1ሰባተኛውም፡ወር፡በደረሰ፡ጊዜ፡የእስራኤል፡ልጆች፡በከተማዎቻቸው፡ነበሩ።ሕዝቡም፡ዅሉ፡በውሃው፡በር፡ ፊት፡ወዳለው፡አደባባይ፡እንደ፡አንድ፡ሰው፡ኾነው፡ተሰበሰቡ፤እግዚአብሔርም፡ለእስራኤል፡ያዘዘውን፡ የሙሴን፡ሕግ፡መጽሐፍ፡ያመጣ፡ዘንድ፡ጸሓፊውን፡ዕዝራን፡ተናገሩት።
2ካህኑም፡ዕዝራ፡በሰባተኛው፡ወር፡በመዠመሪያው፡ቀን፡ሕጉን፡በማኅበሩ፡በወንዶችና፡በሴቶች፡ አስተውለውም፡በሚሰሙት፡ዅሉ፡ፊት፡አመጣው።
3በውሃውም፡በር፡ፊት፡ባለው፡አደባባይ፡ላይ፡ቆሞ፥ወንዶችና፡ሴቶች፡የሚያስተውሉም፡ሲሰሙ፥ከማለዳ፡ ዠምሮ፡እስከ፡ቀትር፡ድረስ፡አነበበው፤የሕዝቡም፡ዅሉ፡ዦሮ፡የሕጉን፡መጽሐፍ፡ለመስማት፡ያደምጥ፡ነበር።
4ጸሓፊውም፡ዕዝራ፡ስለዚህ፡ነገር፡በተሠራ፡በዕንጨት፡መረባርብ፡ላይ፡ቆሞ፡ነበር፤በአጠገቡ፡ መቲትያ፥ሽማዕ፥ዐናያ፥ኦርዮ፥ኬልቅያስ፥መዕሴያ፡በቀኙ፡ በኩል፥ፈዳያ፥ሚሳኤል፥መልክያ፥ሐሱም፥ሐሽበዳና፥ዘካርያስ፥ሜሱላም፡በግራው፡በኩል፡ቆመው፡ነበር።
5ዕዝራም፡በሕዝቡ፡ዅሉ፡ላይ፡ከፍ፡ብሎ፡ሕዝቡ፡ዅሉ፡እያዩ፡መጽሐፉን፡ገለጠ፤በገለጠውም፡ጊዜ፡ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org ሕዝቡ፡ዅሉ፡ቆሙ።
6ዕዝራም፡ታላቁን፡አምላክ፡እግዚአብሔርን፡ባረከ፤ሕዝቡም፡ዅሉ፡እጃቸውን፡እየዘረጉ፦አሜን፥አሜን፡ ብለው፡መለሱ።ራሳቸውንም፡አዘነበሉ፥በግንባራቸውም፡ተደፍተው፡ለእግዚአብሔር፡ሰገዱ።
7ደግሞ፡ኢያሱና፡ ባኒ፥ሰራብያ፥ያሚን፥ዐቁብ፥ሳባታይ፥ሆዲያ፥መዕሴያ፥ቆሊጣስ፥ዐዛርያስ፥ዮዛባት፥ሐናን፥ፌልያ፥ሌዋውያኑ ም፡ሕጉን፡ያስተውሉ፡ዘንድ፡ሕዝቡን፡ያስተምሩ፡ነበር፤ሕዝቡም፡በየስፍራቸው፡ቆመው፡ነበር።
8የእግዚአብሔርንም፡ሕግ፡መጽሐፍ፡አነበቡ፤ዕዝራም፡እግዚአብሔርን፡ማወቅ፡ያስተምርና፡ያስታውቅ፡ ነበር፥ሕዝቡም፡የሚነበበውን፡ያስተውሉ፡ነበር።
9ሐቴርሰታ፡ነሐምያም፡ጸሓፊውም፡ካህኑ፡ዕዝራ፡ሕዝቡንም፡የሚያስተምሩ፡ሌዋውያን፡ሕዝቡን፡ዅሉ፦ዛሬ፡ ለአምላካችን፡ለእግዚአብሔር፡የተቀደሰ፡ቀን፡ነው፤አታልቅሱ፡እንባም፡አታፍስሱ፡አሏቸው፤ሕዝቡ፡ዅሉ፡ የሕጉን፡ቃል፡በሰሙ፡ጊዜ፡ያለቅሱ፡ነበርና።
10ርሱም፦ኺዱ፥የሰባውንም፡ብሉ፥ጣፋጩንም፡ጠጡ፥ለእነዚያም፡ላልተዘጋጀላቸው፡ዕድል፡ፈንታቸውን፡ ስደዱ፤ዛሬ፡ለጌታችን፡የተቀደሰ፡ቀን፡ነው፤የእግዚአብሔርም፡ደስታ፡ኀይላችኹ፡ነውና፥አትዘኑ፡አላቸው።
11ሌዋውያንም፦ቀኑ፡የተቀደሰ፡ነውና፥ዝም፡በሉ፥አትዘኑም፡ብለው፡ሕዝቡን፡ዅሉ፡ጸጥ፡ያደርጉ፡ነበር።
12ሕዝቡም፡ዅሉ፡የተነገረላቸውን፡ቃል፡አስተውለዋልና፥ሊበሉና፡ሊጠጡ፥ዕድል፡ፈንታም፡ሊሰዱ፟፡ ደስታም፡ሊያደርጉ፡ኼዱ።
13በኹለተኛውም፡ቀን፡ከሕዝቡ፡ዅሉ፡የአባቶች፡ቤቶች፡አለቃዎች፡ካህናቱም፡ሌዋውያኑም፡የሕጉን፡ቃል፡ ይተረጕምላቸው፡ዘንድ፡ወደ፡ጸሓፊው፡ወደ፡ዕዝራ፡ተሰበሰቡ።
15በሰባተኛውም፡ወር፡ባለው፡በዓል፡የእስራኤል፡ልጆች፡በዳስ፡ይቀመጡ፡ዘንድ፡በከተማዎቻቸውና፡ በኢየሩሳሌምም፦ወደ፡ተራራ፡ኺዱ፤የዘይትና፡የበረሓ፡ወይራ፡የባርሰነትም፡የዘንባባም፡የለመለመውን፡ዛፍ፡ ቅርንጫፍ፡አምጡ፥እንደ፡ተጻፈውም፡ዳሶችን፡ሥሩ፡ብለው፡ይናገሩ፡ያውጁም፡ዘንድ፡እግዚአብሔር፡በሙሴ፡ እጅ፡እንዳዘዘ፡በሕጉ፡ውስጥ፡ተጽፎ፡አገኙ።
16ሕዝቡም፡ወጥተው፡አመጡ፤እያንዳንዱም፡በቤቱ፡ሰገነት፡ላይ፥በአደባባዩም፡ላይ፥በእግዚአብሔርም፡ ቤት፡አደባባዩ፡ላይ፥በውሃውም፡በር፡አደባባይና፡በኤፍሬም፡በር፡አደባባይ፡ላይ፡ዳስ፡ሠራ።
17ከምርኮም፡የተመለሱት፡ማኅበር፡ዅሉ፡ዳስ፡ሠሩ፥በዳሱም፡ውስጥ፡ተቀመጡ።ከነዌም፡ልጅ፡ከኢያሱ፡ ዘመን፡ዠምሮ፡እስከዚያ፡ቀን፡ድረስ፡የእስራኤል፡ልጆች፡እንዲህ፡ያለ፡አላደረጉም፡ነበር።እጅግም፡ታላቅ፡ ደስታ፡ኾነ።
18ከመዠመሪያውም፡ቀን፡ዠምሮ፡እስከመጨረሻው፡ቀን፡ድረስ፡ዕለት፡ዕለት፡የእግዚአብሔርን፡ሕግ፡ መጽሐፍ፡ያነብ፟፡ነበር።በዓሉን፡ሰባት፡ቀን፡ያኽል፡አደረጉ፤በስምንተኛውም፡ቀን፡እንደ፡ሕጉ፡የተቀደሰ፡ ጉባኤ፡ነበረ።