቃ፡ቤት፡ያምጡት።

39የእስራኤል፡ልጆችና፡የሌዊ፡ልጆችም፡የእኽሉንና፡የወይኑን፡የዘይቱንም፡የማንሣት፡ቍርባንን፡የመቅደሱ፡ ዕቃዎችና፡የሚያገለግሉት፡ካህናት፡በረኛዎቹና፡መዘምራኑ፡ወዳሉባቸው፡ጓዳዎች፡ያግቡት፤እንዲሁም፡ የአምላካችንን፡ቤት፡ከቶ፡አንተውም።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source