1በዚህም፡ወር፡በኻያ፡አራተኛው፡ቀን፡የእስራኤል፡ልጆች፡ጾመው፥ማቅም፡ለብሰው፥በላያቸውም፡ትቢያ፡ ነስንሰው፡ተከማቹ።
2የእስራኤልም፡ዘር፡ከእንግዳዎች፡ዅሉ፡ራሳቸውን፡ለዩ፥ቆመውም፡ኀጢአታቸውንና፡የአባቶቻቸውን፡ ኀጢአት፡ተናዘዙ።
3በየስፍራቸውም፡ቆመው፡የአምላካቸውን፡የእግዚአብሔርን፡የሕግ፡መጽሐፍ፡የቀን፡ሩብ፡ያኽል፡ አነበቡ፤ሦስት፡የቀን፡ሩብም፡ያኽል፡ተናዘዙ፥ለአምላካቸው፡ለእግዚአብሔርም፡ሰገዱ። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org
4ሌዋውያኑም፡ኢያሱና፡ባኒ፥ቀድምኤል፥ሰበንያ፥ቡኒ፥ሰራብያ፥ባኒ፥ክናኒ፡በደረጃዎች፡ላይ፡ቆመው፡ ወደ፡አምላካቸው፡ወደ፡እግዚአብሔር፡በታላቅ፡ድምፅ፡ጮኹ።
5ሌዋውያኑም፡ኢያሱ፥ቀድምኤል፥ባኒ፥አሰበንያ፥ሰራብያ፥ሆዲያ፥ሰበንያ፥ፈታያ፡እንዲህ፡አሉ።ቆማችኹ፡ ከዘለዓለም፡እስከ፡ዘለዓለም፡አምላካችንን፡እግዚአብሔርን፡ባርኩ።እንዲህም፡በሉ።በበረከትና፡በምስጋና፡ዅሉ፡ ላይ፡ከፍ፡ከፍ፡ያለው፡ክቡር፡ስምኽ፡ይባረክ።
6አንተ፡ብቻ፡እግዚአብሔር፡ነኽ፤ሰማዩንና፡የሰማያት፡ሰማይን፡ሰራዊታቸውንም፡ዅሉ፥ምድሩንና፡በርሷ፡ ላይ፡ያሉትን፡ዅሉ፥ባሕሮቹንና፡በእነርሱ፡ውስጥ፡ያለውን፡ዅሉ፥ፈጥረኻል፥ዅሉንም፡ሕያው፡ አድርገኸዋል፤የሰማዩም፡ሰራዊት፡ለአንተ፡ይሰግዳሉ።
7አንተ፡እግዚአብሔር፡አምላክ፡ነኽ፤አብራምን፡መረጥኽ፥ከኡር፡ከላውዴዎንም፡አወጣኸው፥ስሙንም፡ አብርሃም፡አልኸው፤
8ልቡም፡በፊትኽ፡የታመነ፡ኾኖ፡አገኘኸው፤የከነዓናዊውንና፡የኬጢያዊውን፡የአሞራዊውንም፡የፌርዛዊውንም፡ የኢያቡሳዊውንም፡የጌርጌሳዊውንም፡ምድር፡ለርሱና፡ለዘሩ፡ትሰጥ፡ዘንድ፡ከርሱ፡ጋራ፡ቃል፡ኪዳን፡አደረግኽ፡ አንተም፡ጻድቅ፡ነኽና፥ቃልኽን፡ፈጸምኽ።
9በግብጽም፡ሳሉ፡የአባታችንን፡መከራ፡አየኽ፥በቀይ፡ባሕርም፡ሳሉ፡ጩኸታቸውን፡ሰማኽ፤
10እንደ፡ታበዩባቸውም፡ዐውቀኽ፡ነበርና፥በፈርዖንና፡በባሪያዎቹ፡ዅሉ፡በምድሩም፡ሕዝብ፡ዅሉ፡ላይ፡ ምልክትና፡ተኣምራት፡አሳየኽ፤ዛሬም፡እንደኾነው፡ስምኽን፡አስጠራኽ።
11ከፊታቸውም፡ባሕሩን፡ከፈልኽ፥በባሕሩም፡መካከል፡በደረቅ፡አልፉ፤ጠላቶቻቸውን፡ግን፡ድንጋይ፡ ለጥልቅ፡ውሃ፡እንዲጣል፡በቀላይ፡ውስጥ፡ጣልኻቸው።
12የሚኼዱበትንም፡መንገድ፡ታበራላቸው፡ዘንድ፡በቀን፡በደመና፡ዐምድ፥በሌሊትም፡በእሳት፡ዐምድ፡ መራኻቸው።
13ወደሲናም፡ተራራ፡ወረድኽ፥ከሰማይም፡ተናገርኻቸው፤ቅኑን፡ፍርድና፡እውነቱን፡ሕግ፡መልካሙንም፡ ሥርዐትና፡ትእዛዝ፡ሰጠኻቸው፤
14የተቀደሰውንም፡ሰንበትኽን፡አስታወቅኻቸው፥ትእዛዝንና፡ሥርዐትን፡ሕግንም፡በባሪያኽ፡በሙሴ፡እጅ፡ አዘዝኻቸው።
15ለራባቸውም፡ከሰማይ፡እንጀራ፡ሰጠኻቸው፥ለጥማታቸውም፡ከአለቱ፡ውሃ፡ አመጣኽላቸው፤ወደማልኽላቸውም፡ምድር፡ገብተው፡ይወርሱ፡ዘንድ፡አዘዝኻቸው።
16ነገር፡ግን፥እነርሱና፡አባቶቻችን፡ታበዩ፥ዐንገታቸውንም፡አደነደኑ፥ትእዛዝኽንም፡አልሰሙም፥
17ለመስማትም፡እንቢ፡አሉ፥ያደረግኽላቸውንም፡ተኣምራት፡አላሰቡም፤ዐንገታቸውንም፡ አደነደኑ፥በዐመፃቸውም፡ወደ፡ባርነታቸው፡ይመለሱ፡ዘንድ፡አለቃ፡አደረጉ፤አንተ፡ግን፡ይቅር፡ባይ፥ቸርና፡ መሓሪ፡አምላክ፥ለቍጣም፡የምትዘገይ፥ምሕረትንም፡የምታበዛ፡ነኽ፥አልተውኻቸውም።
18ቀልጦ፡የተሠራውንም፡እንቦሳ፡አድርገው፦ከግብጽ፡ያወጣኽ፡አምላክኽ፡ይህ፡ነው፡ባሉ፡ጊዜ፥እጅግም፡ ባስቈጡኽ፡ጊዜ፥
19አንተ፡በምሕረትኽ፡ብዛት፥በምድረ፡በዳ፡አልተውኻቸውም፤በመንገድም፡ይመራቸው፡ዘንድ፡የደመና፡ ዐምድ፡በቀን፥የሚኼዱበትንም፡መንገድ፡ያበራላቸው፡ዘንድ፡የእሳት፡ዐምድ፡በሌሊት፡ከነርሱ፡አልራቀም።
20ያስተምራቸውም፡ዘንድ፡መልካሙን፡መንፈስኽን፡ሰጠኻቸው፥መናኽንም፡ከአፋቸው፡ አልከለከልኽም፥ለጥማታቸውም፡ውሃ፡ሰጠኻቸው።
21አርባ፡ዓመትም፡በምድረ፡በዳ፡መገብኻቸው፥ምንም፡አላጡም፤ልብሳቸውም፡አላረጅም፥እግራቸውም፡ አላበጠም። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org
22መንግሥታትንና፡አሕዛብን፡ከፍለኽ፡ሰጠኻቸው፤የሐሴቦንን፡ንጉሥ፡የሴዎንን፡ምድር፥የባሳንንም፡ንጉሥ፡ የዐግን፡ምድር፡ወረሱ።
23ልጆቻቸውንም፡እንደሰማይ፡ከዋክብት፡አበዛኽ፤ይገቡና፡ይወርሱ፡ዘንድ፡ለአባቶቻቸው፡ ወደተናገርኽላቸውም፡ምድር፡አገባኻቸው።
24ልጆቹም፡ገብተው፡ምድሩን፡ወረሱ፥የምድሩን፡ሰዎች፡ከነዓናውያንን፡በፊታቸው፡ አዋረድኽ፤የሚወዱትንም፡ነገር፡ያደረጉባቸው፡ዘንድ፡እነርሱንና፡ነገሥታታቸውን፡የምድሩንም፡አሕዛብ፡ በእጃቸው፡አሳልፈኽ፡ሰጠኻቸው።
25ምሽጎቹንም፡ከተማዎች፡የሰባውንም፡ምድር፡ወሰዱ፤መልካሙን፡ነገር፡የሞሉትን፡ቤቶች፥የተማሱትንም፡ ጕድጓዶች፥ወይኖቹንና፡ወይራዎቹን፡ብዙዎቹንም፡የፍሬ፡ዛፎች፡ወረሱ፤በሉም፥ጠገቡም፥ወፈሩም፥በታላቅ፡ በጎነትኽም፡ደስ፡አላቸው።
26ነገር፡ግን፥እንቢተኛዎች፡ነበሩ፥ዐመፁብኽም፥ሕግኽንም፡ወደ፡ዃላቸው፡ጣሉት፤ወዳንተም፡ይመለሱ፡ ዘንድ፡የመሰከሩባቸውን፡ነቢያትኽን፡ገደሉ፥እጅግም፡አስቈጡኽ።
27ስለዚህ፥ለጠላቶቻቸው፡እጅ፡አሳልፈኽ፡ሰጠኻቸው፥አስጨነቋቸውም፤በመከራቸውም፡ጊዜ፡ወዳንተ፡ ጮኹ፥ከሰማይም፡ሰማኻቸው፤እንደ፡ምሕረትኽም፡ብዛት፡ከጠላቶቻቸው፡እጅ፡ያዳኗቸውን፡ታዳጊዎችን፡ ሰጠኻቸው።
28ባረፉም፡ጊዜ፡ተመልሰው፡በፊትኽ፡ክፉ፡አደረጉ፤በጠላቶቻቸው፡እጅ፡ ተውኻቸው፥ገዟቸውም፤ተመልሰውም፡ወዳንተ፡በጮኹ፡ጊዜ፡ከሰማይ፡ሰማኻቸው፥እንደ፡ምሕረትኽም፡ ብዛት፡ታደግኻቸው፤
29ወደ፡ሕግኽም፡ትመልሳቸው፡ዘንድ፡አስመሰከርኽባቸው፤ነገር፡ግን፥ታበዩ፥ትእዛዝኽንም፡ አልሰሙም፥ሰውም፡ባደረገው፡ጊዜ፡በሕይወት፡የሚኖርበትን፡ፍርድኽን፡ተላለፉ፤ትከሻቸውንም፡ ሰጡ፥ዐንገታቸውን፡አደነደኑ፥አልሰሙምም።
30ነገር፡ግን፥ብዙ፡ዓመታት፡ታገሥኻቸው፥በነቢያትኽም፡እጅ፡በመንፈስኽ፡ መሰከርኽባቸው፤አላደመጡም፥ስለዚህም፡በምድር፡አሕዛብ፡እጅ፡አሳልፈኽ፡ሰጠኻቸው።
31ነገር፡ግን፥አንተ፡ቸርና፡መሓሪ፡አምላክ፡ነኽና፥በምሕረትኽ፡ብዛት፡ፈጽመኽ፡ አላጠፋኻቸውም፥አልተውኻቸውምም።
32አኹንም፡አምላካችን፡ሆይ፥ቃል፡ኪዳንንና፡ምሕረትን፡የምትጠብቅ፡ታላቅና፡ኀያል፡የተፈራኸውም፡ አምላክ፡ሆይ፥ከአሶር፡ነገሥታት፡ዘመን፡ዠምሮ፡እስከ፡ዛሬ፡ድረስ፡በእኛና፡በነገሥታታችን፡በአለቃዎቻችንም፡ በካህናታችንም፡በነቢያታችንም፡በአባቶቻችንም፡በሕዝብኽ፡ዅሉ፡ላይ፡የደረሰው፡መከራ፡ዅሉ፡በፊትኽ፡ጥቂት፡ መስሎ፡አይታይኽ።
33በደረሰብንም፡ነገር፡ዅሉ፡አንተ፡ጻድቅ፡ነኽ፥አንተ፡እውነት፡አድርገኻልና፥እኛም፡ኀጢአት፡ አድርገናል።
34ነገሥታታችንም፡አለቃዎቻችንም፡ካህናታችንም፡አባቶቻችንም፡ሕግኽን፡አልጠበቁም፥የመሰከርኽባቸውንም፡ ትእዛዝኽንና፡ምስክርኽን፡አልሰሙኽም።
35በመንግሥታቸውም፡በሰጠኻቸውም፡ታላቅ፡በጎነትኽ፥በፊታቸውም፡በሰጠኸው፡በሰባው፡ምድር፡ አላመለኩኽም፥ከክፉም፡ሥራቸው፡አልተመለሱም።
36እንሆ፥ዛሬ፡ባሪያዎች፡ነን፤ፍሬዋንና፡በረከቷን፡ይበሉ፡ዘንድ፡ለአባቶቻችን፡በሰጠኻት፡ ምድር፥እንሆ፥በርሷ፡ባሪያዎች፡ነን፥
37ስለ፡ኀጢአታችንም፡ለሾምኽብን፡ነገሥታት፡በረከቷን፡ታበዛለች፤ሰውነታችንንም፡ ይገዛሉ፥በእንስሳዎቻችንም፡የሚወዱትን፡ያደርጋሉ፥እኛም፡በጽኑ፡መከራ፡ላይ፡ነን። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org
38ስለዚህም፡ዅሉ፡የታመነውን፡ቃል፡ኪዳን፡አድርገን፡እንጽፋለን፤አለቃዎቻችንም፡ሌዋውያናችንም፡ ካህናታችንም፡ያትሙበታል።